2ኛ ጴጥሮስናሙና

2ኛ ጴጥሮስ

ቀን {{ቀን}} ከ3

ጴጥሮስሁለተኛውንደብዳቤሲያጠናቅቅፍላጎቱ የነበረው ህዝቡኢየሱስበቶሎእንደሚመጣእንዲያስታውሱእንዲሁምበምድርሲኖሩእግዚአብሔራዊኑሮንመኖርእንዲገባቸውበማበረታታትነው፡፡ነገርግንይህማስታወሻበሐሰተኛአስተማሪዎችቡድንመካከልያልተለመደነው፡፡እነርሱ ኢየሱስ ተመልሶ ስለመምጣቱ ጥርጥር ውስጥ ያሉና ፍላጎታቸውን ስለመግታት ጉዳይ የማያሳምናቸው ናቸው፡፡

የሀሰት አስተማሪዎቹ ሁለት መከራከሪያ አላቸው፡፡ የመጀመሪያው ዓለም ከተፈጠረችጀምሮእግዚአብሔርበሰውልጅታሪክውስጥጣልቃገብቶክፋት ላይመፍረድአልቻለም፡፡ ስለ ስነ-ምግባር ክፋታችን የተተነበየው ያ የፍርድ ቀን በፍፁም ስለማይመጣ እንደፈለግን ብንኖር ለእግዚአብሔር ግዱም አይደለም፡፡ ነገር ግን ጴጥሮስ እውነትን እየካዱ ነው ይላል፡፡

እግዚአብሔር በሰው ታሪክ ውስጥ ጣልቃ ገብቷል፡፡ እግዚአብሔርምድርን በቀላል ቃል ከሚያስፈራው የጥፋትውሃአወጥቷታል፡፡ እንዲሁምበሌላአባባል ደግሞ ለሰዎች ብልሹ ምግባር ምላሻ ምድርን በጎርፍ እንድትሰጥም አደረጋት፡፡ በኋላእንደገናየሚያነሳውነጥብ እኚህ የሀሰት አስተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በመቀራረብ በሰዎች ታሪክ ውስጥ ይሳተፋል እንዲሁም ቃሉም በዓለም ላይ ለመፍረድ እየጠበቀ ነው፡፡

የሀሰት አስተማሪዎች ሁለተኛ መከራከሪያ ደግሞ እግዚአብሔር አርፍዷል የሚል ነው፡፡ ኢየሱስ በቅርቡ እንደሚመጣ ተናግሯል ነገር ግን አልመጣም፡፡ ጴጥሮስም የሚያተኩረው የማይሞተው እግዚአብሔር በእኛ የጊዜ ሰሌዳ እንደማይሰራ ነው፡፡ ለእርሱ “በቅርብ” ማለት ለእኛ በቅርብ ከምንለው በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ እንደውም እግዚአብሔር ያረፈደ ሳይሆን ታጋሽ ነው፡፡ እግዚአብሔር ማንም እንዲሞትና የእርሱ ፍርድ እንዲሆነበት አይፈልግም፡፡ የእግዚአብሔር ረጅሙ መዘግየት ለእኛ ግድ እንደሌለው የሚያረጋግጥ ሳይሆን ለንስሃ ረጅም ጊዜ ለሚወስድበት ሰው መሃሪነቱን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መዘግየት ትዕግስቱ ነው፡፡ እንዲሁም ስለእግዚአብሔር ጊዜ ስለሚጠራጠሩ ሰዎች የእግዚአብሔር ትዕግስት ብቸኛው የደህንነታችን ተስፋ ነው፡፡

ኢየሱስ በቅርቡ እንደሚመጣ እናውቃለን፡፡ በዚያች ቀን ክፋትና ኃጢአት ይቀልጣሉ ኢንዲሁም ይጠፋሉ፡፡ በቅርቡ የሚቀረው ነገር ቢኖር መልካም የሆነውና ልክ የሆነው ብቻ ይሆናል፡፡ በቅርቡ እንደ ሰማያዊው መልካምነት የምንኖርበት የግድ ይሆናል፡፡ መኖር የሚገባን ለዘላለም እንዲኖር በተደነገገው በፍትህና በስነ-ምግባር ጨዋነት ነው፡፡ ሊመጣ ያለውን የኢየሱስንፍርድወይምየስነ-ምግባርትእዛዛቱንግልጽነትእንድንጠራጠርከሚያደርጉንአስተማሪዎችመጠንቀቅአለብን፡፡ እግዚአብሔር እንዴት እንደምንኖርም ጭምር ይገደዋል፡፡ እንዲሁም ኢየሱስበቅርቡእንደሚመጣለሚያውቁሰዎች የተስፋእንጂየፍርድቀንእንደማይሆንእናውቃለን፡፡

እግዚአብሔር ሊፈርድ ብቻ ሳይሆን አዲሱን የፅድቅ ዓለም ለመመስረት፣ የስነ-ምግባር ፍፅምናን ሊያደርግና ሰላምን ሊያሰፍን ይመጣል፡፡ እግዚአብሔር በትዕግሥት እየጠበቀ ያለው ግድየለሽ ስለሆነ ሳይሆን ሁሉም ሰው ንስሐ እንዲገባ ስለሚፈልግ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉም ሰው የሌሎች የእርኩሰት ክፋትና ጉዳት ወደማይኖርበት ወደ አዲሱ ዓለም እንዲገቡ ይፈልጋል፡፡ የኃጢአትን ባርነት የሚለማመዱትን ወደራሱ የሚጠራቸው ሁሉ ንስሐ እንዲገቡና አዲስ በተሠራው ዓለም ውስጥ ነፃነትን ያገኙ ዘንድ እግዚአብሔር “በቅርቡ” ይመጣል፡፡

እግዚአብሔር በሆነ ጊዜ ላይ ፍርድን አድርጓል እንዲሁም አዲስ ፍርድን ደግሞ በቅርቡ ያደርጋል፡፡ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ዝግ ማለት እንደ ግድየለሽነት አትቁጠሩት፤ የእግዚአብሔርን ትዕግስት እንደ ደኅንነት ቁጠረው፡፡ የእግዚአብሔርን የአሁን መዘግየት ሰዎችን ሁሉ እየጋበዘ እንዳለ ቁጠረው፡፡ በፀጋ፣ በኃይል፣ በመልካምነትና በውበት የምትገለጥ የዘላለም መንግስት አለች፡፡ ሁላችንም በሌሎች ላይ ከምንሰራው አመፅና ክፋት ነፃ የምንወጣበት ቀን ይመጣል፡፡ ያቺንም ቀን በጉጉት ለሚጠባበቁ ሁሉ በቅርቡ ይሆናል፡፡

ምድርን የሰራትንና ፍርድንም የሚፈርደውን እግዚአብሔርን ታይ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ዓይኖችህን ያብራልህ፡፡ በክፉ ላይ ሊፈርድና ለሰዎች ሁሉ አዲሲቷን የፅድቅ ምድር ሊመሰርት የሚመጣውን ኢየሱስን ማየት ይሁንልህ፡፡

ቀን 2

ስለዚህ እቅድ

2ኛ ጴጥሮስ

2ኛ የጴጥሮስ መጽሐፍ በዕምነት እንድታድግ፣ የሀሰት ትምህርቶችን እንድትቋቋም እና የኢየሱስን ዳግም ምፅዓት በጉጉት ስትጠባበቅ ደግሞ እግዚአብሔርን የመምሰል ህይወት እንድትኖር በዚህም እግዚአብሔርን ለመምሰል ላለው ኑሮ ሁሉን እንደሰጠህ እንድታውቅ ያነቃቃሃል፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/