የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2ኛ ጴጥሮስናሙና

2ኛ ጴጥሮስ

ቀን {{ቀን}} ከ3

ሐዋሪያው ጴጥሮስ በመጨረሻው የሞት ጣር ላይ ነው፡፡ እናም 2ኛ ጴጥሮስ የኢየሱስ የቅርብ ደቀ-መዝሙር ስለሆነው የመጨረሻ ንግግር የሚያትት ነው፡፡ ኢየሱስ የእኛ እግዚአብሔርና አዳኛችን ነው በማለት ይጀምራል፡፡ በጴጥሮስ ዘመን የነበሩ ብዙዎች እኚህን የአዋጅ ንግግሮችና ውጤታቸውን ክደዋል በዚህም ጴጥሮስ ኋላ ላይ በደብዳቤው እነዚህን የሀሰት አስተማሪዎች ትኩረት አድርጓል፡፡ ለአሁኑ ጴጥሮስ ከመሞቱ በፊት አንድ የስብከት መድረክ ላይ መስበክ ይፈልጋል፡፡

የስብከቱዋናጭብጥደግሞመለኮታዊኃይሉንተጠቅሞኢየሱስእግዚአብሔርንበመምሰልእንድንኖርየሚያስፈልገንንሁሉእንደሰጠንከማስቻሉም በላይ አምላካዊሕይወትምየሚመጣውኢየሱስንበማወቅመሆኑን አሳይቷል። ኢየሱስ አምላካችንና አዳኛችን መሆኑን ማወቃችን ልክ ስለ ኢየሱስ የሆነ እውነታ የማወቅ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህሪም መካፈል ጭምር ነው፡፡ ጴጥሮስእያለ ያለው እንካፈላለን፣ህብረት እናደርጋለን እንዲሁምበእግዚአብሔርባህሪወይምጽድቅእንሞላለን ማለቱ ነው።ከመለኮት ባህሪ የመካፈሉ ጉዳይ እግዚአብሔር በመልካምነቱ ቃሉን እየፈፀመ ነው እያለን ነው፡፡ ጴጥሮስ እነዚያ የተስፋ ቃሎች ምን እንደሆኑ በግልፅ አያብራራም ነገር ግን ምን እንደሚያደርጉ ግን ያሳያል፡፡ የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎችከሥነምግባራዊፍፁምመለኮታዊተፈጥሮውጋርአንድ ያደርገናል፤ካለመታመንም ያስመልጠናል፡፡

የስና-ምግባር ብልሹነት ምድራችንን ይመርዛል፡፡ እርስበርስያለን ግንኙነትእንዲሁም ከእግዚአብሔርጋርያለንግንኙነትብዙውንጊዜባለማወቅ፣ራስንባለመግዛት፣በቸልተኝነት፣በመራርነትናበጥላቻተለይቶይታወቃል። ነገር ግን በመለኮታዊኃይሉየባህሪውፍፅምናእንካፈል ዘንድ ኢየሱስወደክብሩጽድቅይጠራናል። በኢየሱስ የባህሪ ብልሹነትን እናመልጥበታለን፡፡

ይህ ማምለጥ ግን ክስተትም ጉዞም ነው፡፡ ኢየሱስ የሚያድነን በእምነት ነው ይሁን እንጂ እኛም ታማኝነታችን ላይ የስነ-ምግባር ጨዋነትን ለመጨመር ማንኛውንም ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ እግዚአብሔር እኛን ወደ ራሱ ፍፁም ጥበቡ፣ ራስን ወደ መግዛት፣ ወደ ታማኝነቱ ወደ ወዳጅነት እና ወደ ፍቅሩ ለመጨመር መለኮታዊ ኃይሉን ይጠቀማል፡፡

እግዚአብሔርሕዝቡንበሥነምግባርልዕልናውስጥለማካተቱስርዓትምላሽ በመስጠት ረገድእየጨመረ ባለው የስነ-ምግባር ማንነትና እግዚአብሔርን የመምሰል ጉዞ ውስጥ በመኖር በመለኮቱ እንሳተፋለን፡፡ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔርነቱና እንደ አዳኝነቱ የሚያውቁት ሁሉ በዚህ መንገድ እያደጉ ናቸው፡፡

