የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 142

142
1ጸሎት፥ በዋሻ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት ትምህርት።
2በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥
በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ለመንሁ።
3ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥
መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።
4 # መዝ. 139፥24፤ 141፥9፤ 143፥4። መንፈሴ በዛለ ጊዜ መንገዴን አወቅሁ፥
በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
5 # መዝ. 16፥8፤ 73፥23፤ 121፥5። ወደ ቀኝ ተመለከትሁ አየሁም፥
የሚያውቀኝም አጣሁ፥
መሸሸጊያም የለኝም፥ ስለ ነፍሴም የሚያስብ የለም።
6 # መዝ. 91፥2፤9፤ መዝ. 16፥5፤ 27፥13፤ 116፥9፤ ኢሳ. 38፥11። አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦
አንተ መጠጊያዬ ነህ፥
በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ።
7 # መዝ. 79፥8። እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥
በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
8አቤቱ፥ ስምህን አመሰግን ዘንድ
ነፍሴን ከወህኒ አውጣት፥
ስለ ምታጠግበኝ
ጻድቃን እኔን ይከባሉ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