የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

በእምነት መኖርናሙና

በእምነት መኖር

ቀን {{ቀን}} ከ5

አጣብቂኝ

በዚህ ክፍል እስራኤል በተለይ ሰማርያ በችግር ውስጥ ነው፡፡ በከባድ ድርቅ መካከል ነው ያሉት፡፡ እናቶች ልጆቻቸውን እየበሉ ነበር፣ የአህያ ጭንቅላትና የአዕዋፍ ኩስ ሜንዩ ላይ የቀረበበት ጊዜ ነበር፡፡ እኔ ስለእናንተ አላውቅም ግን በዚያም ጊዜ ቢሆን እነዚህ ትክክለኛም ሆነ የቅንጦት ምግብ አይመስሉኝም፡፡ ነገር ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ነበር፡፡ በዚህ መሃል አንድ ንጉስ መላውን ከተማ ከበበ፡፡ አጣብቂኝ ማለት ይህ ነው።

ወደ ጌታ መጮህ ሲጀምሩ ጌታ መልስ ሰጣቸው። ባልታሰበ መንገድ መሥራት ጀመረ፡፡ ሶስት ያልተጠበቁ ነገሮችን ላሳያችሁ እፈልጋለሁ፦

1.    ያልተጠበቀ ጊዜ - እግዚአብሔር ነገ በዚህ ጊዜ ረሃብ አይኖርም ብሎ ሲናገር የንጉሡ መኮንን ለማመን ተቸገረ፡፡ አለማመኑም ልክ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ምንም እንኳን ምግብ ለመግዛት አቅም ቢያገኙ በወረራው ምክንያት የትም ሄደው መግዛት አይችሉም፡፡ እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ዝናብ ቢልክም እንኳ ለመዝራትና ለመሰብሰብ አንድ ዓመት ያስፈልጋቸዋል። እግዚአብሔር ግን ሁኔታውን ሁሉ ባልተጠበቀ ጊዜ አዞረው፡፡ በ24 ሰዓት ውስጥ ነገሩን ሁሉ ቀየረው፡፡

2.    ያልተጠበቀ ምንጭ - አራቱ ለምጻሞች ወደ ጠላት ሰፈር ለመውረድ ሲወስኑ እግዚአብሔር እግሮቻቸው እንደ ሰረገሎች፣ ፈረሶችና ታላቅ ሰራዊት እንዲሰማ አደረገው እናም ጠላቶቻቸው በፍሃት እቃዎቻቸውንና ምግቦቻቸውን ጥለው ሸሹ፡፡ በዚያም ምሽት እግዚአብሔር ይሸጥበታል ባለው ዋጋ ምግብ መሸጥ ተጀመረ፡፡ ይህ አቅርቦት ከጠላቶቻቸው መንደር ይመጣል ብሎ ማን ያስባል፡፡... ያልተጠበቀ ምንጭ ማለት ይህ ነው!

3.    ያልተጠበቁ ሰዎች - በዚያን ጊዜ እስራኤል ውስጥ ለምጻሞች እንደ ርኩስ ይቆጠራሉ እናም ከህብረተሰቡ ይገለሉ ነበር፡፡ እነሱ “የማይነኩ” ሰዎች ነበሩ፡፡ ግን እግዚአብሔር ጠላትን ለማስወገድ የተጠቀመው እነሱን ነው፡፡ ጠላት ምግብ ትቶ መሸሹን ለከተማው ያወጁት እነሱ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በጣም ያልተጠበቁ ሰዎችን ለአቅርቦቱ መልክተኛ አድርጎ ተጠቀመባቸው፡፡

የሳምሪያን ታሪክ በምናይበት ጊዜ የራሳችንንም ሆነ የሀገራችንን ሁኔታ በተመሳሳይ ሁኔታ እንድናይ ሊያደርገን ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ሃሳብ ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ፣ እሱም እግዚአብሔር ሊንቀሳቀስ እንደሆነ ነው፡፡ ሲንቀሳቀስም ባልተጠበቀ ጊዜ፣ ባልተጠበቀ ምንጭ እና ባተጠበቁ በሰዎች በኩል ነው!

የሕይወት ተዛምዶ

እግዚአብሔር ሊያደርግ ከሚችለው ነገር ላይ ገደባችንን እናንሳ።

ፀሎት

ጌታ ሆይ አምናለሁ! ኤፌ 3፡20



ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

በእምነት መኖር

በእምነት ለመቆም፣ በእምነት የተሞሉ ፀሎቶችን ለመጸለይ እና በሕይወትዎና በሌሎችም ሕይወት ውስጥ ለመንግሥቱ አስገራሚ ነገሮችን ለማከናወን እግዚአብሔር ሊጠቀምብዎት ይችላል። የሚቅጥሉትን 5 ቀናት ይህን እምነቶን በማሳደግ ያሳልፉ።

More

ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org