ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀን {{ቀን}} ከ14

ፍርሀትን አውጥቶ መጣል

በፍቅር ፍርሀት የለም፤ፍጹም ፍቅር ግን ፍርሀትን አውጥቶ ይጥላል፤ፍርሀት ከቅጣት ጋር የተያያዘ ነውና፡፡ - 1 ኛ ዮሐ 4፡18

ራት ፊደል ስላለው ቃል ነው ላዋራችሁ የፈለግኩት፡ፍርሀት!

አብዛኞቻችን በልጅነታችን መጥፎ ቃል ከተናገርን እናቶቻችን አፋችንን በሳሙና እናጥባለን እያሉ ያስፈራሩን እንደነበር ሳናስታውስ አንቀርም፡፡ፍርሀት ቆሻሻ የሆነ ባለ አራት ፊደል ቃል ከሆነ በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ያለ እምነት ደግሞ ሳሙና ነው፡፡

እያወራሁ ያለሁት ስለደካማ እምነት አይደለም፡፡እያወራሁ ያለሁት እግዚአብሔር ለእኛ ባለው ወሰን የለሽ፣የማይለዋወጥ እና ፍጹም የሆነ ፍቅር ላይ ስላለ ሀይለኛ እምነት ነው፡፡

አንደኛ ዮሐንስ 4፡18 የሚያስተምረን ለእኛ ያለውን የእግዚአብሔርን ፍቅር መረዳት ከፍርሀቶቻችን እንደሚያድነን ነው፡፡ይሄ ማለት የፍርሀት ስሜት ጭራሽ አይሰማንም ማለት ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት እና ፍቅሩ አስፈላጊ ከሆነ እንድንቋቋመው ያደርገናል ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር አብሯችሁ እንዳለ እንድታውቁ ይፈልጋል፡፡ስለሚመራችሁ እና መንገዳችሁን ስለሚያሳያችሁ እምነታችሁን እና መደገፋችሁን በእርሱ ላይ ማድረግ ትችላላችሁ! እኛ እንኳ ፍጹም ባልሆንን ጊዜ የእርሱ ፍቅር ግን ፍጹም እንደሆነ አስታውሱ፡፡በስህተቶቻችን የተነሳ ትንሽ ወይም ብዙ አይወደንም፡፡እግዚአብሔር ከነአላችሁበት ሁኔታ እንደሚወዳችሁ ማወቅ አያስደስትም? ይሄንን ማሰብ ብቻ እምነታችሁን አሳድጎ ትንሽ ፍርሀታችሁን አይቀንሰውም?

እኔና እናንተ አሁንም አሁንም የፍርሀት ስሜትን እናስተናግዳለን፡፡ እንደዚህ ሲሰማን እያጋጠመን ባለው በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔር እንደሚመራን በማወቅ ትኩረታችንን ወደ እርሱ መመለስ እንችላለን፡፡

በእያንዳንዱ ጊዜ ፍርሀትን አውጥቶ የሚጥለው ፍጹሞቹ እኛ ሳንሆን ፍጹሙ የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ 

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ፍርሀቶቼን አውጥቶ መጣል የሚችለው የአንተ ፍቅር ብቻ ስለሆነ እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ፡፡ህልውናህ ከእኔ ጋር እንዳለና በማናቸውም በሚያጋጥመኝ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ሳልፍ እንደምትመራኝ አውቃለሁ፡፡ፍቅርህን እቀበላለሁ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 13

ስለዚህ እቅድ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!

More

ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/