ጴጥሮስወደመቃብርየወሰደውየምስራችዜናኢየሱስያዳነን በመለኮታዊ ፍፅምናው እንድንሳተፍና በምድር ላይ ደግሞ ልክ እንደ እርሱ እንድንኖር ነው፡፡ጨዋነት የጎደላቸው፣በስነ-ምግባር ያልታነፁናፍቅርየሌላቸውለምንእንደዳኑ እንኳንረስተዋል። ነገርግንበመለኮታዊውውስጥየሚካፈሉትበደህንነታቸው ላይእየጨመረ የሚሄድ መተማመን እንዲሁም በሕይወታቸውእግዚአብሔርንመምሰልምይጨምራል።

ጴጥሮስ ሲሞት፤ በኢየሱስ መለኮታዊ ተፈጥሮ ውስጥ ተካፋይ መሆን ከሥነ ምግባር ብልሹነታችንእና በሕይወት ስንኖርም የሥነ ምግባር እድገት ይኖረን ዘንድ እንደሚያድነን ያውቃል።ነገር ግን የጴጥሮስ ተስፋ ከዚህ ህይወት የዘለለ ነው፡፡ በመለኮታዊ ተሳትፎ ማለት በጊዜ ሂደት ፃድቅ እየሆኑ መምጣት ማለት አይደለም፤ ይልቅ በመለኮታዊ አለመሞትም መሳተፍ ማለት ጭምር ነው፡፡ ኢየሱስ በገዛ ራሱ ፈቃድ ከእኛ ጋር ተቆጠረ፤ ይሁን እንጂ በዘላለም መንግስት ውስጥ ደግሞ ለእኛ አቀባበል ያደርግልናል፡፡ ጴጥሮስ በደብዳቤው መጨረሻ ላይ ፅድቅ ለዘላለም በሚኖርበት ስፍራ ኢየሱስ አቀባበል እንደሚያደርግልን አዲስ እውነታን ጨምሮ ይነግረናል፡፡

ጴጥሮስ በዕድሜው መጨረሻ ላይ በስብከቱ ሲነግረን ፃድቁ አዳኛችን የራሱን የፅድቅ ባህሪ ስላካፈለን ወደ ዘላለሙ ፅድቅ የሚመራንን የፅድቅን ኑሮ መኖር እንደምንችል መልዕክት ያኖርልናል፡፡አሁን በዓለም ሁሉ ላይ የሚስተዋለው የስነ-ምግባር ብልሹነት እንደሚጠፋና የስነ-ምግባር ዕድገታችንም ለዘለዓለም የስነ-ምግባር ፍፅምና መንገድ ይሰጠናል፡፡

የስነ-ምግባር ብልሹነት ለገዛው የዘላለም እውነታው ሲዖል ይባላል፡፡ ጴጥሮስ ግን ሲናገር ኢየሱስን የሚያውቁ አሁንም ለዘለዓለምም ፅድቅን ይለማመዳሉ ይለናል፡፡ ስለዚህበመጨረሻውየብዕርንግግሩያመሰገነውንጻድቅ የሆነውን ጴጥሮስእመኑት። ወደክብሩናወደ ታላቅነቱሁሉእንደሚጠራችሁ ደግሞኢየሱስን እመኑት። ኢየሱስ ካለህበት የስነ-ምግባር ብልሹነት ወደ ዘላለማዊ ፍፅምና እንደሚስብህ እመነው፡፡

ፃድቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ አዳኛችን ሆኖ የፅድቅ ባህሪውን የሚያካፍለንን በዚህም ለዘለዓለም ክብሩን መለማመድ እንድንችል ያስቻለንን ኢየሱስን ማየት ይሁንልህ፡፡

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

2ኛ ጴጥሮስ

2ኛ የጴጥሮስ መጽሐፍ በዕምነት እንድታድግ፣ የሀሰት ትምህርቶችን እንድትቋቋም እና የኢየሱስን ዳግም ምፅዓት በጉጉት ስትጠባበቅ ደግሞ እግዚአብሔርን የመምሰል ህይወት እንድትኖር በዚህም እግዚአብሔርን ለመምሰል ላለው ኑሮ ሁሉን እንደሰጠህ እንድታውቅ ያነቃቃሃል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/