መዝሙረ ዳዊት 105
105
1 #
1ዜ.መ. 16፥8-22። ሃሌ ሉያ! ጌታን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥
ለአሕዛብም ድንቅ ሥራውን አውሩ።#መዝ. 18፥50፤ 96፥3፤ 145፥5፤ ኢሳ. 12፥4-5።
2ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥
ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
3በቅዱስ ስሙ ክበሩ፥
ጌታን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው።
4 #
መዝ. 24፥6፤ 27፥8። ጌታንና ኃይሉን ፈልጉ፥
ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
5-6አገልጋዮቹ የአብርሃም ዘር፥
ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥
የሠራውን ድንቅ ሥር አስቡ፥
ተአምራቱን የተናገረውንም ፍርድ።
7እርሱ ጌታ አምላካችን ነው፥
ፍርዱ በምድር ሁሉ ላይ ነው።
8ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥
እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፥
9 #
ዘፍ. 15፥1፤ 26፥3። ከአብርሃም ጋር ያደረገውን ኪዳን፥
ለይስሐቅም የማለውን፥
10ለያዕቆብ ሥርዓት እንዲሆን፥
ለእስራኤልም የዘለዓለም ኪዳን እንዲሆን አጸና፥
11 #
ዘፍ. 12፥7፤ 15፥18። እንዲህም አለ፦ ለአንተ የከነዓንን ምድር
የተመደበላችሁን ርስታችሁን እሰጣለሁ፥
12 #
ዘዳ. 4፥27፤ 26፥5። ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር አነስተኛና፥
ለሀገሩም እንግዶች በነበሩበት ጊዜ ነው።
13ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥
ከመንግሥታትም ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
14-15የቀባኋቸውን አትንኩ፥
በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ ብሎ፥
ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፥
ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።
16 #
ዘፍ. 41፥54፤57። በምድር ላይ ራብን ጠራ፥
የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።
17 #
ዘፍ. 37፥28፤36፤ 45፥5። በፊታቸው ሰውን ላከ፥
ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ።
18 #
ዘፍ. 39፥20። እግሮቹም በእግር ብረት ደከሙ፥
እርሱም በብረት ውስጥ ገባ።
19 #
ዘፍ. 40—41። ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥
የጌታ ቃል ፈተነው።
20 #
ዘፍ. 41፥14። ንጉሥ#105፥20 የግብጽ ንጉሥ ላከና ፈታው፥
የአሕዛብም አለቃ አስፈታው።
21 #
ዘፍ. 41፥41-44። የቤቱ ጌታ፥
የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፥
22መኰንኖቹን እንደ ፈቃዱ ይገሥጽ ዘንድ፥
ሽማግሌዎቹንም ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
23 #
ዘፍ. 46፥1—47፥12፤ የሐዋ. 7፥15። እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥
ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።
24 #
ዘፀ. 1፥7፤ የሐዋ. 7፥17። ሕዝቡንም እጅግ አበዛ፥
ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።
25 #
ዘፀ. 1፥8-14። ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ
በአገልጋዮቹም ላይ ተንኰል ይፈጽሙ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።
26 #
ዘፀ. 3፥10፤ 4፥27። አገልጋዩን ሙሴን
የመረጠውንም አሮንን ላከ።
27 #
መዝ. 78፥43-51፤ ዘፀ. 7—12። ተኣምራቱን በላያቸው
ድንቁንም በካም አገር አደረጉ።
28ጨለማን ላከ፥ ጨለመባቸውም፥
በቃሉም ዐመፁ#105፥28 ዕብራይስጡ “አላመፁም” ይላል። እንዲህ ከተነበበ፥ ሙሴንና አሮንን እንደባለቤት መቁጠር ያስፈልጋል።።
29ውኃቸውን ወደ ደም ለወጠ፥
ዓሦቻቸውንም ገደለ።
30ምድራቸውና የንጉሦቻቸው ቤቶች
በእንቁራሪት ተሞሉ።
31ተናገረ፥ የዝንብ መንጋና
ተናካሽ ትንኞች በዳርቻቸው መጡ።
32ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥
በምድራቸውም የእሳት ነበልባል ወረደ#105፥32 መብረቅ ጣለ።።
33ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥
የአገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
34 #
ኢዩ. 1፥4። ተናገረ፥ አንበጣም
ስፍር ቍጥር የሌለውም ኩብኩባ መጣ፥
35የአገራቸውንም ተክሎች ሁሉ በላ፥
የምድራቸውንም ፍሬ በላ።
36 #
ዘፀ. 12፥29። የአገራቸውንም በኩር ሁሉ፥
የጉልበታቸውን መጀመሪያ ሁሉ መታ።
37 #
ዘፀ. 12፥33-36። ከወርቅና ከብርም ጋር አወጣቸው፥
በወገናቸውም ውስጥ የተደናቀፈ አልነበረም።
38ፈርተዋቸው ነበርና
ግብጽ በመውጣታቸው ደስ አላት።
39 #
መዝ. 78፥14፤ ዘፀ. 13፥21-22፤ ጥበ. 18፥3። ደመናን ለመሸፈኛ ዘረጋባቸው፥
እሳትንም በሌሊት እንዲያበራላቸው።
40 #
መዝ. 78፥24-28፤ ዘፀ. 16፥13-15፤ ዘኍ. 11፥31፤ ጥበ. 16፥20። ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥
የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
41 #
መዝ. 78፥15-16፤ ዘፀ. 17፥1-7፤ ዘኍ. 20፥11። ዓለቱን ሰነጠቀ፥ ውኃውም ፈለቀ፥
ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ፥
42ለአገልጋዩ ለአብርሃም የነገረውን
ቅዱስ ቃሉን አስታውሶአልና።
43ሕዝቡንም በደስታ
የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ።
44 #
ዘዳ. 4፥37-40። የአሕዛብንም አገሮች ሰጣቸው፥
ከሕዝቦችም ድካም ወረሱ፥
45 #
ዘዳ. 6፥20-25፤ 7፥8-11። ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥
ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 105: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