የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት ናሙና

መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት

ቀን {{ቀን}} ከ7

እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ፈጠረ፡፡ እግዚአብሔር የመጀመሪያው ሰው አዳምን ሲፈጥር በኤደን ገነት ውስጥ ከሚስቱ ከሄዋን ጋር ይኖር ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በመታዘዙ ፍጹም ደስተኛ ነበሩ አንድ ቀን በህይወታቸው እስኪከስት ድረስ ከእግዚአብሔር አብሯቸው ከመሆኑ የተነሣ ነበር፡፡

“ከየትኛውም ዛፍ ፍሬ እንዳትበሉ እግዚአብሔር ተናግሯችሁ ነበር? በማለት እባቡም ሔዋንን ጠየቃት፡፡” ከሁሉም ዛፎች ፍሬ እንድንበላ ፍቅዶልናል ነገር ግን አንዲት ፍሬዋ የማይበላ ዛፍ እንዳለች ነግሮኛል፡፡ “እባቡም አትሞቱም” ብሎ መለሠላት፡፡ “እንደ እግዚአብሔርም ትሆናላችሁ” አላቸው፡፡ ሔዋንም ከዚያ ዛፍ ፍሬን ለመብላት አሠበች እባቡንም ሠማች እንዳላት ብዚያች ዛፍ ፍሬን በላች፡፡

ሔዋንም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ከተላለፈች በኋላ ባሏም አዳም ከዚያች ዛፍ ፍሬን እንዲበላ ሰጠችው እሱም በላ፡፡ አዳምም ስትሰጠው “አይሆንም የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ልንተላለፈው አይገባም” ማለት ነበረበት፡፡

አዳምና ሔዋን ኃጢአትን ከሠራ ወይም ካደረጉ በኋለ እርቃናቸውን መሆናቸውን አወቁ፡፡ ለሀፍረታቸው መሸፈኛ ይሆን ዘንድ ቅጠል ሰፈተው ሀፍረታቸውን ሽፈኑት ከቁጥቋጦው ሥር በመሸሸግም ከእግዚአብሔር ተደበቁ፡፡

ፀሐይም ባዘቀዘቀች ጊዜ እግዚአብሔርም ወደ ኤደን ገነት ውስጥ መጣ፡፡ አዳምና ሔዋን ያደረጉትን ያውቅነበርና፡፡ አዳምም በሔዋን ላይ አመካኘ ሔዋንም በእባብ አመካኘች፡፡ እግዚአብሔርም እባብን “የተረገምክሁን፡፡ ሴትቱም በወላጀዋ ጊዜ በምጥ ትውለድ” ብሎ ረገማቸው፡፡ “አዳም አንተ ኃጢአትን ከመሥራትህ የተነሣ ምድር ተረገመች እሾህንና አሜክላን ታብቅል፡፡ ጥረህ ግረህ የላብህን ወዝ ፈሬዋንም ብላ” አለው፡፡

እግዚአብሔርም አዳምና በሔዋንን ከኤደን ገነት ውስጥ አሰወጣቸው ምክንያቱም ኃጢአትን ሠርተዋልና ህይወት ሰጪ ከሆነው እግዚአብሔር ተለይተዋል፡፡

እንደ እሳት የሚንበለበሉ ሰይፎችንም እግዚአብሔር በኤደን ገነት ውስጥ አኖረ አስወጣቸውም እግዚአብሔርም ለአዳምና ለሔዋን የበግ ለምድን አለበሳቸው፡፡ እግዚአብሔር ይህንን እግዚአብሔርም ለአዳምና ለሔዋን የበግ ለምድን አለበሳቸው፡፡ እግዚአብሔርም ይህንን ለምድ ከየት አመጣው?

