በእምነት መኖርናሙና
ቀላል እርምጃዎች — ሥርነቀል እምነት
“ዳንኤልም ዐዋጁ እንደወጣ ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ሄደ፤ መስኮቶቹ በኢየሩሳሌም አንጻር ተከፍተው ባሉበት በሰገነቱ ቀድሞ ያደርግ እንደ ነበረው በቀን ሶስት ጊዜ ተንበርክኮ ጸለየ፤ አምላኩንም አመሰገነ፡፡”
በአንድ በተወሰነ አውድ የእምነት ተግባር ቀላል ቢመስልም፣ በተለየ ዐውድ ተመሳሳይ የእምነት ድርጊት ደማችንን የሚያሮጥ ትልቅ የእምነት እርምጃ ሊሆን ይችላል፡፡ ዳንኤል ልክ እንደማንኛውም ቀን በመስኮት በኩል ተንበርክኮ ሲጸልይ ራሱን ያገኘበት ሁኔታም ይህ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን በአደባባይ - በካፌዎችና ሌሎች የህዝብ ማህበራዊ ስፍራዎች ማንበብን በህይወቴ ላይ የምተገብረው ነገር ነበር - ምክንያቱም እንደ ዳንኤል ሁሉ እምነት የግል ነው ግን ድብቅ አይደለም እናም በምንኖርበት ቦታ ሁሉ ራሳችን መሆን መቻል አለብን ብዬ አምናለሁ።
በኢየሱስ ማመን ሕገ ወጥና አደገኛ በሆነበት ቦታ ከገባሁ በኋላ በሃይማኖት ነፃ፣ የተለያዩ ሰዎች አብረው ሚኖሩባትና የተረጋጋች የሆነችውን ሃገሬን ናፈቅሁ፡፡ ግን ከማውቀው የምቾት ቀጠና ውጭ እያለሁ ጥያቄዎች በአእምሮዬ ይመላለሱ ጀመር።
ከምግብ በፊት አሁንም መጸለይ ይኖርብኛል? መጽሐፍ ቅዱስን እንደተለመደው ከካፌ ወደ ካፌ ይዤው ልሂድ ወይስ ልተወው? በዘመናዊው ዓለም ውስጥ ከጥንታዊ ሕግ የተጠበኩ ነኝ? ምን ያደርጉኛል? እስከዛሬ የተዋወቁት ብቸኛ ክርስቲያን እኔ ነኝ? ምን ይላሉ? ለእኔ የተከፈቱ በሮች ይዘጉ ይሆን?” ምን ሆንኩ? ከምቾቴ ስለወጣሁ ከምግብ በፊት መፀለይ ምንም ጉዳት የሌለው የሚመስል ወግ በነፍሴ ውስጥ ሥርነቀል የእምነት መግለጫ ሆነ፡፡
የዐውድ ለውጥ ምን ያህል የባህላችንን ትክክለኛነትን መፈተሽ፣ ተነሳሽነታችንን ማጥራትና ከድሮ እምነታችን ጋር ዳግም ማስተዋወቅ በመቻሉ እናመስግን።
የሕይወት ልምምድ
ራሳችሁን በአዲስ አውድ ውስጥ በጥልቅና ጽኑ በሆነ እምነት ኑሩ፡፡ የእምነት ሥራችሁን ከምቾት ቀጠናቹ ወጥታችሁ ምቾት ወደሌለበት ቦታ አስገቡት፡፡ ምን አዲስ ተግባርና ሕይወት በልባችሁ ውስጥ እንደሚቃጠል ይመልከቱ።
ፀሎት
እግዚአብሔር ሆይ፣ ስኖርባቸው የነበሩትን መሰረታዊ መርሆችን ለመቀየር እና እንደገና ለመጻፍ ፈቃዴን እሰጥሃለሁ፡፡ ማንም ቢያየኝም እና የትም ብሆን ድርጊቴ ንጹህ ልብ እንዲኖርበት እጸልያለሁ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በእምነት ለመቆም፣ በእምነት የተሞሉ ፀሎቶችን ለመጸለይ እና በሕይወትዎና በሌሎችም ሕይወት ውስጥ ለመንግሥቱ አስገራሚ ነገሮችን ለማከናወን እግዚአብሔር ሊጠቀምብዎት ይችላል። የሚቅጥሉትን 5 ቀናት ይህን እምነቶን በማሳደግ ያሳልፉ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org