የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት ናሙና

መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት

ቀን {{ቀን}} ከ7

ከብዙ ዓመታት በፊት እግዚአብሔር ድንግል ወደ ሆነችው ማሪያም ወደምትባል አይሁዳዊት ሴት መልአኩ ገብርኤልን ላከው፡፡ እንዲህ አላት “ድንግል ትፀንሻለሽ ወንድልጅም ትወልጃለሽ ሰሙንም እየሱስ ብለሽ ትጠሪዋለሽ፣ እሱም የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል ለዘለዓለምም ይነግሣል፡፡”

“ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” በሚል ይህች ሴት ጠየቀችው፡፡ “ከማንም ሰው ጋር አልነበርኩም አላቸው” መልአኩም ህፃኑ የመጣው ከእግዚአብር ዘንድ ነው፡፡ ከሰው አባት የተገኘ ልጅ አይደለም አላት፡፡

መልአኩም ለማሪያም እንዲህ አላት ዘመድሽ ኤልሳቤጥም ፀንሳለች፡፡ ይህ ተአምር ነው ብሎ ማርያምም ዘመዷን ኤልሣቤጥን ልትጎበኛት ሄደች፡፡ ሁለቱም በጋራ እግዚአብሔርን አመሠገኑ፡፡

ማሪያም ዮሴፍ ለሚባል ሰው ታጭታ ነበር፡፡ ማሪያምም እንደፀነሰች በሰማ ጊዜ ዮሴፍም በጣም አዘነ፡፡ ከሌላ ሰው ልታረግዝ እንደምትችልም አሠበ፡፡

መልአኩም በህልም ተገልጦለት ዮሴፍ ሆይ ይህ ህፃን የተፀነሰው በሰው ፈቃድ ሣይሆን በእግዚአብሔር ነውና ማሪያምን ለመውሰድ አትፈራ አለው፡፡ ዮሴፍም ማሪያም ይረዳት ነበር ህፃኑን እንሱስንም ይንከባከበው ነበር፡፡

ዮሴፍም እግዚአብሔርን አመነው ታዘዘውም በተጨማሪም የሃገሪቱን ህግ ይታዘዝና ለህጉም ይገዛለት ነበር ምክንያቱም አዲስ ህግ ከመውጣቱ የተነሣ ማሪያና ዮሴፍ ሃገራቸውን ለቅቀው ወደ ሌላ ሃገር ተሰደዱ ቤተልሄምም በደረሱ ጊዜ ታክስ (ግብር) ከፈሉ፡፡

ማሪያም ልጅ የመውለጃዋ ጊዜም ደረሠ ነገር ግን ዮሴፍ የምትወልድበትን ምቹ ቦታ ሊያገኝ አልቻለም ሁሉም ክፍት የሚመስሉ ቦታዎች ሁሉ ሞልተው ነበር፡:

ዮሴፍም በመጨረሻው የከብቶች በረት አገኘ በዚያም ህፃኑ እየሱስ ተወለደ፡፡ እናቱም ህፃኑን በከብቶች በረት ውስጥ አስተኛችው፡፡ ይህ ሥፍራ የእንሰሳት ማደሪያና መኖአቸው የሚቀመጥበት ሥፍራ ነው፡፡

በአቅራቢያው መንጋቸውን የሚያሠማሩ እረኞች ነበሩ የእግዚአብሔር መልአክም ወደ እነርሱ ቀርቦ ድንቅ ዜና የምሥራች ነገራቸው፡፡

ዛሬ በደዊት ከተማ አዳኝ የሆነው ክርስቶስ ኢየሱ ተወልዶላችኋል ህፃኑም በከብቶች በረት በግርግም ተኝቶ ታገኙታችሁ ብሎ ነገራቸው፡፡

ወዲያው የሚያበሩ መልአክትም ተገልጠው እግዚአብርሔን እንዲህ እያሉ ያመሰግኑት ነበር ክብር በላይ በሠማይ በታችም በምድር ለእግዚአብሔር ይሁን ሰላምና በጎ ፈቃዱ በምድር ይሁን አሉ፡፡