በጊዜው አዳምና ሔዋን ልጆችን ወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸውም ቃየል አትክልተኛ ነበር፡፡ ሁለተኛው ልጃቸውም አቤል ይባላል እሱም እረኛ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ቃየል ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ከእርሻው ሰብል ስጦታን አመጣለት፡፡ አቤልም በጣም ምርጥ ከሚላቸው በጎች መሃከል አንዱን መርጦ ለእግዚአብሔር በስጦታ መልክ አመጣለት፡፡ እግዚአብሔርም በአቤል ስጦታ በጣም ደስ ብሎት ነበር፡፡

እግዚአብሔር በቃየልና በመሥዋዕቱ ደስተኛ አልነበረም፡፡ ቃየልም በጣም ተናደደ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ አለ “ትክክለኛውን ነገር ካደረግክ ተቀባይነትን አታገኝምን?”

የቃየልም ንዴት ከውስጡ አልጣፋም ነበር፡፡ ከእርሻው በኋላ ወንድሙን አቤልን አደጋ አደረስበት ከዚያም በኋላ ገደለው፡፡

እግዚአብሔርም ቃየልን እንዲህ አለው “ወንድምህ አቤል ወዴት አለ?” “ከወዴት እንዳለ አላውቅም” ብሎ ዋሸው፡፡ “እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?” አለው፡፡ እግዚአብሔርም አቤል በመዋሸቱና እራሱን አዳኝ በማስመሰል አራሽ (ገበሬ) ሆኖ ሥጦታን በውሽት በማቅረቡ ነው፡፡

ቃየልም ከእግዚአብር ፊት ሸሽቶ ሄደ፡፡ እሱም የአዳምንና የሔዋንን ልጅ አገባ፡ ቤተሰባቸውንም አሣደጉ፡፡ በቅርቡም የቃል የልጅ ልጆችና፣ የልጅ ልጅ ልጆች ቃየልም የመሠረታትን ከተማ ሞሉትት፡

የአዳምና የሔዋን ቤተሰብ በፍጥነት አደገ፡፡ በዚያን ዘመን የነበሩ ሠዎች ዛሬ ከሚኖሩት ሠዎች ይልቅ ረጅም ዕድሜ አላቸው፡፡

ሴት ልጇ ሴት በተወለደችበት ጊዜ ሔዋን እንደህ አለች “በአቤል ምትክ እግዚአብሔርን ሴትን ሰጥቶኛል ሴትም ብዙ ልጆችን ወለደ 912 ዓመት ኖረ፡፡

በዚህ ዓለም ውስጥ በተለያዩ ትውልዶች መሃከል ዓመጽ እየበዛ መጣ፤ በመጨረሻም እግዚአብሔር የሠውን ልጆች ለማጥፋት ወሠነ፡፡ ሁሉም አውሬዎችና እንሰሳት፡፡ እግዚአብሔር ሰው በመፍጠሩ ተጸጸተ፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔርን አስደሰተ፡፡

ይህም ሰው ኖህ ይባላል፡፡ በሴት የዘር ሐረግ የመጣ ነበር ኖህም ቅዱስና ነቀፌታ የሌለበት ሰው ነበር አካሄዱንም ከከእግዚአብሔር ጋር ያደረግ ነበር፡፡ ሦስቱ ልጆቹም እግዚአብሄርን እንደታዘዙ አስተማራቸው፡፡ እንግዳና አዲስ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር ኖህን ለራሱ ለመጠቀም መረጠው፡፡

መጨረሻ

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 1ቀን 3

ስለዚህ እቅድ

መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት

ይህ ሁሉ እንዴት ጀመረ? የመጣነው ከየት ነው? በዓለም ላይ ይህን ያህል መከራ የበዛው ለምንድን ነው? ተስፋ አለ? ከሞት በኋላ ሕይወት አለ? የዚህን እውነተኛ የዓለም ታሪክ ሲያነቡ መልሱን ያግኙ.

More

ይህንን እቅድ ስላቀረበ መጽሐፍ ቅዱስን ለህፃናት፣ Inc. ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡-https://www.bibleforchildren.org/languages/amharic/stories.php