2ኛ ጴጥሮስናሙና
![2ኛ ጴጥሮስ](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans%2F52058%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
ጴጥሮስ በጥቃት ላይ ነው፡፡ የሀሰት አስተማሪዎች ኢየሱስ ስለ ወሲባዊ ዕርኩሰታቸውና ስለ ስግብግብነታቸው ሊፈርድ ዳግም ይመጣል ስለሚለው ተረት ከሰውታል፡፡ ይህ የሀሰት ትምህርት የኢየሱስን የገዢነት ስልጣን እና የፍርድ ቀን መምጣትን ይክዳል፤ ሰለሆነም ክርስቲያኖች የግድ አንድ የስነ-ምግባር ደንብ ይኑራቸው የሚለውን ይክዳል፡፡ በሌላ አባባል እግዚአብሔር ካልፈረደ የምንፈልገውን ሁሉ ማድረግ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ጴጥሮስ ግን እነኚህን እያንዳንዷን አመለካከት ይመታል፡፡
በመጀመሪያ ከኢየሱስ ስልጣን ጋር በተያያዘ ጴጥሮስ እርሱና ሌሎች ሐዋርያት የኢየሱስን ተአምራዊ መለወጥ የዓይን ምሥክሮች ስለመሆናቸው መናገሩ ተረት አይደለም ይላል።በወንጌልውስጥየኢየሱስተአምራዊለውጥሐዋርያቱኢየሱስዓለምንየመግዛትሥልጣንእንዳለውየተገነዘቡበትወቅትነው። እግዚአብሔር ከሰማይ ኢየሱስ የሚወደው ልጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡ በመጽሐፍቅዱስውስጥአንድንሰውከሙታንበማስነሳትየእስራኤልየመጀመሪያንጉሥ ከሆነውከሙሴ፤የተሃድሶ ሰው ከሚባለውከኤልያስጋርተቀላቅሏል። የሀሰት አስተማሪዎች ተሳስተዋል፡፡ የተዓምራዊ ለውጡ ኢየሱስ በህይወት ላይ፣ በሞት ላይ እና በዓለማት ላይ ስልጣን እንደተሰጠው ይገልጣል፤ ለዚህም ጴጥሮስ ምስክር ነው፡፡
ሁለተኛ ጴጥሮስ የሚመጣውን የፍርድ ቀን ያረጋግጣል፡፡የሐሰተኛአስተማሪዎችአንዱ መከራከሪያበትንቢትየተነገረለትየፍርድቀንሀሳብየሰውፈጠራእንጂየእግዚአብሔርአይደለምየሚልነበር። “ፍርድ” ሀይማኖተኞች በፍርሃት የስነ-ምግባር ቁጥጥር ጫና የሚያደርጉበት መሳሪያ ነው፡፡ ጴጥሮስ ግን የፍርድ ትንቢቶች ሰው ወለድ ፈጠራዎች ሳይሆኑ የመንፈስ ቅዱስ ውጤቶች ናቸው ይለናል፡፡ የሚመጣ የፍርድ ቀን የለም የሚለው ፍልስፍና ሰው ወለድ ነው፤ በእርግጥ ይህ ተቃውሞ በሚክዱት በመንፈስ ቅዱስ የተተነበየ ነበር፡፡
ይህ የማይቀረውን ፍርድ ክህደት ከጥንት የነበረ ሲሆን የሚያስከትለውም ነገር አለው፡፡ ጴጥሮስ ይህንን ሦስት ታዋቂ የፍርድ ታሪኮችን ከብሉይ ኪዳን በማንሳት ያረጋግጣል፤ እኚህም የእግዚአብሔር ልጆች መጣልን፣ የኖኅ ዘመንን ጎርፍ እና የሰዶምና ገሞራን ይጠቅሳል፡፡ በእነዚህ ታሪኮች ውስጥ የመላዕክት ፍጡራን፣ የኖኅ ዘመን ሰዎች እና የመንትዬዎቹከተሞችዜጎችሁሉምየእግዚአብሔርንየሥነምግባርሥልጣንይቃወማሉ፣የፆታስሜታቸውንናየቁሳዊፍላጎት እርኩሰታቸውንይከተላሉእንዲሁምበኃጢአተኞችሁሉላይ ሊከሰት ላለው ነገርምሳሌይሆናሉ።
