እኔ ተኝቼአለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ውዴ እንዲህ እያለ በር ሲያንኳኳ ሰማሁት፤ “ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ! እንከን የሌለብሽ ርግቤ ሆይ! እባክሽ በሩን ክፈችልኝ፤ ራሴ በጠል ርሶአል ጠጒሬም በሌሊት ካፊያ ረስርሶአል።” ልብሴን አውልቄአለሁ፤ ታዲያ፥ እንደገና ልልበስን? እግሬንም ታጥቤአለሁ፤ ታዲያ፥ እንዴት እንደገና ላሳድፈው? ውዴ በመተላለፊያው በኩል እጁን ወደ ውስጥ ዘረጋ፤ አንጀቴም ስለ እርሱ ተንሰፈሰፈ። ስለዚህ ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፤ የበሩን መክፈቻ እጀታ ስይዘው እጆቼ ከርቤ አንጠባጠቡ፤ ጣቶቼም የከርቤ ፈሳሽ አፈሰሱ። ለውዴ በሩን ከፈትኩለት። ውዴ ደርሶ ተመለሰ፤ ድምፁን ለመስማት እጅግ ጓጉቼ ነበር፤ አጥብቄ ፈለግኹት፤ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም፤ ጠራሁት፤ እርሱ ግን አልመለሰልኝም። እየተዘዋወሩ ከተማውን የሚጠብቁ ሰዎች አገኙኝ፤ ደብድበውም አቈሰሉኝ፤ የከተማውን ቅጽር የሚጠብቁ ዘበኞች መጐናጸፊያዬን ገፈው ወሰዱብኝ። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ውዴን ያገኛችሁት እንደ ሆነ እኔ ከፍቅሩ የተነሣ መታመሜን እንድትነግሩት ዐደራ እላችኋለሁ። አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ! በውኑ የአንቺ ፍቅረኛ ከሌሎች የተለየ ነውን? ስለ እርሱ ይህን ያኽል ዐደራ የምትዪን? እርሱ ከሌሎች የሚለይበት ነገር ምንድን ነው? ውዴ እጅግ የተዋበና ጤነኛ ነው፤ ከዐሥር ሺህ ወንዶች መካከል እርሱን የሚመስለው የለም። የእርሱ ራስ የወርቅ ሉል ይመስላል፤ ጠጒሩም ዞማና እንደ ቊራ የጠቆረ ነው። ዐይኖቹ በወንዝ አጠገብ እንደሚታዩና በወተት የታጠቡ እንደሚመስሉ ርግቦች ያምራሉ። የጉንጮቹ ማማር ጣፋጭ ሽታ ያላቸው የቅመማቅመም ዕፀዋት እንደሚገኙበት የአትክልት ቦታ ነው፤ ከንፈሮቹ መዓዛው የሚጣፍጥ የከርቤ ሽቶ እንደሚያፈሱ የአሸንድዬ አበባዎች ናቸው። ክንዶቹ የዕንቊ ፈርጥ እንዳለበት የወርቅ ዘንግ ያምራሉ፤ አካሉ በሰንፔር ዕንቊ እንዳጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው። እግሮቹ በወርቅ መሠረት ላይ የተተከሉ የዕብነበረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤ መልኩ በሊባኖስ ዛፍ እንዳጌጠ እንደ ሊባኖስ ተራራ ነው። አፉ እንደ ማር. የጣፈጠ ነው፤ ሁለንተናውም የደስ ደስ አለው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት እንግዲህ ውዴና ወዳጄ ይህን የመሰለ ነው።
መኃልየ መኃልይ 5 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መኃልየ መኃልይ 5:2-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች