ለዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ተስፋናሙና
ህልማችሁን እንደ አዲስ ጀምሩት
ራዕይ በሌለበት ህዝብ መረን ይሆናል… - ምሳ 29፡18
እግዚአብሄር በልባችሁ ያስቀመጠው ህልም ምንድነው? ህልም አላችሁ ወይ ብዬ አይደለም እየጠየቅኳችሁ ያለሁት -እንዳላችሁ አውቃለኋ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሁላችንም ህልምን ሰጥቷል፡፡
ሰዎች ህልማቸውን ብዙ አይነት ነገር ሲያደርጉት አይቻለሁ፡፡አንዳንዶች ራሳቸውን ከሌሎች ትችት ለመጠበቅ ሲሉ በልባቸው ጥልቀት ውስጥ ይቀብሩታል፡፡አንዳንዶች ደግሞ ህልማቸውን አርቀው ስለእርሱ ምንም እንዳያስቡ ይሆናሉ፡፡ሌሎች ደግሞ ይዞ መቀጠል በጣም ስለሚጎዳቸው በህልማቸው ላይ ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
ህልማችሁ እንደ አዲስ መጀመር ካለበት ሁለት ነገሮችን ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ፡፡የመጀመሪው ነገር ግልጽ ሆነ ራዕይ ማግኘት አለባችሁ፡፡ሁለተኛው ደግሞ ሁልጊዜ ራዕያችሁን ከፊት ለፊታችሁ ልታደርጉት ይገባል፡፡
ነገር ግን ራዕይ ማግኘት ማለት በቅጽበት ይፈጸማል ማለት አይደለም፡፡እግዚአብሔር እንደ ራዕዩ ውጤት ሁሉ የራዕዩም አካሄድ ያሳስበዋል፡፡
በፊሊጲሲዩስ 4፡11-13 ሐዋሪያው ጳውሎስ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን እንደተማረ እና በማንኛውም ሁኔታ የማይታወክበት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ይናገራል፡፡በሌላ ቋንቋ በጊዜው ካለበት ሁኔታ በመነሳት እንዲናደድ ለራሱ አይፈቅድለትም…ሁሌም የሚያየው ነገ የሚደርስበትን ነው፡፡
ይሄ ማለት እናንተም እንደ ጳውሎስ በፍላጎታችሁ እና ያለኝ ይበቃኛል በማለት መካከል ሚዛናዊ ልትሆኑ ይገባል፡፡ቁልፉ ደግሞ ይሄ ነው፡ወደ ምትደርሱበት እየሄዳችሁ ሳለ በምታልፉበት መደሰትን ተማሩ፡፡
ህልም ወይም ራዕይ ሲኖራችሁ፣ከፊት ለፊታችሁ ልታደርጉት ይገባል፡፡የሚረዳችሁ ከሆነ ጻፉት፡፡ይሄንን አስታውሱ፤እግዚአብሔር የሰጣችሁን ህልም ቀስ በቀስ በአንድ ቀን አንድ ነገር እደረገ እንድትኖሩት ይረዳችኋል፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ኢየሱስ፣ምንም እንኳ ሁልጊዜ እንደዚህ ባይሰማኝም ደግሞም ኑሮ እንዳቋርጥ ቢገፋፋኝም ለህይወቴ ትልቅ እቅድ አለህ ብዬ አምናለሁ፡፡በሁኔታዎቼ ከመታመን ይልቅ የሰጠኸኝን ህልም እንድኖረው ትረዳኛለህ ብዬ በአንተ መታመንን መርጫለሁ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ቀንዎን ከጆይስ ሜየር ተግባራዊ በሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይጀምሩ። ይህ ዕለታዊ ማበረታቻ ተስፋ እንዲኖርዎ ፣ አዕምሮዎን ማደስ እንዲችሉ እንዲሁም በየቀኑ በዓላማ መኖር እንዲችሉ ያግዛል!
More
ጆይስ ሜየር ሚኒስትሮች ይህንን ዕቅድ ስላቀረብን ማመስገን እንወዳለን ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎን ይጎብኙ https://tv.joycemeyer.org/amharic/