የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀን {{ቀን}} ከ14

ኦው ትችላላችሁ!

በሰዎች ሁሉ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም… - 1 ኛ ቆሮ 10፡13

እኛ ሁላችን እንፈተናለን-ልናስወግደው የማንችል የህይወታችን ክፍል ነው፡፡ጥያቄው ትፈተናላችሁ ወይ? አይደለም፡፡ጥያቄው ስትፈተኑ ዝግጁ ትሆኑ ይሆን ወይ? ነው፡፡

ይሄ እንዲገባችሁ በጣም እፈልጋለሁ፤ፈተናን ማሸነፍ ትችላላችሁ፡፡“ጆይስ የምችል አይመስለኝም” ማለት አቁሙ፡፡አልችልም የሚለውን ቃል ከመጠቀም ታቀቡ፡፡

በራሳችሁ ጉልበት እና ችሎታ ልክ ናችሁ አትችሉም፡፡ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል በልባችሁ ስታኖሩ፣በጉልበቱ ስትደገፉ እና ቃል ኪዳኖቹን ስታምኑ ላታሸንፉት የምትችሉት ፈተና አይኖርም፡፡

ፈተናን በማሸነፍ ረገድ ልዩነትን የሚያመጡ አምስት ነገሮችን ባለፉት በአመታት ውስጥ አስተውያለሁ፡፡መጀመሪያ ብልህ መሆን አለባችሁ፡፡እየመረጣችኋቸው ስላሉት ምርጫዎቻችሁ እና ውጤቶቻቸው ከመምረጣችሁ በፊት አስቡ፡፡ጥበብ የሩቁን ያያል፡፡

በመቀጠል ፈተናን ማሸነፍ እንደምትችሉ ማመን ይኖርባችኋል፡፡ክስ፣ዕፍረት እና የጥፋተኝነት ስሜት እንዳትበረቱ ያደርጓችኋል፡፡በጊዜ ካስቆማችኋቸው ሀይላቸውን ያጣሉ፣ነገር ግን አንዴ እየተንከባለሉ ከቀጠሉ ለማቆም አስቸጋሪ ናቸው፡፡ሶስተኛው ፈተና መጋፈጥን እንደ መደበኛ የህይወት ዘይቤ ቁጠሩት፡፡ግጭት ይነሳል ብላችሁ ከጠበቃችሁ ሁሌም ዝግጁ ነው የምትሆኑት፡፡አራተኛው የምትደክሙበትን ነገር አስወግዱ፡፡በቀላሉ ልትወድቁ ምትችሉበት ሁኔታ ላይ እራሳችሁን አታስቀምጡ፡፡ ገንዘባችሁን ማስተዳደር ፈተና ከሆነባችሁ ምንም ለመግዛት አቅም በሌላችሁ ወቅት ወደ የገበያ ስፍራ አትሂዱ! 

በመጨረሻም ለራሳችሁ በጣም ትልቅ ስፍራን አትስጡ፡፡ከመፈተን አንመረቅም፡፡ከመደናቀፍ እንዳደጋችሁ ማሰብ በጣም ቀላል ነው ነገር ግን አንዴ ካጋጠማችሁ በኋላ እራሳችሁን በቀላሉ የምትገኙ ነው የምታደርጉት፡፡

እግዚአብሔር በህይወታችሁ በሁሉም አቅጣጫ ድልን ያመጣል ብላችሁ እንድትታመኑበት ይፈልጋል፡፡በጸጋው ….ትችላላችሁ!

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ፣ፈተና የህይወቴ አካል እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ሲመጣ እንዳያስደነግጠኝ ወይም በድንገት እንዳያጋጥመኝ እርዳኝ፡፡ሁሉንም እና ማናቸውንም አይነት ፈተናዎች በማሸነፍ በአንተ ድል እንድኖር ስለሰጠኸኝ ጥበብ እና ጸጋ አመሰግናለሁ፡፡

ቅዱሳት መጻሕፍት

ቀን 2ቀን 4

ስለዚህ እቅድ

ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋ

ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!

More

ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/