መጽሐፍ ቅዱስ ለህፃናት ናሙና
ሴትየዋም ጩኽት በሞላበት ከፍታ ሥፍራ ላይ ቆማ አይኗንም ወደ ላይ በማሻቀብ የሚያስፈራ ነገር ታይ ነበር፡፡ ልጇም ሞቷል፡፡ እናቱም ማሪያም ትባል ነበር እሷም ኢየሱስ በሚስማር ተቸንክሮ በተሰቀለበት ቦታ ነበረች፡፡
ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኢየሱስ እንዴት ይህን መልከም ህይወት በእንዳበህ ዓይነት አሳዛኝ ሁኔታ እዲጠናቀቅ ያደርጋል? እግዚአብሔር እንዴት ልጁን በሚስማር ተቸንክሮ እንዲሞት ፈቀደ? በማንነቱ ኢየሱስ ሐጢያት ሰርቶ ነበር? እግዚአብሔር ተሳሳተ?
ፈጽሞ! እግዚአብሔር አልተሳሳተም፡፡ ኢየሱስ ፈጽሞ ኃጢአትን አልሠራም፡፡ ኢየሱስ አንድ ቀን በኃጢአተኛ አመጸኛ ሠዎች አማካኘነት ለመሰቀል ሞት አልፎ እንደሚሰጥ ያውቅ ነበር፡፡ ኢየሱስ ህፃን ሆኖ እንኳን ሽማግሌው ስሞኦን ለማሪያም ኃዘን ከፊት ለፊት እንደሚጠብቃት ተናግሯታል፡፡
ኢየሱስ ከመሞቱ ከጥቂት ቀናት በፊት አንዲት ሴት መጥታ እግሩን ሽቶ ቀብታው ነበር “ገንዘቧን እያባከነች ነው” በማለት ቀደመዝሙርት አጉርምርመውበት ነበር፡፡ ኢየሱስም እሷ መልካም ሥራ ሠርታለች አለ፡፡ “ለቀብሬ እንዲሆንም አድርጋዋለች” አለ፡፡ ይህ እንዴት ዓይነት አዲስ ቃል ነው!
ከዚህም በኋላ ይሁዳ ከ12ቱ ደቀመዛሙርት አንዱ ኢየሱስን በ30 ብር አሣልፎ ለመሰጠት ከአንድ ካህን ጋር ተስማ፡፡
በአይሁውያን የቂጣ በዓል ኢየሱስ የመጨረሻውን እራት ከእነርሱ ጋር በልቶ ነበር፡፡ ለእነሱም ስለእግዚአብሔርና ስለገባው ቃል-ኪዳን የሚገርም ነገር ለሚወዱት ሁሉ ነገራቸው፡፡ ኢየሱስም ዳቦውን ቆርሶ ጽዋውንም አንስቶ ስጣቸው፡፡ ይህም የኢየሱስን የሥጋዋንና የደሙን ምሣሌ በወሰዱ ጊዜ የኃጢአትን ይቅርታ እንደሚያገኙ ለማስተወስ ነው፡፡
ኢየሱስም ለተከታዮቹ አሣልፈው እንደሚሰጡት ከነገራቸው በኋላ ሁሉም ተበታተኑ ከፊቱ ሸሹ፡፡ እኔ አልሸሽም በማለት ጴጥሮስ ተናገረ፡፡ ኢየሱስም ዶሮ ከመጨኹ በፊት 3 ጊዜ ትክደኛለህ አለው፡፡
ከዚያ ምሽት በኋላ ኢየሱስም ለመጸለይ ወደ ጌተሰማኒ የአትክልት ሥፍራ ሄደ፡፡ ከሱ ጋር የነበሩት ደቀመዛሙርትም አንቀላፉ፡፡ ኢየሱስም በሰማይ የምትኖር አባት ሆይ --- ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ በፍጹም እኔ እንዳልኩት ሣይሆን አንተ እንደወደድከው ይሁን አለ፡፡
ወዲያው ብዙ ሰዎችም ወደ አትክልቱ ሥፍራ መጡ መሪያቸውም የአስቆሮንቱ ይሁዳ ነበር፡፡ እየሱስም ምንም እላለም ነገር ግን ጴጥሮስ የአንዱን ጆሮ ቆረጠው፡፡ ወደያው ኢየሱስም የሰውየውን ጆሮ ነክቶ ወዲያው ፈወሠው፡፡ ኢየሱስም መታሠሩና በሠዎች መያዙ የእግዚአብር ፈቃድ እደሆነ ያውቅ ነበር፡፡
ኢየሱንም ከያዙት በኋላ ወደ ሊቀካህኑም ቤት ወሰዱት እዚያም የአይሁድ መሪዎች የሆኑት ኢየሱስ መሞት አለበት ይሉ ነበር፡፡ አቅራቢያው ጴጥሮስ በአንዲት ገረድ አጠገብ እሣት ይሞቅና የሚሆነውንም ሁሉ ያይ ነበር፡፡ ሦስት ጊዜ ሠዎች እንደህ ሲሉ ጠየቁት ከኢየሱስ ጋር ነበርክ? አሉት ሦስትም ጊዜ ጴጥሮስ አልነበርም ብሎ ካደ፡፡
ከዚያ በኋላ ብዙ ህዝብም መጡ የእግዚአብርን ደምፅ የሚመስል ለጴጥሮስ ሲመጣለት ኢየሱስ ብሎት የነበረውን ጴጥሮስ አስታወሰው ምርር ያለ ለቅሶ አለቀሰ፡፡
