ረሃብናሙና

ረሃብ

ቀን {{ቀን}} ከ4

በወደቀች ዓለም ያለ ረሃብ

ምናልባት ሎተሪ ቢወጣልኝ ወይም እጅግ በርካታ መጠን ያለው ገንዘብ ብወርስ ብለህ ትመኝ ይሆናል፡፡ ያን ካሽ ገንዘብ ብታገኝ ደግሞ ምን ልትሰራበት እንደምትችል ወስነህም ይሆናል፡፡ በርግጥ ማንኛውም በጎ ስጦታ ፍፁምም በረከት ከእግዚአብሔር ዘንድ በመሆኑ የሁሉ ነገር አቅራቢያችን እርሱ ነው፡፡ እኛ ግን የተጠራነው ከቁሳዊ ሃብትና ከዓለማዊ እርካታ እጅግ ለሚበልጥ ነገር ነው፡፡ የሚወድህ የሰማዩ አባትህ ወጥመድ የሆነውን ይህን ዓለም እንዳንራብ እንድናስተውልና ከሁሉ የሚቀድመውንና ዋና የሆነውን ኢየሱስን በመራብ ከመነገር የሚያልፈውን ሰላምና ደስታን እንድንለማመድ ይመክረናል፡፡

ኢየሱስ አንዳንድ ሰዎች በከንፈራቸው ያከብሩት እንደነበርና ልባቸው ግን ከእርሱ የራቀ መሆኑን አስተውሏል፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ይህ በእኛ ትውልድ መካከል ባለችው ቤተ-ክርስቲያን ያለ እውነት ነው፤ ይህም በአብዛኛው በዓለማዊ ሀሳብ የተዋጠ ነው፡፡ መቼም ኢየሱስን ከመራብ ይልቅ ቁሳዊ ሃብትና ምቾትን የሚራብ ክርስቲያን ማግኘት የተለመደ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን እግዚአብሔርን በቅድሚያ የምከተለው ለቁሳዊ ማግኛ ነው (በሰበብና በምክንያት) ወይስ ከእርሱ ጋር ህብረት የምናደርገው ልባችን እርሱ ራሱን በይበልጥ ናፍቆ ነው ብለን መጠየቅ አለብን፡፡

ኢየሱስ ለተከታዮቹ ስለማያምኑ ሰዎች (በእርሱ ዘመን ስለነበሩት አህዛብ) ሲያብራራ ከመጠን በላይ ገና ስለሚበሉት ነገር፣ ስለሚጠጡት ነገርና ስለሚለብሱት ነገር ይጨነቃሉ በማለት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች እነዚህን ነገሮች አንዴ ከሰጪው እግዚአብሔር እጅ ከተቀበሉ በኋላ መንፈሳዊ ፍለጋቸው ሲደበዝዝ ይታያል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችሁ ወይም በሰፊው ማህበረሰብ ዘንድ በቅንነት እግዚአብሔርን የመራብ ጉዳይ በሀዘንና በስግብግብነት ተተክቶ ትመለከት ይሆናል፡፡ ምናልባት ደግሞ አንተና የአንተ አማኝ ባልንጀሮች ፍፁም ቁሳዊ ያልሆነ የህይወት ስርዓትን ለማሳየት እንደተጠራችሁ እያደገ የመጣ ግንዛቤ ይኖራችሁም ይሆናል፡፡

የኢየሱስ መልዕክት ዛሬ ዛሬ በእኛ ዘንድ ባህል እንደሆነው ቁሳዊ ነገርን የማግበስበስ ምኞት ፈፅሞ አያበረታታም ነበር፡፡ ስለዚህም እርሱን መከተል ከዓለማዊ ጥቅም ጋር ልናስተያየው አንደፍርም። በምድር ላይ ምንም ነገር እንደ ከበረው እግዚአብሔር አስፈላጊ የምንለው የለም፡፡ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች አስቀድመን እርሱን ለመፈለግ ከምንም በላይ ደግሞ እርሱን በማወቅና እርሱን ከማሳወቅ ደስታ ውጭ ምንም አይነት ሽልማቶችን ሳንጠብቅ ለማቅረብ እንግባ።

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ረሃብ

ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ በህይወታችን እግዚአብሔርን ለማወቅና እርሱ እንዲታወቅ ማድረጋችን እኛን ወደ እርሱ ዓላማ እንዴት እንደሚገፋን ይዳስሳል፡፡ ዳዊትን እግዚአብሔር እንደ ልቤ እንዲለው ያደረገው ምን እንደሆነ እወቅና አንተስ እንዴት በሙሉ ትኩረትህ በእግዚአብሔር ፍቅር መኖር እንደምትችል እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ባለህ ህብረት በመደሰትና ፍላጎቶችህን እንደሚፈፅም ስለማመንም ጭምር፡፡ ይህ ዕቅድ የበለፀገው በዩቨርዥን ነበር፡፡

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Lawrence Oyor ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://www.youtube.com/lawrenceoyor