የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 105

105
ሃሌ ሉያ።
1ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ።
2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኀይል ማን ይና​ገ​ራል?
ምስ​ጋ​ና​ው​ንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደ​ር​ጋል?
3ፍር​ድን የሚ​ጠ​ብቁ፥
ጽድ​ቅ​ንም ሁል​ጊዜ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ብፁ​ዓን ናቸው።
4አቤቱ፥ ሕዝ​ብ​ህን በይ​ቅ​ር​ታህ#ዕብ. “በሕ​ዝ​ብህ ሞገስ” ይላል። ዐስ​በን፥
በማ​ዳ​ን​ህም ይቅር በለን፤
5የመ​ረ​ጥ​ሃ​ቸ​ውን በጎ​ነት እናይ ዘንድ፥
በሕ​ዝ​ብ​ህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥
ከር​ስ​ት​ህም ጋር እን​ከ​ብር ዘንድ።
6ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ኃጢ​አት ሠራን፥
ዐመ​ፅ​ንም፥ በደ​ል​ንም።
7አባ​ቶ​ቻ​ችን በግ​ብፅ ሀገር ሳሉ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥
የም​ሕ​ረ​ት​ህ​ንም ብዛት አላ​ሰ​ቡም፤
በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስ​መ​ረ​ሩህ።#ዕብ. “ዐመ​ፁ​ብህ” ይላል።
8ኀይ​ሉን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ
ስለ ስሙ አዳ​ና​ቸው።
9የኤ​ር​ት​ራ​ንም ባሕር ገሠ​ጻት፥ ደረ​ቀ​ችም፤
እንደ ምድረ በዳ በጥ​ልቅ መራ​ቸው።
10ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ና​ቸው፥
ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተቤ​ዣ​ቸው።
11ያሳ​ደ​ዱ​አ​ቸ​ው​ንም ውኃ ደፈ​ና​ቸው፥
ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ አል​ቀ​ረም።
12ያን​ጊ​ዜም በቃሉ አመኑ፥
በም​ስ​ጋ​ና​ውም አመ​ሰ​ገ​ኑት።
13ፈጥ​ነ​ውም ሥራ​ውን ረሱ፥
በም​ክ​ሩም አል​ጸ​ኑም።
14በም​ድረ በዳም ምኞ​ትን ተመኙ፥
በበ​ረ​ሃም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ኑት።
15የለ​መ​ኑ​ት​ንም ሰጣ​ቸው፤
ለነ​ፍ​ሳ​ች​ውም ጥጋ​ብን#ዕብ. “ክዳ​ትን” ይላል። ላከ።
16ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም
በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።
17ምድር ተከ​ፈ​ተች፥ ዳታ​ን​ንም ዋጠ​ችው፥
የአ​ቤ​ሮ​ን​ንም ወገን ደፈ​ነች፤
18በማ​ኅ​በ​ራ​ቸው እሳት ነደ​ደች፥
ነበ​ል​ባ​ልም ኃጥ​ኣ​ንን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።
19በኮ​ሬ​ብም ጥጃን ሠሩ፥
ቀልጦ ለተ​ሠራ ምስ​ልም ሰገዱ።
20ሣር​ንም በሚ​በላ በበሬ ምሳሌ
ክብ​ራ​ቸ​ውን ለወጡ።
21ያዳ​ና​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረሱ።
ታላቅ ነገ​ር​ንም በግ​ብፅ፥
22ድን​ቅ​ንም በካም ምድር፥
ግሩም ነገ​ር​ንም በኤ​ር​ትራ ባሕር ያደ​ረ​ገ​ውን።
23እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ልስ ዘንድ
የተ​መ​ረ​ጠው ሙሴ በመ​ቅ​ሠ​ፍት ጊዜ በፊቱ ባይ​ቆም ኖሮ፥
ባጠ​ፋ​ቸው ነበር አለ።
24የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ው​ንም ምድር ናቁ፥
በቃ​ሉም አል​ታ​መ​ኑም፥
25በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ውስጥ አን​ጐ​ራ​ጐሩ፤
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙም።
26እጁ​ንም አነ​ሣ​ባ​ቸው።
በም​ድረ በዳ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ፥
27ዘራ​ቸ​ው​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይጥል ዘንድ፥
በየ​ሀ​ገ​ሩም ይበ​ት​ና​ቸው ዘንድ።
28በብ​ዔል ፌጎ​ርም ዐለቁ፥#ዕብ. “ተባ​በሩ” ይላል።
የሞተ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም በሉ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሙ​ታን መሥ​ዋ​ዕ​ትን በሉ” ይላል።
29በሥ​ራ​ቸ​ውም አነ​ሣ​ሱት
ቸነ​ፈ​ርም በላ​ያ​ቸው በዛ።
30ፊን​ሐ​ስም ተነ​ሥቶ አዳ​ና​ቸው፥
ቸነ​ፈ​ሩም ተወ።
31ያም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት።
32በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም አስ​ቈ​ጡት፥
ስለ እነ​ር​ሱም ሙሴ ተበ​ሳጨ፤
33መን​ፈ​ሱን አስ​መ​ር​ረ​ዋ​ታ​ልና፤
በከ​ን​ፈ​ሮ​ቹም አዘዘ።
34እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ላ​ቸው አሕ​ዛ​ብን አላ​ጠ​ፉም፤
35ከአ​ሕ​ዛብ ጋር ተደ​ባ​ለቁ፥ ሥራ​ቸ​ው​ንም ተማሩ።
36ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ተገዙ፥ በደ​ልም ሆነ​ባ​ቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወጥ​መ​ድም ሆኑ​ባ​ቸው” ይላል።
37ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ጋ​ን​ንት ሠዉ፤
38ንጹሕ ደም​ንም አፈ​ሰሱ፥
የወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ደም፥
ለከ​ነ​ዓን ጣዖ​ቶች ሠዉ፥
ምድ​ርም በደም ታለ​ለች።
39በሥ​ራ​ቸ​ውም ረከ​ሰች፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ረከሱ” ይላል።
በጣ​ዖ​ታ​ቸ​ውም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሥ​ራ​ቸ​ውም” ይላል። አመ​ነ​ዘሩ።
40እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥
ርስ​ቱ​ንም ተጸ​የፈ።
41በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።
የሚ​ጠ​ሉ​አ​ቸ​ውም ገዙ​አ​ቸው።
42ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው፥
ከእ​ጃ​ቸ​ውም በታች ተዋ​ረዱ።
43ብዙ ጊዜ አዳ​ና​ቸው፤
እነ​ርሱ ግን በም​ክ​ራ​ቸው አስ​መ​ረ​ሩት፥
በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም መከራ ተቀ​በሉ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተዋ​ረዱ” ይላል።
44እንደ ተጨ​ነ​ቁም ተመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፥
ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰማ​ቸው፤
45ለእ​ነ​ር​ሱም ኪዳ​ኑን አሰበ፥
እንደ ምሕ​ረ​ቱም ብዛት አዘ​ነ​ላ​ቸው።
46በማ​ረ​ኩ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ፊት ይቅ​ር​ታን ሰጣ​ቸው።
47አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አድ​ነን፤
ቅዱስ ስም​ህን እና​መ​ሰ​ግን ዘንድ፥
በም​ስ​ጋ​ና​ህም እን​መካ ዘንድ፥
ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ሰብ​ስ​በን።
48ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም
የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤
ሕዝ​ቡም ሁሉ ይሁን ይሁን ይበል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}