ማሕልየ መሓልይ 5:2-16

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።” ቀሚሴን አውልቄአለሁ፤ ታዲያ እንዴት እንደ ገና ልልበስ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ እንዴት እንደ ገና ላቈሽሸው? ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤ ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር። ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤ በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣ በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣ የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ። ለውዴ ከፈትሁለት፤ ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዷል፤ በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤ ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም። የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ ልብሴንም ገፈፉኝ። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እማጠናችኋለሁ፤ ውዴን ካገኛችሁት፣ ምን ትሉት መሰላችሁ? በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት። አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤ ከዐሥር ሺሖችም የሚልቅ ነው። ራሱ የጠራ ወርቅ፣ ጠጕሩ ዞማ፣ እንደ ቍራም የጠቈረ ነው። ዐይኖቹ፣ በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣ በወተት የታጠቡ፣ እንደ ዕንቍም ጕብ ጕብ ያሉ ናቸው። ጕንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣ የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ ውብ አበቦች ናቸው። ክንዶቹ በቢረሌ ፈርጥ ያጌጠ፣ የወርቅ ዘንግን ይመስላሉ፤ ሰውነቱም በሰንፔር ፈርጥ ያጌጠ፣ አምሮ የተሠራ የዝኆን ጥርስን ይመስላል። እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣ የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤ እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው። አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ ሁለንተናውም ያማረ ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ። ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ? ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ። ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ እጆቼ በደጁ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ። ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም። ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት። አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ይህን የሚያህል አምለሽናልና ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው። ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፥ ቈንዳላው የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራ ጥቁረትም ጥቁር ነው። ዓይኖቹ በሙሉ ፈሳሽ አጠገብ እንዳሉ በወተት እንደ ታጠቡ በፈሳሽ ውኃ አጠገብ እንደ ተቀመጡ እንደ ርግቦች ናቸው። ጕንጩና ጕንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ። እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ እንዳለበት እንደ ወርቅ ቀለበት ናቸው፥ አካሉ ብልሃተኛ እንደ ሠራው በሰንፔር እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው። እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው። አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወን​ድሜ ቃል ደጅ እየ​መታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍ​ን​ዳ​ላ​ዬም የሌ​ሊት ነጠ​ብ​ጣብ ሞል​ቶ​በ​ታ​ልና ክፈ​ች​ልኝ። ቀሚ​ሴን አወ​ለ​ቅሁ፥ እን​ዴት እለ​ብ​ሰ​ዋ​ለሁ? እግ​ሬን ታጠ​ብሁ፥ እን​ዴት አሳ​ድ​ፈ​ዋ​ለሁ? ልጅ ወን​ድሜ እጁን በቀ​ዳዳ ሰደደ፥ አን​ጀ​ቴም ስለ እርሱ ታወ​ከች። ለልጅ ወን​ድሜ እከ​ፍ​ት​ለት ዘንድ ተነ​ሣሁ፤ እጆች በደጁ መወ​ር​ወ​ሪያ ላይ ከር​ቤን አፈ​ሰሱ፥ ጣቶች ፈሳ​ሹን ከርቤ አን​ጠ​ባ​ጠቡ። ለልጅ ወን​ድሜ ከፈ​ት​ሁ​ለት፥ ልጅ ወን​ድሜ ግን ሂዶ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተ​ነሣ ደነ​ገ​ጠች፤ ፈለ​ግ​ሁት፥ አላ​ገ​ኘ​ሁ​ትም፤ ጠራ​ሁት፥ አል​መ​ለ​ሰ​ል​ኝም። ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ዞ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች አገ​ኙኝ፤ መቱኝ፥ አቈ​ሰ​ሉ​ኝም፤ ቅጥር ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የዐ​ይነ ርግብ መሸ​ፈ​ኛ​ዬን ከራሴ ላይ ወሰ​ዱት። እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ በም​ድረ በዳ ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ልጅ ወን​ድ​ሜን ያገ​ኛ​ች​ሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍ​ቅር የተ​ነሣ መታ​መ​ሜን ትነ​ግ​ሩት ዘንድ። አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አም​ለ​ሽ​ና​ልና ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው? ወን​ድሜ ነጭና ቀይ ነው፥ ከአ​እ​ላፍ የተ​መ​ረጠ ነው። ራሱ ምዝ​ምዝ ወርቅ ነው፤ ቈን​ዳ​ላው የተ​ዝ​ረ​ፈ​ረፈ ነው፥ እንደ ቍራ ጥቍ​ረ​ትም ጥቁር ነው። ዐይ​ኖቹ በሙሉ የውኃ ኵሬ አጠ​ገብ እን​ዳሉ በወ​ተት እንደ ታጠቡ በኵሬ ውኃ አጠ​ገብ እንደ ተቀ​መጡ፥ እንደ ርግ​ቦች ናቸው። ጕን​ጮቹ ሽቱን የሚ​ያ​ፈ​ስሱ የሽቱ መደብ ናቸው። ከን​ፈ​ሮቹ እንደ አበ​ቦች ናቸው፥ የሚ​ፈ​ስስ ከር​ቤ​ንም ያን​ጠ​ባ​ጥ​ባሉ። እጆቹ የተ​ር​ሴስ ፈርጥ እን​ዳ​ለ​ባ​ቸው እንደ ለዘቡ የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ናቸው፤ ሆዱ በሰ​ን​ፔር ዕንቍ እን​ዳ​ጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው፥ እግ​ሮቹ በም​ዝ​ምዝ ወርቅ እንደ ተመ​ሠ​ረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰ​ሶ​ዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባ​ኖ​ስና እንደ ዝግባ ዛፍ የተ​መ​ረጠ ነው። ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤ ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤ “እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣ አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ። ራሴ በጤዛ፣ ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።” ቀሚሴን አውልቄአለሁ፤ ታዲያ እንዴት እንደ ገና ልልበስ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ እንዴት እንደ ገና ላቈሽሸው? ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤ ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር። ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤ በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣ በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣ የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ። ለውዴ ከፈትሁለት፤ ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዷል፤ በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤ ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም። የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ ልብሴንም ገፈፉኝ። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እማጠናችኋለሁ፤ ውዴን ካገኛችሁት፣ ምን ትሉት መሰላችሁ? በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት። አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣ ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው? ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤ ከዐሥር ሺሖችም የሚልቅ ነው። ራሱ የጠራ ወርቅ፣ ጠጕሩ ዞማ፣ እንደ ቍራም የጠቈረ ነው። ዐይኖቹ፣ በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣ በወተት የታጠቡ፣ እንደ ዕንቍም ጕብ ጕብ ያሉ ናቸው። ጕንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣ የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ ውብ አበቦች ናቸው። ክንዶቹ በቢረሌ ፈርጥ ያጌጠ፣ የወርቅ ዘንግን ይመስላሉ፤ ሰውነቱም በሰንፔር ፈርጥ ያጌጠ፣ አምሮ የተሠራ የዝኆን ጥርስን ይመስላል። እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣ የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤ እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው። አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ ሁለንተናውም ያማረ ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ። ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ? ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ። ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ እጆቼ በደጁ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ። ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም። ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት። አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ይህን የሚያህል አምለሽናልና ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ውድሽ ማን ነው? ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው። ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፥ ቈንዳላው የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራ ጥቁረትም ጥቁር ነው። ዓይኖቹ በሙሉ ፈሳሽ አጠገብ እንዳሉ በወተት እንደ ታጠቡ በፈሳሽ ውኃ አጠገብ እንደ ተቀመጡ እንደ ርግቦች ናቸው። ጕንጩና ጕንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ። እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ እንዳለበት እንደ ወርቅ ቀለበት ናቸው፥ አካሉ ብልሃተኛ እንደ ሠራው በሰንፔር እንዳጌጠ እንደ ዝሆን ጥርስ ነው። እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ እንደ ተመሠረቱ እንደ ዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስና እንደ ዝግባ ዛፍ መልካም ነው። አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እኔ ተኝቼአለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ውዴ እንዲህ እያለ በር ሲያንኳኳ ሰማሁት፤ “ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ! እንከን የሌለብሽ ርግቤ ሆይ! እባክሽ በሩን ክፈችልኝ፤ ራሴ በጠል ርሶአል ጠጒሬም በሌሊት ካፊያ ረስርሶአል።” ልብሴን አውልቄአለሁ፤ ታዲያ፥ እንደገና ልልበስን? እግሬንም ታጥቤአለሁ፤ ታዲያ፥ እንዴት እንደገና ላሳድፈው? ውዴ በመተላለፊያው በኩል እጁን ወደ ውስጥ ዘረጋ፤ አንጀቴም ስለ እርሱ ተንሰፈሰፈ። ስለዚህ ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፤ የበሩን መክፈቻ እጀታ ስይዘው እጆቼ ከርቤ አንጠባጠቡ፤ ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አፈሰሱ። ለውዴ በሩን ከፈትኩለት። ውዴ ደርሶ ተመለሰ፤ ድምፁን ለመስማት እጅግ ጓጉቼ ነበር፤ አጥብቄ ፈለግኹት፤ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም፤ ጠራሁት፤ እርሱ ግን አልመለሰልኝም። እየተዘዋወሩ ከተማውን የሚጠብቁ ሰዎች አገኙኝ፤ ደብድበውም አቈሰሉኝ፤ የከተማውን ቅጽር የሚጠብቁ ዘበኞች መጐናጸፊያዬን ገፈው ወሰዱብኝ። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ እኔ ከፍቅሩ የተነሣ መታመሜን እንድትነግሩት ዐደራ እላችኋለሁ። አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ! በውኑ የአንቺ ፍቅረኛ ከሌሎች የተለየ ነውን? ስለ እርሱ ይህን ያኽል ዐደራ የምትዪን? እርሱ ከሌሎች የሚለይበት ነገር ምንድን ነው? ውዴ እጅግ የተዋበና ጤነኛ ነው፤ ከዐሥር ሺህ ወንዶች መካከል እርሱን የሚመስለው የለም። የእርሱ ራስ የወርቅ ሉል ይመስላል፤ ጠጒሩም ዞማና እንደ ቊራ የጠቆረ ነው። ዐይኖቹ በወንዝ አጠገብ እንደሚታዩና በወተት የታጠቡ እንደሚመስሉ ርግቦች ያምራሉ። የጉንጮቹ ማማር ጣፋጭ ሽታ ያላቸው የቅመማቅመም ዕፀዋት እንደሚገኙበት የአትክልት ቦታ ነው፤ ከንፈሮቹ መዓዛው የሚጣፍጥ የከርቤ ሽቶ እንደሚያፈሱ የአሸንድዬ አበባዎች ናቸው። ክንዶቹ የዕንቊ ፈርጥ እንዳለበት የወርቅ ዘንግ ያምራሉ፤ አካሉ በሰንፔር ዕንቊ እንዳጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው። እግሮቹ በወርቅ መሠረት ላይ የተተከሉ የዕብነበረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ በሊባኖስ ዛፍ እንዳጌጠ እንደ ሊባኖስ ተራራ ነው። አፉ እንደ ማር. የጣፈጠ ነው፤ ሁለንተናውም የደስ ደስ አለው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት እንግዲህ ውዴና ወዳጄ ይህን የመሰለ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 5:2-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል። ቀሚሴን አወለቅሁ፥ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ፥ እንዴት አሳድፈዋለሁ? ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ። ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ እጆቼ በደጁ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠባጠቡ። ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም። ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አስምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት። አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው? ይህን የሚያህል የምታስምይን? ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው? ውዴ ብሩህና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው። ራሱ ምዝምዝ ወርቅ ነው፥ ጸጉሩ የተዝረፈረፈ ነው፥ እንደ ቁራም ጥቁር ነው። ዐይኖቹ በውሃ ምንጮች አጠገብ እንዳሉ በወተት እንደ ታጠቡ በፈሳሽ ውኃ አጠገብ እንደ ተቀመጡ እንደ ርግቦች ናቸው። ጉንጩና ጉንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ። እጆቹ የቢረሌ ፈርጥ ያለበት የወርቅ ቀለበት ናቸው፥ አካሉ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው። እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ ላይ የተመሠረቱ የዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ዝግባ ዛፍ ምርጥ ነው። አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።