መዝሙረ ዳዊት 141
141
1የዳዊት መዝሙር።
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በፍጥነት ድረስልኝ፥
ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ድምፅ ስማ።
2 #
መዝ. 134፥2፤ ዘፀ. 30፥8። ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን፥
እጆቼን ማንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይሁን።
3 #
ሲራ. 22፥27። አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥
የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
4ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥
ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር
ለክፋት ምክንያት እንዳልሰጥ፥
ከድግሳቸውም አልቅመስ።
5 #
ምሳ. 9፥8፤ 25፥12። ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥
የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥
ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።
6አለቆቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፥
ጣፋጭ ናትና ቃሌን ይሰማሉ።
7በምድር ላይ እንደ ተሰነጠቀ እንደ መሬት ጓል፥
እንዲሁ አጥንቶቻችን በሲኦል ተበተኑ።
8 #
መዝ. 25፥15፤ 123፥1-2። አቤቱ ጌታ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፥
በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አትተዋት።
9 #
መዝ. 142፥4። ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥
ዓመፅንም ከሚያደርጉ ሰዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ።
10እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ
ክፉዎች በወጥመዳቸው ይውደቁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 141: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