ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ። የእግዚአብሔርን ኀይል ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል? ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው። አቤቱ፥ ሕዝብህን በይቅርታህ ዐስበን፥ በማዳንህም ይቅር በለን፤ የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥ በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከርስትህም ጋር እንከብር ዘንድ። ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአት ሠራን፥ ዐመፅንም፥ በደልንም። አባቶቻችን በግብፅ ሀገር ሳሉ ተአምራትህን አላስተዋሉም፥ የምሕረትህንም ብዛት አላሰቡም፤ በኤርትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስመረሩህ። ኀይሉን ያሳያቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳናቸው። የኤርትራንም ባሕር ገሠጻት፥ ደረቀችም፤ እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው። ከጠላቶቻቸውም እጅ አዳናቸው፥ ከጠላቶቻቸውም እጅ ተቤዣቸው። ያሳደዱአቸውንም ውኃ ደፈናቸው፥ ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልቀረም። ያንጊዜም በቃሉ አመኑ፥ በምስጋናውም አመሰገኑት። ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልጸኑም። በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን አሳዘኑት። የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳችውም ጥጋብን ላከ።
መዝሙረ ዳዊት 105 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 105:1-15
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos