የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀን {{ቀን}} ከ14

ቀጣይነት ያለው ህይወት

በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡ - መዝ 23፡2

ቀጣይነት ያለው ህይወት ነው ያላችሁ? ምናልባት ራሳችሁን “ከዚህ በላይ እንደዚህ መቀጠል አልችልም። ይሄንን ለዘላለም መሸከም አልችልም” ስትሉ አግኝታችሁት ሊሆን ይችላል። እንደዚህ አይነት አስተያየት ስትሰጡ እያላችሁ ያላችሁት “አቅሜ ውስን ነው፤አሁን ደግሞ አልቋል ነገር ግን ዝም ብዬ ምን ያህል መቀጠል እንደምችል አያለሁ፡፡” ነው፡፡

ሰውነታችንን ከአቅሙ በላይ ስንገፋው እንደ ቁርጠት ወይም የህመም ስሜት ያለ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል፡፡ነገር ግን ማስጠንቀቂያዎቹን በመናቅ ግድየለም ይሻለኛል ብለን እንልና በጣም ታመን መቋቋም በማንችልበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፡፡

ምንም እንኳን የምኮራበት ነገር ባይሆንም ለመጀመሪያዎቹ 20 የአገልግሎት አመታቶቼ ብዙውን ጊዜ አካላዊ ጤንነት አይሰማኝም ነበር፡፡ወደ ሀኪሞች እመላለስ እና ብዙ ኪኒኖች እና ቫይታሚኖችን እወስድ ነበር፡፡ሀኪሞቹ ከአቅሜ በላይ እየሰራሁ እንደሆነ ሊነግሩኝ ይሞክሩ ነበር እኔ ግን ችላ አልኳቸው፡፡ከአቅም በላይ እየሰራሁ እራሴን ማድከሜን ብዙ በመጓዝ፣ብዙ ንግግር በማድረግ እና ሌሎች ነገሮችን በማከናወን ቀጠልኩበት፡፡

በመጨረሻ ለማረፍ ጊዜ ለመውሰድ እግዚአብሔር ሲመራ ቸል ማለት እንደማይቻል እና ዋጋ መክፈል እንደሌለብኝ ተረዳሁ፡፡ስለዚህም አንዳንድ ለውጦችን አደረግኩ እናም ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥሩ ይሰማኛል፡፡

የምትኖሩት ኑሮ ቀጣይነት የሌለው ከሆነ ማድረግ ያለባችሁን ለውጥ ከማድረግ ራሳችሁን አትከልክሉት፡፡እንደ የስሜት መጎዳት የልብ ድካም ያለ አንድ ነገር እስኪፈጠር አትጠብቁ፡፡እግዚአብሔር እንድትኖሩ የሚፈልገውን አይነት ኑሮ ለመኖር አሁን ለውጦችን አድርጉ፡፡

የእግዚአብሔር በሆነው መንገድ ስትኖሩ በጣም አስደናቂ የሆነ አዲስ የሰላም ደረጃ ውስጥ እንደምትገቡ ዋስትናን እሰጣችኋለሁ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ቀጣይነት ሊኖራቸው የማይገባቸውን የህይወቴን አቅጣጫዎች አሳየኝ፡፡ለአንተ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፡፡ህይወቴን እንድደሰትበት እና ለሚመጡት አመታት ሁሉ እንዳገለግልህ ወደ እረፍትህ እና ሰላምህ ምራኝ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 9ቀን 11

ስለዚህ እቅድ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!

More

ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/