የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 140

140
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 71፥4። አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድነኝ፥
ከዓመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ
3በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥
ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።
4 # መዝ. 64፥4፤ ሮሜ 3፥13። ምላሳቸውን እንደ እባብ ሳሉ፥
ከከንፈራቸው በታች የእፉኝት መርዝ አለ።
5 # ኤር. 18፥22፤ መዝ. 56፥7፤ 57፥7። አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥
እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ
ከዓመፀኞች አድነኝ።
6ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥
ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፥
በመንገድ ዕንቅፋትን አኖሩ።
7 # መዝ. 31፥15። ጌታንም፦ አንተ አምላኬ ነህ፥
የልመናዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድምጥ አልሁት።
8አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የመድኃኒቴ ጉልበት፥
በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ።
9አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥
ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።
10የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ#140፥10 ኮሩብኝ።
የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው።
11 # መዝ. 11፥6፤ 120፥4፤ ዘፍ. 19፥24። የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፥
እንዳይነሡም ወደ እሳትና ወደ አዘቅት ይጣሉ።
12ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፥
ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።
13ጌታ ለድሀ ዳኝነትን
ለችግረኛም ፍርድን እንደሚያደርግ አወቅሁ።
14 # መዝ. 11፥7፤ 16፥11፤ 17፥15። ጻድቃንም በእውነት ስምህን ያመሰግናሉ፥
ቅኖችም በፊትህ ይኖራሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