እረኞቹም እየሮጡ የተባለበት ሥፍራ ደረሱ ህፃኑንም ካዩት በኋላ ላገኙት ሰው ሁሉ መልአኩ ስለ ኢየሱስ (ስለህፃኑ) የነገራቸውን ሁሉ እውነት እንደሆነ መናገር ጀመሩ፡፡

ከ40 ቀናትም በኋላ ማሪያምና ዮሴፍ ህፃኑን ወደ ኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ መልሠው አመጡት ስምኦን የሚባል ሰውም አገኙ እሱም ስለህፃኑ እግዚአብሔርን አመሠገነ ሌላው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሃናንያ የሚባል ሰውም ለእግዚአብሔር ምሥጋናን አቀረበ፡፡

ሁለቱም ኢየሱስ የእግዚአብር ልጅ እንደሆነ ያውቁ ነበር፡ ሊመጣ ያለው መሲህ ነው አሉ፡፡ ዮሴፍም 2 ወፎችን መሥዋዕት አደረገ፡፡ ይህም እግዚአብሔር ከሠጣቸው ህግ ውስጥ አንድ ሰው ልጅ ሲወልድ ማቅረብ ያለበት መሥዋት ነው፡፡

ከጥቂት ጊዜያት በኋላም አንዲት ኮከብ ጠቢባንን እየመራች ህፃኑ ተወለደ ወደ ተባለበት ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰቻቸው፡፡ “የተወለደው የአይሁ ንጉሥ ወዴ አለ?” ሲሉ ጠየቁት “እሱንም ልናመልከው እንፈልጋን አሉ፡፡”

እኝህ ጠቢባን ሠዎች ያሉትን ሁሉ ንጉሡ ሄሮዲስ ሰማ፡፡ እሱም ተረበሸና እየሱን መቼ እዳገኙት ጠየቃቸው “እኔም እሱን ላመልከው እፈልጋለሁ” አላቸው፡፡ ነገር ግን ውሸቱን ነበር ሊገድለው ይፈልግ ነበር፡፡

ከህፃኑ ልጅ ጋር ወደ ሚኖሩበት ወደነ ማሪያም ቤት ኮከቧ ጠቢባንን መርታ አደረሠቻቸው ወድቀው ከሠገዱለት በኋላ ያመጡለትን የከበረ ስጦታ እጅ መንሻ ለህፃኑ ሰጡት፡፡

እግዚአብሔር ለጠቢባን በማስተዋል ወደቤታቸው እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡ ሔሮዲስም ስለ ተቆጣ ህፃኑንም ሊገድለው ወሰኖ ነበርና፡፡ በቤተልሄም የሚገኙትን ወንድ ህፃናቶች በሙሉ አስገደለ፡፡

ነገር ግን ሄሮዲስ የእግዚአብሔርን ልጅ ሊያገኘው ፈጽሞ አልቻለም፡፡ በዚህም አስጠነቀቃቸው “ዮሴፍ ማሪያምን ይዘው ወደ ግብፅ አገር ሂድ” አለው፡፡

ንጉሤ ሄሮደስም ከሞተ በኋላ ዮሴፍ ሚስቱን ማሪያምንና ኢየሱስን ከግብፅ አገር ወደ ቤተልሄም መልሶ ይዟቸው መጣ፡፡ እነሱም በገሊላ ባህር አጠገብ በምትገኝ ናዝሬት በምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡

መጨረሻ

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 3ቀን 5

ስለዚህ እቅድ

መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት

ይህ ሁሉ እንዴት ጀመረ? የመጣነው ከየት ነው? በዓለም ላይ ይህን ያህል መከራ የበዛው ለምንድን ነው? ተስፋ አለ? ከሞት በኋላ ሕይወት አለ? የዚህን እውነተኛ የዓለም ታሪክ ሲያነቡ መልሱን ያግኙ.

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ መጽሐፍ ቅዱስን ለህፃናት፣ Inc. ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡-https://www.bibleforchildren.org/languages/amharic/stories.php