በመጨረሻም ጴጥሮስ የሀሰት አስተማሪዎች ስለ ስነ-ምግባር የሚያራግቡትን ጉዳይ የማይቀረውን የኃጢአተኞችን ፍርድ ከማይቀረው የስነ-ምግባር የፃድቅ ትድግና ጋር በማጣመር ይዳስሳል፡፡ ኖኅና ሎጥ ሁለቱም ፃድቃን ሰዎች ነበሩ፤ ሁለቱም በዙሪያቸው ባለው የስነ-ምግባርና መንፈሳዊ ክፋት የተነሳ አዝነው ሁለቱም ግን ድነዋል፡፡ ፅድቅ ወሳኝነት አለው፡፡ ኢየሱስ ዳግም ይመጣል የሚለውን በመካድና ምንምዓይነትሥነምግባርንበማስፋፋትእኚህየሐሰትአስተማሪዎችቅዱሳትመጻሕፍትንእየካዱ ብቻ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከክፉው ዓለም ማንኛውንም ትድግና ጭምር እየካዱ እንጂ፡፡
ጴጥሮስ ይህን ዓይነት አስተሳሰብ እንስሳዊ ብሎ ይጠራዋል፡፡ እኚህሐሰተኛአስተማሪዎችከፍላጎታቸውወደፍላጐትይኳትናሉ፣ለመረዳትባልወደዱትነገርደግሞ ይጮኻሉ። በገንዘብምተገፋፍቶንግርቱንለከፍተኛተጫራችእንደሸጠው፤ እንዲሁምእንስሳውከጌታውተሽሎጤነኛእንደነበረውነቢይእንደ ሽማግሌው ነቢይ እንደ በለዓም ናቸው። ልክውሃ እንደሌለውምንጭ የኢየሱስንመምጣትእየካዱነፃነትየሚሉትንመስበክጥቅሙከንቱነትሲሆንሲከፋደግሞኢ-ሰብአዊነትነው። ስለዚህየእግዚአብሔርንሥልጣንበመፍራት ቅድሚያ ለሚሰጡት ለራሳቸውመሻት የገዛ ራሳቸውንባሪያያደርጋሉ።እናምልክእንደውሾችእናአሳማዎችየራሳቸውን ትፋትና ቆሻሻከመብላትውጪመርዳትአይችሉም፡፡
ወንጌሉ የት ነው?
ጴጥሮስ በመፋለም ላይ ነው፤ ይህንንም መናገር ትችላለህ፡፡ እርሱ ለእኛ እየነገረን ያለው የሀሰተኛ አስተማሪዎችን ለመቋቋም በመናገር ውስጥ ነው፡፡ አንዳንዶቻችንስለፍርድአይቀሬነትየጴጥሮስንከባድተግሣጽመስማትሊያስፈልገንይችላል። ሌሎቹ ደግሞ አስተማሪውስለኢየሱስመምጣትያለውንጥርጣሬአምነው ሲቀበሉከሥነምግባሩያነሰንጥብቅእምነትግን ይማርካቸውይሆናል። አንዳንዶቻችሁ ለራሳችሁ መሻት፣ እንዲሁም ከራስህ ውጪ ላለው ለሌላኛው ገዥ ስለማይቀረው የሕይወት ጥፋት የጴጥሮስን ማስጠንቀቂያ መስማት የግድ ይለናል፡፡
ነገርግንሁላችንምመታደግንናነፃ መውጣትንለጻድቃንየማይቀር የምሥራችመሆኑንመስማትየግድ ይለናል፡፡ ጴጥሮስ ኢየሱስን የሚያውቁ ሰዎች የእርሱን የፅድቅ ማንነት ይካፈላሉ ብሎ ነግሮናል፡፡ ታዳጊያችን አስተማማኝ ነው፤ እንደ ኖኅ ወደ ታች እየሰጠመች ላለችው ዓለም ፅድቅን መስበክ እንችላለን፡፡ ልክ እንደ ሎጥ ደግሞ በርኩሰቱ ስለጠፋው ዓለም በጥልቀት ሀዘን ማልቀስ እንችላለን። እኛ ደግሞ እንደ ሁለቱም ስለ ፍርዱ በማንበብ መቅረባችንን እርግጠኞች ነን፡፡ እግዚአብሔር ፃድቁን እንዳዳነ ታሪክ አለን፤ ይህንንም ንጉሱን፤ ልጁን ኢየሱስን ለምናውቅና ለምናምን እንዲሁ ያደርግልናል፡፡
በክፉ ላይ የሚፈርደውን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ ዓለምን የሚገዛውን እንዲሁም ፃድቁን ከፍርድ የሚያድነውን ኢየሱስን ማየት ይሁንልህ፡፡
ስለዚህ እቅድ
![2ኛ ጴጥሮስ](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans%2F52058%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
2ኛ የጴጥሮስ መጽሐፍ በዕምነት እንድታድግ፣ የሀሰት ትምህርቶችን እንድትቋቋም እና የኢየሱስን ዳግም ምፅዓት በጉጉት ስትጠባበቅ ደግሞ እግዚአብሔርን የመምሰል ህይወት እንድትኖር በዚህም እግዚአብሔርን ለመምሰል ላለው ኑሮ ሁሉን እንደሰጠህ እንድታውቅ ያነቃቃሃል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/