የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀን {{ቀን}} ከ14

ያለመታከት ነጻነት

ክርስቶስንና የትንሳኤውን ሀይል እንዳውቅ፣በስቃዩ ተካፋይ እንድሆንና በሞቱም እርሱን እንድመስል እመኛለሁ… - ፊሊጲ 3፡10

ትጋት እግዚአብሔርን መከተል ቀላል ነው ማለት አይደለም ፣ ነገር ግን በእርግጠኝነት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ቢሆንም ግን በመጀመሪያ እውነተኛ ነጻነትን እስክትለማመዱ ድረስ የእውነት እግዚአብሔርን ለመከተል አትችሉም፡፡

እግዚአብሔር እኛን ነጻ በማውጣት ስራ ተጠምዷል፤እናም ከጥፋተኝነት ስሜት፣ከክስ፣ሰዎች ስለኛ ስለሚያስቡት ከመጨነቅ ነጻ መውጣት በጣም የከበረ ነገር ነው፡፡

በክርስቶስ ማን መሆናችንን ስናውቅ ከመውደቅ ፍርሀት ነጻ ወጥተናል፡፡ይሄ ደግሞ ተነስተን የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃላት ለመከታተል ወደ ምንችልበትን ብርታት ያደርሰናል፡፡

እግዚአብሔር ከሰጠኝ ነጻነቶች ትልቁ ራሴን የመሆን ነጻነት ነው፡፡ምንም እንኳ እንደ ሌሎች ሰዎች እንዳልሆንኩ ባውቅም ይሄንን ወይም ያንን መሆን እንዳለብኝ እየተሰማኝ ለአመታት ያልሆንኩትን ለመሆን ስጥር ነበር፡፡ከእግዚአብሔር ጋር ባለኝ ግንኙነት ምን እንድሆን እንደፈጠረኝ እስክማር ድረስ ሌሎችን ለመሆን መጣሬን ቀጥዬ ነበር፡፡በኢየሱስ ላይ እንዳተኩር እና ሌሎችን እርሱ እንድደርሳቸው በፈለገው መንገድ እንድደርሳቸው እራሴን ከራሴ ነጻ አውጥቶልኛል፡፡

ፊሊጲሲዩስ 3 ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተላቸውን ነገሮች ማለትም እርሱን እና የትንሳኤውን ሀይል ለማወቅ እንደቆረጠ ይናገራል፡፡ዳግም ስንወለድ በውስጣችን የሚነሳ የቁርጠኝነት መንፈስ አለ ብዬ አምናለሁ፡፡ይሄንንም የመንፈስ ቅዱስ መሻት ወይም ቅናት ብለን መጥራት የምንችል ሲሆን በከባድ ጊዜ “ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ፣የሞቀ፣ጥልቅ የሆነ የግል ግንኙነት ከማድረግ ወደኋላ አልልም፡፡ክርስቶስ እንድሆን የፈለገውን ሁሉ ከመሆን አልታክትም” ለማለት የሚያስችለንን አቅም የሚሰጠን ነው፡፡ 

በእምነት ለመቀጠል እና የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ለመቀበል ቁርጠኛ ሁኑ፡፡የእግዚአብሔር እንደሆናችሁ እና እርሱም ቆራጥ መንፈስ እንደሰጣችሁ አስታውሱ!

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ያለመታከት አንተን እና የተስፋ ቃሎችህን በመከታተል አዲስ ህይወት መኖር እፈልጋለሁ፡፡ስትፈጥረኝ እንድሆን የፈለግከውን እንድሆን እና እውነተኛ ነጻነትን እንድለማመድ እንደምትረዳኝ አምናለሁ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 11ቀን 13

ስለዚህ እቅድ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!

More

ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/