የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 105:1-15

መዝሙር 105:1-15 - እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አሳውቁ።
ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤
ድንቅ ሥራዎቹንም ሁሉ ተናገሩ።
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤
እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።
እግዚአብሔርንና ብርታቱን ፈልጉ፤
ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ።

ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣
ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤
እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣
ለራሱም የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ አስታውሱ።
እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤
ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው።

ኪዳኑን ለዘላለም፣
ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል።
ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣
ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ አይረሳም።
ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ፣
ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጎ አጸናለት፤
እንዲህም አለ፤ “የርስትህ ድርሻ አድርጌ፣
የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ።”

ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣
በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣
ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣
ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ተንከራተቱ፣
ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤
ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤
“የቀባኋቸውን አትንኩ፤
በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”

እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አሳውቁ። ተቀኙለት፤ ዘምሩለት፤ ድንቅ ሥራዎቹንም ሁሉ ተናገሩ። በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ። እግዚአብሔርንና ብርታቱን ፈልጉ፤ ፊቱንም ዘወትር ፈልጉ። ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤ እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣ ለራሱም የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ አስታውሱ። እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው። ኪዳኑን ለዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል። ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ አይረሳም። ይህንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ፣ ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አድርጎ አጸናለት፤ እንዲህም አለ፤ “የርስትህ ድርሻ አድርጌ፣ የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ።” ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣ በርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣ ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣ ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ተንከራተቱ፣ ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤ በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።”

መዝሙር 105:1-15