መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት ናሙና
ኢየሱስ በመድር ላይ ይኖር በነበረበት ዘመን ስለስማይ ቤት ለደቀመዛሙርት ይነግራቸው ነበር የአባቴ ቤት እያለም ይጠራው ነበር፡፡ በዚያ ብዙ ሥፍራ አለ እሱም በጣ ትልቅ ሰፊ ነው፡ የሰማይ ቤት በምድር ላይ ካሉት ፈጽሞ የተለየና እጅግ በጣም የሚበልጥ ስፍራ ነው፡፡
ኢየሱ እንዲህ አለ ሥፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ ብሄድና ሥፍራ ባዘጋላችሁ ተመልሼ እመጣና ወደ እወሰዳችኋለሁ፡፡ ኢየሱስም ከሞት ከተነሣ በኋላ ወደ ሠማይ አረገ ደቀመዛሙርቱም እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከፊታቸው ጋረደው፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያኖች ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃል የገባልን በማታወስ ደግመኛ እንደሚመጣ እንደሚገናኙት ያናሉ፡፡ ኢየሱም በድንገት በቶሎ እንደሚመለስ ተናግሯል፡፡ ነገር ግን እሱ ከመምጣቱ በፊት የሚሞቱ ክርቲያች ምን ይሆናሉ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በቀጥታ ከሱ ጋር ይሆናሉ፡፡ ከአካል መለየት ማለት ከክርስቶስ ጋር አብሮ መሆን ማለት ነው፡
የዮሐንስ ራዕይ የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው፡፡ መንግሥተ ሰማያት ምን ያህል ድንቅ እንደሆነች ይናገራል፡፡ በጣም የሚደንቀው ነገር ሰማይ የእግዚአብሔር መኖሪያ መሆኑ ነው እግዚአብሔር በሁሉም ሥራ የሚገኝ ቢሆንም ሰማይ ግን ዙፋኑ ነው፡፡
መላዕክትና በሰማይ የሚገኙ ኃይለት ሁሉ በሰማይ ያለውን እግዚአብሔርን ያመልኩታል፡፡ ሁሉም የሞቱት ክርቲያኖች ከእግዚአብሔር ጋር አሁን በሰማይ ይገኛሉ፡፡ ለእግዚአብር የተለየ የምስጋና መዝሙር እየዘመሩለት ነው፡፡ ከሚዘምሩት መዝሙሮች ውስጥ አንድ ቃል አለ ይኸውም በደምህም ለእግዚአብሐር ከነገደ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከህዝብም ሁሉ፤ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው በምድርም ላይ ይነግሣሉ ይላል፡፡ ራይ 5፡9
የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደሚነግረን መንግሥተ ሰማያት ማለት “አዲስቲቱ እየሩሌም” ማለት ነው፡፡ እጅግ በጣም በጣም ትልቅና በጣም ረጅም ግድግዳ ያለው ከተማ ነው፡፡ ግድግዳውም የከበረ ድንጋይ እንደእምነበረድ የጠራ ነው፡፡ የወለሉም መሠረት ከከበረ ወርቅና እንቁ፣ ማዕድናት የተሠራ ነው በልዩ ልዩ ብርሃናት ያሸበረቀ ነው፡፡ እያንዳንዱ በር ከከበረ እንቁ የተሠራ ነው፡፡
እነዚህ ከእንቁ የተሠሩ በሮች ፈጽሞ አይዘጉም፡፡ በውስጡ ገብተን ዙሪያውን ስናየው--- እንዴት ይደንቃል መሠላችሁ፡፡ ከተማዋም የተሠራችው ከወርቅ ሆኖ እንደሚያበራ ብርጭቆ ናት መንገዶቿም ሁሉ ከወርቅ የተሠሩ ናቸው፡፡
ከእግዚአብሔር ዙፋን ሥር የህይወት ውሃ ምንጭ ያለማቋረጥ ይፈልቃል፡፡ በሌላኛው በዙፋኑ በኩል በኤደን ነገት ውስጥ የነበረችው ሌላይቱ የህይወት ዛፍ ትገኛለች፡፡ ይህች ዛፍ እጅግ በጣም የተለየች ናት ዛፏም 12 ፍሬዎችን ይዛለች በየወሩም የተለያየ ፍሬ ታፈራለች፡፡ ቅጠሎቿም ለህዝብ መድኃኒት ወይም መፈወሻ ይሆናል፡፡
