የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 105:1-15

መዝሙር 105:1-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኀይል ማን ይና​ገ​ራል? ምስ​ጋ​ና​ው​ንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደ​ር​ጋል? ፍር​ድን የሚ​ጠ​ብቁ፥ ጽድ​ቅ​ንም ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ብፁ​ዓን ናቸው። አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን በይ​ቅ​ር​ታህ ዐስ​በን፥ በማ​ዳ​ን​ህም ይቅር በለን፤ የመ​ረ​ጥ​ሃ​ቸ​ውን በጎ​ነት እናይ ዘንድ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከር​ስ​ት​ህም ጋር እን​ከ​ብር ዘንድ። ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ኃጢ​አት ሠራን፥ ዐመ​ፅ​ንም፥ በደ​ል​ንም። አባ​ቶ​ቻ​ችን በግ​ብፅ ሀገር ሳሉ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥ የም​ሕ​ረ​ት​ህ​ንም ብዛት አላ​ሰ​ቡም፤ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስ​መ​ረ​ሩህ። ኀይ​ሉን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳ​ና​ቸው። የኤ​ር​ት​ራ​ንም ባሕር ገሠ​ጻት፥ ደረ​ቀ​ችም፤ እንደ ምድረ በዳ በጥ​ልቅ መራ​ቸው። ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ና​ቸው፥ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተቤ​ዣ​ቸው። ያሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ው​ንም ውኃ ደፈ​ና​ቸው፥ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም። ያን​ጊ​ዜም በቃሉ አመኑ፥ በም​ስ​ጋ​ና​ውም አመ​ሰ​ገ​ኑት። ፈጥ​ነ​ውም ሥራ​ውን ረሱ፥ በም​ክ​ሩም አል​ጸ​ኑም። በም​ድረ በዳም ምኞ​ትን ተመኙ፥ በበ​ረ​ሃም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ኑት። የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን ላከ።

መዝሙር 105:1-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አሳውቁ። ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ ድንቅ ሥራዎቹንም ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ። እግዚአብሔርንና ብርታቱን ፈልጉ፤ ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ። ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤ እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣ ለራሱም የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ አስታውሱ። እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው። ኪዳኑን ለዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል። ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ አይረሳም። ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ፣ ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጎ አጸናለት፤ እንዲህም አለ፤ “የርስትህ ድርሻ አድርጌ፣ የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ።” ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣ በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣ ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ተንከራተቱ፣ ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”

መዝሙር 105:1-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ ያደረገውንም ሁሉ ለአሕዛብ ንገሩ። ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤ ያደረገውንም አስደናቂ ነገር ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ደስ ይበላችሁ! እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ሁሉ ሐሴት ያድርግ! በእግዚአብሔርና በኀያል ሥልጣኑ ተማመኑ፤ ዘወትርም እርሱን ፈልጉ። አገልጋዮች የሆናችሁ የእስራኤል ልጆች ሆይ! የእግዚአብሔር ምርጥ የሆናችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች፥ የሰጠውን ፍርድና ያደረጋቸውን ተአምራት አስታውሱ። እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በዓለም ሁሉ ነው። ቃል ኪዳኑን ወይም የሰጠውን ተስፋ እስከ ሺህ ትውልድም ሆነ ለዘለዓለም አይረሳም። ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ይጠብቃል፤ ለይስሐቅ የሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸናል። ለያዕቆብ ሥርዓት፥ ለእስራኤልም ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን አድርጎ አጸናው። ይህም ቃል ኪዳን “የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ፤ ለአንተም የተመደበ ርስት ይሆናል” የሚል ነው። ይህም የሆነው እነርሱ በቊጥር አነስተኞች ለሀገሩም እንግዶች ሆነው ሳለ ነው። ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላ ሕዝብ፥ ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ተንከራተቱ። እግዚአብሔር ግን ማንም እንዲጨቊናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ። “የተመረጡ አገልጋዮቼን አትንኩ፤ ነቢያቴንም አትጒዱ” በማለት አስጠነቀቃቸው።

መዝሙር 105:1-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሃሌ ሉያ! ጌታን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ድንቅ ሥራውን አውሩ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ክበሩ፥ ጌታን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። ጌታንና ኃይሉን ፈልጉ፥ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። አገልጋዮቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራውን ድንቅ ሥር አስቡ፥ ተአምራቱን የተናገረውንም ፍርድ። እርሱ ጌታ አምላካችን ነው፥ ፍርዱ በምድር ሁሉ ላይ ነው። ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥ እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥ ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ኪዳን፥ ለይስሐቅም የማለውን፥ ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን፥ ለእስራኤልም የዘለዓለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፥ እንዲህም አለ፦ ለአንተ የከነዓንን ምድር የተመደበላችሁን ርስታችሁን እሰጣለሁ፥ ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር አነስተኛና፥ ለሀገሩም እንግዶች በነበሩበት ጊዜ ነው። ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ። የቀባኋቸውን አትንኩ፥ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።

መዝሙር 105:1-15

መዝሙር 105:1-15 NASVመዝሙር 105:1-15 NASV