ረሃብናሙና
ረሃብ ዳዊታዊ ዘረመል ነው
ምናልባት በመልካምም ይሁን በክፉ በተወሰነ መልኩ የወላጆቻችንን ፈለግ እንከተላለን፡፡ ልጆች ካሉህ እንዴት አንተን እንደሚከታተሉ አስተውለህ ይሆናል፡፡ አንዳንድ የወረስካቸው ወይም ያሳለፍካቸው ነገሮች ከአከባቢህ የምትማረው ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ በተፈጥሮ ይኸውም ከዘረመል ሊሆን ይችላል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ዳዊት የእግዚአብሔር የልብ ሰው መሆኑ ተገልጿል፡፡ ያ ማለት የእግዚአብሔርን ፈለግ ተከትሏል ማለት ነው፡፡ ዳዊት እግዚአብሔርን በሚያከብርና የእግዚአብሔርን ባህርይ በሚመስል ሁኔታ ያስባል፣ ይሰማዋል እንዲሁም ይተገብረዋል፡፡ ለእኛም ዳዊታዊ ዘረመልን ማጎልበት ይቻላል፤ ይኸውም እግዚአብሔርን የሚራቡ ህዝቦች መሆን፣ ራሳችንንም ከእርሱ ጋርና ከመንገዱ ጋር በማጣጣም መከተል ያስፈልገናል፡፡
እግዚአብሄርን መራብ ማለት ያለማቋረጥ የእግዚአብሄርን የልቡን ሃሳብ መጠማትና መፈለግ ማለት ነው፡፡ ዳዊት ይህን የእግዚአብሔር ረሃብን ሲገልፅ ዋላወደውኃጅረትእንደሚናፍቅእንዲሁ ልቡ እግዚአብሔርን እንደሚናፍቅ ነው፡፡ ምናልባት ለእግዚአብሔር መገኘት ይህን መሰል ተስፋ የመቁረጥ ወቅቶች ገጥሞህ ይሆናል፡፡ በሌሎች ጊዜያቶች ደግሞ ነፍስህ ከእግዚአብሄር ይልቅ ሌላ ነገር ስትጠማ ታገኛትም ይሆናል፡፡ ወይም ደግሞ የዳዊትን የማያቋርጥ፣ የሚጋባ እግዚአብሄርን መራብ፤ በእርሱ መገኘት ውስጥ በተነቃቃ ህይወት እንድትኖር ማለቂያ በሌለው ደስታ ፀንተህ እንድትኖር ትፈቅድም ይሆናል፡፡ ልብ በሉ ይህንን አይነት ስሜት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ጊዜአችሁን አሳልፉ እንዲሁም ከልማዶቻቸው፣ ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ነገሮች፣ ወይም የውሳኔ አሰጣጥ ዘዴዎቻቸውንተማሩ፡፡
የዳዊት ንግግር በመዝሙር 63 ላይ እንዴት እግዚአብሔርን እንደሚናፍቅና ያለ እግዚአብሔር የሆነ ህይወት ሁሉ ባዶና ከንቱ የመሆኑን መረዳት በግልፅ ተብራርቶ እናገኘዋለን፡፡ ይህ የመዝሙር ክፍል የሚያሳየው እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ የመፈለግን ጥቅም የሆነውን ኃይሉንና ክብሩን የመለማመድ ዕድል ይኸውም እርሱን ወደ መምሰል የሚለውጠን ነው፡፡ ጠቢቡ ሲናገር እግዚብሔርን በአጋጣሚ ሳይሆን ያለማቋረጥ ፈልገን፣ በዓላማ እና በሙሉ ልብ ስንከተለው መሆኑን ያመለክታል፡፡ የሰው ልጅ በኃጢአት ሲወድቅ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ህብረት ተቋርጧል፡፡ ልባችን በኃጢአት ምክንያት ደንድኖ እንዲሁም ለእግዚአብሔርና ለሌሎች ፍቅር ግትሮች ሆነናል፡፡ ምንም እንኳን ርኩስና አመጸኞች የነበርን ብንሆንምእግዚአብሔር ግን በሚዋጀው ፍቅሩ ተከታተለን። ልክ እግዚአብሔር በአስደናቂ ፍቅሩ እኛን እንደሚከታተለን ሁሉ እኛም በዓላማ እንከተለው ዘንድ እንጀምር፡፡ ከሁሉ ነገር በላይ እርሱን መፈለግ መጀመር አለብን፡፡ በመጀመሪያ እርሱን መፈለግና የነቃ ጊዜያችንን በሙሉ ከእርሱ ጋር በእውነተኛ ህብረት ማሳለፍ አለብን፡፡ እርሱን በሀሳባችን እንድንሸከመው የሚረዳን የእርሱ ሕያው ንቃተ ህሊና ነው።
ኢየሱስን እንደ ህይወትህ ጌታና ታዳጊ ፍፁም ያልተቀበልህ ከሆነ እባክህ ዛሬ አድርገው፡፡ ማንነትህን በፍቅሩ እብዲለውጠው ፍቀድለት፡፡ እግዚአብሔርን በፍፁም ልብህ መፈለግ ማለት እርሱን መፈለግ ማለት እንደሆነ ልብ በል፡፡ እንዲሁም እርሱን መፈለግ ማለት ደግሞ እርሱን መምሰልና የክብሩን ሙላት መለማመድ ማለት እንደሆነ ማወቅ ይሁንልህ፡፡
ስለዚህ እቅድ
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ በህይወታችን እግዚአብሔርን ለማወቅና እርሱ እንዲታወቅ ማድረጋችን እኛን ወደ እርሱ ዓላማ እንዴት እንደሚገፋን ይዳስሳል፡፡ ዳዊትን እግዚአብሔር እንደ ልቤ እንዲለው ያደረገው ምን እንደሆነ እወቅና አንተስ እንዴት በሙሉ ትኩረትህ በእግዚአብሔር ፍቅር መኖር እንደምትችል እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ባለህ ህብረት በመደሰትና ፍላጎቶችህን እንደሚፈፅም ስለማመንም ጭምር፡፡ ይህ ዕቅድ የበለፀገው በዩቨርዥን ነበር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Lawrence Oyor ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.youtube.com/lawrenceoyor