ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀን {{ቀን}} ከ14

ድንበሮች አላማ አላቸው!

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፤እርሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል፡፡ - ምሳሌ 3፡5-6

ራስን መቆጣጠር እና ራስን መግዛትን መለማመድ እና ድንበሮችን እና ገደቦችን በህይወታችን ማበጀት ልናደርግ የምንችላቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ስነ-ስርዐት የሌለው ህይወት በግድየለሽነት የተሞላ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቃል በእግዚአብሔር ደህንነታችን ተጠብቆ እንዲቆይ አስፈላጊ ድንበሮችን ያሰምርልናል። ልናደርግ የምንችለውን እና ለደህንነታችን ሲባል ባናደርግ የሚሻለውን ይነግረናል፡፡

እንደ ክርስቲያን ድንበር ጫፍ ላይ መኖር አስደሳች ነው ብለን ልናስብ እንችላለን። “እኔ እኮ አፋፍ ላይ ነው የምኖረው!” የሚለውን ነገር ልንወደው እንችላለን፡፡ህይወትን መመልከቻ ዝነኛ መንገድ ሆኗል፡፡ሀቁን ለመነጋገር ግን እግዚአብሔር አፋፍ ላይ መኖራችንን አይወደውም፡፡ምክንያቱም የምንኖረው ጫፍ ላይ ከሆነ ለስህተት ምንም ድንበር አይኖረንም፡፡

አውራ ጎዳናዎች መስመር አላቸው፣ዳር እና ዳር እና መሀል ላይ፡፡ስንነዳ ደህንነታችን የሚጠበቅበትን ክልል የሚወስኑልን እነዚህ መስመሮች ናቸው፡፡በአንዱ በኩል ያለውን መስመር አልፈን ብንነዳ ገደል እንገባለን፡፡ወደመሀል ያተሰመረውን መስመር ብናልፍ ልንገደል እንችላለን፡፡እነዚያን መስመሮች እንወዳቸዋለን ምክንያቱም ደህንነታችንን ይጠብቁልናል፡፡

በግል ህይወታችንም እንደዚያው ነው፡፡ድንበሮች፣ገደቦች እና ጠርዞች ሲኖሩን የበለጠ ጥሩ ስሜት ይሰማናል የእግዚአብሔርንም ሰላም እንለማመዳለን፡፡

ቁልፉ ልንኖርባቸው የሚገባንን ድንበሮቹን ሁሉ ወደ ዘረዘረበት ወደ እግዚአብሔር ቃል መሄድ ነው፡፡እግዚአብሔር የዕለት ተዕለት መንገዳችሁን ይምራ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በህይወቴ ድንበር ማስመር እንዴት እንደሚያስፈልገኝ ተረድቻለሁ፡፡ ቃልህን ሳነብ ያንተን ጤናማ ድንበሮች እንዴት በህይወቴ በተግባር ላይ ማዋል እንደምችል አሳየኝ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 8ቀን 10

ስለዚህ እቅድ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!

More

ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/