በእምነት መኖርናሙና
መለኮታዊ አጋጣሚዎች
የተሰበሰበውን ሕዝብ አስቡት፤ በመቶዎች በሚቆጠሩ ግንባሮች ላይ በሞቃታማው ፀሀይ ላብ እየወረደ የኢየሱስን ድምፅ በጉጉት እየሰሙ ነው - እያንዳንዱ ቃል ለነፍስ እርካታን ሰጪ ነው፡፡ ማንም እንዲያቆም አይፈልግም፡፡ በቤቱ ጣሪያ በኩል የቁፋሮ ድምፅ ሲሰማ ሕዝቡ ምን ያህል እንደተበሳጨ መገመት ትችላላችሁ፡፡ “ያ ጫጫታ ምንድነው!? መስማት አልቻልንም! ጫጫታውን አቁሙ - ኢየሱስ እየተናገረ ነው እኮ!”
ግን አንድን ሰው ወደ ኢየሱስ መገኛ ቦታ ዝቅ ማድረግ መቻል እንዴት ያለ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ የሕዝቡን አስተያየት ንቆና በቀጥታ ወደ ኢየሱስ የፍቅር እጆች መግባት እንዴት እፎይታን ይሰጣል። ኢየሱስ እንደነዚህ ያሉትን አጋጣሚዎች መታገስ ብቻ አይደለም ነገር ግን ያስደስቱታል፡፡ ምክንያቱም ጣሪያውን የሚቆፍሩት እርሱ ማን እንደሆነ ተገንዝበዋል ማለት ነው። እምነታቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ ያስገድዳቸዋል! ለመስማት የሚታክት እምነት አለ፣ ደግሞ ጣሪያ ገንጥሎ የሚገባ እምነት አለ፡፡ ለራስ የሚያምን እምነት አለ ደግሞ ለሌላው የሚቆም እምነት አለ፡፡
ኢየሱስ ለሌሎች ያለንን እምነት ያከብረዋል። ኢየሱስ ያየው የሽባውን ሰው እምነት ብቻ ሳይሆን የጓደኞቹንም እምነት ነው፡፡ ሌሎችን ይዘን ወደ ጌታ መቅረብ እንችላለን፡፡ እናም ይህን ስናደርግ የአካል፣ የነፍስና የአዕምሮ ተዓምር እንጠብቃለን፡፡
እምነታችሁ የጋራ ልምምዳችን ላይ ተጽዕኖ አለው፡፡ ከጎናችሁ ያለው ሰው እምነት በእናንተ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። የግላችን ነው፣ ነገር ግን የብቻችን አይደለም። በእያንዳንዳችን ጉዞ ውስጥ ግን እንደ ሕብረት እምነት የተገነባ መለኮታዊ ስርዓት ነው። የጓደኛቹ እምነት በእናንተ ላይ የሚያመጣውን ውጤት አቅልላችሁ አትመልከቱት፡፡ ለሌላ ሰው ብላችሁ ጣራዎችን ለመቆፈር አጋጣሚ ካገኛችሁ አይለፋችሁ፡፡ ሁልጊዜ መቆፈሪያ የሚሸከም አማኝ ሁኑ።
የሕይወት ተዛምዶ
በምን ዓይነት እምነት ውስጥ ነው የምትመላለሱት? በሕይወታችሁ ውስጥ የኢየሱስ መገኘት ምን እንድታደርጉ ይገፋፋችኋል? ጓደኞችህን ለኢየሱስ ቆፍረህ ዝቅ እንድታደርግ የሚጋብዙህ ጣሪያዎች የትኞቹ ናቸው? መቆፈሪያ የሚሸከሙ ሰዎች በዙሪያሽ ሰብስበሻል?
ፀሎት
ኢየሱስ ሆይ፣ ለሌሎች ወዳንተ ለመቆፈር ቃል እገባለሁ፡፡ ፍቅርህን ለማግኘት የሕዝቡን ድምፅ ለመተው ቃል እገባለሁ። በሥራ የተሞላውን እምነቴን ለሌሎች እንዲገኝ አደርጋለሁ።
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
በእምነት ለመቆም፣ በእምነት የተሞሉ ፀሎቶችን ለመጸለይ እና በሕይወትዎና በሌሎችም ሕይወት ውስጥ ለመንግሥቱ አስገራሚ ነገሮችን ለማከናወን እግዚአብሔር ሊጠቀምብዎት ይችላል። የሚቅጥሉትን 5 ቀናት ይህን እምነቶን በማሳደግ ያሳልፉ።
More
ቤዛ ዓለም አቀፍ ሚኒስትሮችን ይህንን እቅድ ስላቀረቡልን እናመሰግናለን ፡፡ ለበለጠ መረጃ ይጎብኙ http://bezainternational.org