መዝሙረ ዳዊት 140:6-8

መዝሙረ ዳዊት 140:6-8 መቅካእኤ

ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥ ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፥ በመንገድ ዕንቅፋትን አኖሩ። ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥ የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት። አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጉልበት፥ በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።