ረሃብናሙና
![ረሃብ](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans%2F51975%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
ረሃብ ለሌላ ብርታት
የተለያዩ ሰዎች በቀን ውስጥ በተለያየ ጊዜ ይራባሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በቀን ሦስት ጊዜ ይመገባሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በመሃል መክሰስ ነገር ይጨምራል፡፡ ረሃብ የሰው ዘር የየዕለት ተግባር ነው፡፡ ሁላችንም መብላት እንፈልጋለን፡፡ እውነታውም የስጋው ረሃባችን የመንፈሳዊውን ጥልቅ እውነት ያንፀባርቃል፤ እኛ እግዚአብሔርን እንድንራብ ተደርገን ተፈጥረናል፡፡
ክርስትና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚብሔር ጋር ያለን ጥብቅ ግንኙነት ነው፤ ሰለዚህ በማያቋርጥ፣ በሚጨምርና በሚያድግ ረሃብ እርሱን የማወቅና በህልውናው ውስጥ የመኖር ጉዳይ ነው፡፡ ኢየሱስ ሲናገር ፅድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁኃን ናቸው ይሞላሉና ብሏል፡፡ ምናልባት ሁላችሁም የየራሳችሁን የመንፈሳዊ ረሃብ ጥግ በእጅጉ ትገነዘቡ ይሆናል፡፡ ምናልባትም ደግሞ በእግዚአብሔር ፅድቅ መሞላት የሚገባቸው የህይወት ክፍሎችም ይኖራሉ፡፡
ኢየሱስ ወደዚህ ምድር ሲመጣ ሰዎች ወደ ቀደመውና ወደ እውነተኛው ወደ እግዚአብሔር ህብረት እንዲመለሱ አመልክቷል፡፡ እግዚአብሔር ከጅምሩ እርሱንና መንግስቱን የሚራቡ ሌላው ሁሉ ግን የሚቀልባቸውን ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ኢየሱስ ምግቡ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ እንደሆነ ለወዳጆቹ በነገራቸው ጊዜ እንዲሁም የተጠማ ሁሉ ከሕይወት ውሃ ወንዞች በነፃነት ለመጠጣት ወደ እርሱ ሊመጣ እንደሚችል ይህንን እውነታ ምሳሌ አድርጎ አሳይቷል።
የእግዚአብሔር ረሃብ ይኸውም ድንቅ የሆነው እርሱን የማወቅ መሻት በየዘመናቱ የእግዚአብሔርን ህዝብ የሚያመሳስላቸው መለያ ነው፡፡ እርሱን ማወቅ ለኑሯችን ወደ እርሱ ዓላማ የሚገፋን ነው፡፡ እርሱን ማወቃችን ማለት በመላው አለም በመለኮታዊ ኃይል እየገሰገሰ ላለው የመንግስቱ አካል የሚያደርገን ነው።
የመጀመሪያዎቹ የኢየሱስ ተከታዮች የምድር ህይወት ፍፁም ለእግዚአብሔር በመሰጠት ካልኖሩ በቀር ትርጉም የለሽ መሆኑን በሚገባ ተረድተውት ነበር፡፡ ጳውሎስ ሲፅፍ የክርስቶስ ፍቅር ለሞተልን ለእርሱ እንጂ ለራሳችን እንዳንኖር ያስገድደናል ይላል፡፡ ከእግዚአብሔር ረሃብ ውጪ ያለ ሕይወት በራስና ጠፊ በሆነው በዚህ ዓለም እውነታ ላይ ሲዳክር ይታያል፡፡ ይህን መሰል ሕይወት መንግሥቱን በምድር ላይ ለመመሥረት ለሚያስችለን ከእግዚአብሔር ጋር ላለን አስደናቂ ኅብረት ውስጥ ሊያሳትፈን አያስችልም።
እግዚአብሔርን እየተራብን በሄድን ቁጥር እርሱን ለማወቅ መጨረሻ እንደሌለው እየተረዳን እንመጣለን፡፡ እስቲ የአንተን የረሃብ ደረጃ ለማጤን ጊዜ ውሰድ፡፡ እግዚአብሔር እርሱን የማወቅ መሻትን፣ እርሱንም የምታሳውቅበትን እንዲሁም ለህይወትህ ወደ ዕቅዱና ወደ ዓላማው እንድትገባ ያብዛልህ፡፡ ከዚህች ዓለም ምንም ሊያረካ የሚችል ነገር እንደሌለ ታስተውል ዘንድ እግዚአብሔር ማስተዋልን ይጨምርልህ፡፡ ለኢየሱስ ብቻ ትኖር ዘንድ ያጀግንህ፡፡
ስለዚህ እቅድ
![ረሃብ](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2Fhttps%3A%2F%2Fs3.amazonaws.com%2Fyvplans%2F51975%2F1280x720.jpg&w=3840&q=75)
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ በህይወታችን እግዚአብሔርን ለማወቅና እርሱ እንዲታወቅ ማድረጋችን እኛን ወደ እርሱ ዓላማ እንዴት እንደሚገፋን ይዳስሳል፡፡ ዳዊትን እግዚአብሔር እንደ ልቤ እንዲለው ያደረገው ምን እንደሆነ እወቅና አንተስ እንዴት በሙሉ ትኩረትህ በእግዚአብሔር ፍቅር መኖር እንደምትችል እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ባለህ ህብረት በመደሰትና ፍላጎቶችህን እንደሚፈፅም ስለማመንም ጭምር፡፡ ይህ ዕቅድ የበለፀገው በዩቨርዥን ነበር፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Lawrence Oyor ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.youtube.com/lawrenceoyor