ይሁዳም ይቅርታ ጠየቀ ኢየሱስ ምንም ዓይነት ኃጢአት ወይም በደል እንዳሌለበት ያውቅ ነበር፡፡ ይሁዳም የሸጠበትን 30 ብር መልሶ አመጣው ነገር ግን ካህናት አልተቀበሉትም ነበር፡፡
ይሁዳም ገንዘቡን መሬት ላይ ወረወረው ከዚያም ወጣና ራሱን አጠፋ፡፡
ካህናቱም ኢየሱስን ጵላጦስ ፊት አቀረቡት እሱም የሮማ ገዢ ነበር፡፡ ጲላጦስም እንዲህ አለ በዚህ ሰው ላይ ምንም ዓይነት ስህተት አላገኘሁበትም፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ጨኸታቸውን በመቀጠል ሥቀለው ስቀለው አሉት፡፡
በመጨረሻም ጲላጦስ ኢየሱስ ተሰቅሎ እንዲሞት ወሠነ፡፡ ወታደሮችም በጥፊ ይመቱትና ያንገላቱት ነበር በፊቱም ምራቅ እየተፉበት ይገፉት ነበር፡፡ በጭንቅላቱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍተውበት ነበር ከዚያም እጆቹን በእንጨት መስቀል ላይ በሚሰማር በመቸንከር ሠቀሉት፡፡
ኢየሱስ ሁልጊዜ እንደዚህ ዓይነት ሞት እደሚጠብቀው ያውቅ ነበር፡፡ ሁል ጊዜም የእርሱ መሞት በእርሱ የሚያምኑት ሁሉ የኃጢአትን ይቅርታ ሊያገኙም እንደሚችሉ ያሳስብ ነበር፡፡ ሁት ወንበዴዎች በኢየሱ አጠገብ ተሠቅለው ነበር፡፡ አንዱ በኢየሱስ ስላመነ መንግሥተ ሠማያት ገባ ሌላው ግን ስላለመነ አልገባም፡፡
ከሠዓታት ሥቃና መከራ በኋላ ኢየሱስ ተፈፀመ ብሎ ሞተ፡፡ ሥራው ተከናወኗል፡፡ ጓደኞቹ የቀሩት ለብቻው ነበር፡፡
የሮማ ወታደሮች መቃሩን በማህተም በመዝጋት ይጠብቁት ነበር፡፡ ማንም ሰው ሊገባት ወይም ሊወጣ አይችልም ነበር፡፡
ይህ የታሪኩ መጨረሻ ከሆነ ምን ያህል አሣዛኝ ነው ነገር ግን እግዚአብሔር አንድ ድንቅ ነገር አድርጓል ኢየሱስ ሞቶ አልቀረም፡፡
በሳምንቱ በመጀመሪያ ቀን በማለዳ አንዳንድ የኢየሱስ ደቀመዝሙሮች ድንጋይ ተንከባሎ አዩት ወደ ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ ኢየሱስ በዚያ አልነበረም፡፡
አንዲት ሴት ቆይታ መቃብሩ አጠገብ ሆና ታለቅስ ነበር፡፡ ኢየሱስም ወደ እርሱ ቀረበ፡፡ እየሮጠችም ለሌሎች ደቀመዛሙርት የምሥራች ልትናገር ሄደች ኢየሱስም አልሞተም ኢየሱስ ከሙታን ተነስቷል አለቻቸው፡፡
ኢየሱስም ወደ ደቀመዛሙርቱ ቀርቦ በሚስማር የተቸነከሩ እኮቹን ያሣይ ነበር እውነት ነበር ኢየሱስ እንደገና ህያው ነው! ውሸታሙን ጴጥሮስንም ይቅር አለው ስለመነሣቱም ለሰዎች ሁሉ የምስራች እንዲናገሩ ለደቀመዛርት ነገራቸው፡፡
መጨረሻ
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ ሁሉ እንዴት ጀመረ? የመጣነው ከየት ነው? በዓለም ላይ ይህን ያህል መከራ የበዛው ለምንድን ነው? ተስፋ አለ? ከሞት በኋላ ሕይወት አለ? የዚህን እውነተኛ የዓለም ታሪክ ሲያነቡ መልሱን ያግኙ.
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበ መጽሐፍ ቅዱስን ለህፃናት፣ Inc. ማመስገን እንፈልጋለን። ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎን ይጎብኙ፡-https://www.bibleforchildren.org/languages/amharic/stories.php