መንግሥተ ሰማያት የፀሐይ ብርሃን ወይም ጨረቃ አያስፈልጋትም፡፡ የእግዚአብር ክብር እራሱ ብርሃኗ ይሆናል፡፡ በዚያም ሌሊትም ሆነ ቀን የለም፡፡
በሰማያ የሚኖሩት እንሰሳት ራሳቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ ሁሉም ቤተሰብ እና የሰው ወዳጅ ናቸው፡፡ በጎችና ተኩላዎች በአንድነት ሣር ይበላሉ፡፡ የሚያስፈራው አንበሳ እኳን እንደበሬ ሣር ይበላል፡፡ እግዚአብሔርም እንደህ አለ በተቀደሰው ተራራም ላይ ሳይጎዳዱም ሆነ ሳይበላሉ ተስማምተው በአንድነት ይኖራሉ፡፡
ዙሪያችንን ስንመለከት ከመንግሥተ ሰማያት የሚያስቀሩን ነገሮች እንዳሉ እናሰባለን፡፡ የቁጣ ቃሎች ፈጽሞ አይሰሙባትም፤ ማንም እርስ በርስ አይጣላም በዚያ ራስ ወዳድነት አይኖርም በበሮች ላይ ቁልፎች ፈጽሞ አይኖሩባቸውም፡፡ ነፍስ ገዳዮች ሌቦች፣ ሐሰተኞችና አመፀኞች በዚያ ፈጽመው አይኖሩም ምንም አይነት ኃጢአት በዚያ የለም አይገኝም፡፡
በመንግሥተ ሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር በዚያ እምባ የለም፡፡ አንዳንዴ የእግዚአአብሔር ሰዎች እዚህ ስላለው ስለምድር ኑሮ ሊያለቅሱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በመንግሥተ ሰማያት እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከአይናቸው ላይ ያብሣል፡፡
በሠማይ በዚያ ሞት የለም የእግዚአብሔር ሠዎች በሙሉ ለዘልዓለም ከእግዚአብሔር ጋር ይኖራሉ በዚያ ለቅሶ፣ ሐዘን፣ ህመም የለም፡፡ በዚያ ህመም ልዩነት እና የቀብር ሥነ ሥርት የለም፡፡ በሠማይ የሚኖር ሁሉ ለዘላለም ደስተኛ ነው፡፡
መንግስተ ሰማይ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛቸው ለአመኑ እና እንደ ጌታቸው ለተቀበሉ ለወንዶችና ለሴቶች (ለአዋቂዎችም) ናትና። በመንግሥተ ሠማያት አንድ መጽሐፍ አለ እሱም የበጉ የህይወት መጽሐፍ ይባል፡፡ ይህም በሠዎች ሥሞች የተሞላ ነው፡፡ ሰሙ በዚያ የህይወት መዝገብ ላይ የተጻፈ የምታውቁት ሰው አለ ሁሉም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምነው የሞቱት ሁሉ በዚያ የህይወት መዝገበ ውስጥ ይኖራሉ፡፡
የመጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻ ስለሠማይ የተጻፈው ቃል በጣም ድንቅ እና ጋባዥ ነው፡፡ “መንፈሱና ሙሽሪይቱ ና ይላሉ! የሚሰሙ ሁሉ ና ይላሉ፡፡ የተጠማ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣና የህይወትን ውሃ በነጸ ይጠጣ፡፡”
መጨረሻ
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ ሁሉ እንዴት ጀመረ? የመጣነው ከየት ነው? በዓለም ላይ ይህን ያህል መከራ የበዛው ለምንድን ነው? ተስፋ አለ? ከሞት በኋላ ሕይወት አለ? የዚህን እውነተኛ የዓለም ታሪክ ሲያነቡ መልሱን ያግኙ.
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ መጽሐፍ ቅዱስን ለህፃናት፣ Inc. ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡-https://www.bibleforchildren.org/languages/amharic/stories.php