የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀን {{ቀን}} ከ14

ጸጋ-በነጻ የተሰጠን የእግዚአብሔር ሀይል

…እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችሁ በሰጣችሁ እምነት መጠን… - ሮሜ 12፡3

በዚህ አለም ላይ መኖር ከጀመራችሁ ረጅም ጊዜ ያስቆጠራችሁ ከሆነ በጣም ጥቂት ቀናት ብቻ ልክ እንደምንፈልጋቸው ሆነው እንደምናገኛቸው ተምራችኋል ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር ደስታችንን ጠብቀን የምናሳልፍበትን አቅም ሳይሰጠን በአንድ ነገር ውስጥ ስለማያሳልፈን ምስጋና ይግባው፡፡

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሁኔታ ልዩ የሆነውን ጸጋውን ሰጥቶናል ብዬ አምናለሁ፡፡ጸጋን የምተረጉመው እንደዚህ ነው፡፡ “ማድረግ ያለብንን ማናቸውንም ነገር እንድናደርግ የሚረዳን የእግዚአብሔር ሀይል” ይሄን ሀይል ዛሬ ማግኘት ትችላላችሁ ነገር ግን መቀበል ነው ያለባችሁ እና ደግሞ መቀበያው ብቸኛ መንገድ እምነት ነው፡፡ 

ሮሜ 12፡3 እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነት መጠን ሰጥቷል ይላል፡፡ዛሬ ራሳችሁን በተሰጠኝ እምነት ምን እያደረግኩበት ነው? ብላችሁ ጠይቁ፡፡እምነታችሁን በራሳችሁ ላይ፣በሰዎች ላይ፣ወይስ በነገሮቻችሁ ላይ እያደረጋችሁ ነው? ይህ በጸጋ መኖር አይደለም፡፡ይሄ በራሳችሁ ጥንካሬ እና በስራችሁ መኖር ነው፡፡እናም ይሄ ውጤታማ እንድትሆኑ አያደርግም!

ነገር ግን እምነታችሁን መጠቀም ስትጀምሩ እና እናንተ ማድረግ የማትችሉትን ማድረግ እንደሚችል በእግዚአብሔር ስትታመኑ ያ እምነታችሁን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ ነው፡፡ጸጋ-የእግዚአብሔር ሀይል በእምነት በኩል ይመጣና እናንተን እና ሌሎችን የሚያስገርም ነገር እንድታደርጉ ያስችላችኋል፡፡

ረጅሙ የጸጋ ትርጉሜ ይሄ ነው፡ “ወደ እኛ በነጻ የመጣ የእግዚአብሔር ሀይል ነው-ይህም ማለት እምነታችንን በእግዚአብሔር ላይ ከማድረግ ሌላ ለማግኘት ምንም ዋጋ አልከፈልንም ማለት ነው፡፡በየትኛውም አይነት ትግል እና ጥረት በፍጹም በራሳችን ልናደርገው የማንችለውን በቀላሉ እንድናደርገው የሚያስችለን ነው፡፡”

እምነታችሁን በእግዚአብሔር ላይ አድርጉ፡፡ዛሬ ጸጋውን ሊሰጣችሁ ይፈልጋል፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ህይወት ሁልጊዜ እኔ በፈለግኩት መንገድ እንደማይሄድ አውቃለሁ፡፡ነገር ግን በአንተ እታመናለሁ፡፡በእምነት ጸጋህን እቀበላለሁ፤ይኸውም ዛሬ በሚያጋጥመኝ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ሳልፍ እንዲረዳኝ በነጻ የሰጠኸኝ ሀይል ነው፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 4ቀን 6

ስለዚህ እቅድ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!

More

ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/