መዝሙር 140:6-8
መዝሙር 140:6-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኀያላኖቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፥ ተችሎኛልና ቃሌን ስሙኝ። እንደ ጓል በምድር ላይ ተሰነጣጠቁ እንዲሁ አጥንቶቻቸው በሲኦል ተበተኑ፥ አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፤ በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አታውጣት።
መዝሙር 140:6-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ “አንተ አምላኬ ነህ” እልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የልመና ጩኸቴን ስማ። ብርቱ አዳኝ የሆንህ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በጦርነት ዕለት የራስ ቍር ሆንኸኝ። እግዚአብሔር ሆይ፤ የክፉዎች ምኞት አይፈጸም፤ በትዕቢትም እንዳይኵራሩ፣ ዕቅዳቸው አይሳካ። ሴላ