የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 106

106
ሃሌ ሉያ።
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤
ቸር ነውና፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና።
2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዳ​ና​ቸው፥
ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ያዳ​ና​ቸው ይና​ገሩ።
3ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ፥ ከመ​ስ​ዕና ከባ​ሕር፥
ከየ​ሀ​ገሩ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።
4ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤
የሚ​ኖ​ሩ​በ​ት​ንም ከተማ መን​ገድ አላ​ገ​ኙም።
5ተራቡ፥ ተጠ​ሙም፥
ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው አለ​ቀች።
6በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥
ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው፤
7ወደ​ሚ​ኖ​ሩ​በ​ትም ሀገር ይሄዱ ዘንድ
የቀና መን​ገ​ድን መራ​ቸው።
8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት
ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤
9የተ​ራ​በ​ችን ነፍስ አጥ​ግ​ቦ​አ​ልና፥
የተ​ራ​ቈ​ተ​ች​ንም ነፍስ በበ​ረ​ከት ሞል​ቶ​አ​ልና።
10በጨ​ለ​ማና በሞ​ትም ጥላ የተ​ቀ​መጡ፥
በች​ግር በብ​ረ​ትም የታ​ሰሩ፥
11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ አማ​ረሩ፥
የል​ዑ​ል​ንም ምክር ስለ አስ​ቈጡ፥
12ልባ​ቸው በመ​ከራ ደከመ፤
ታመሙ የሚ​ረ​ዳ​ቸ​ው​ንም#ግእዝ “የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው” ይላል። አጡ።
13በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥
ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።
14ከጨ​ለ​ማና ከሞት ጥላ አወ​ጣ​ቸው፥
እግር ብረ​ታ​ቸ​ው​ንም ሰበረ።
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት
ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤
16የና​ሱን ደጆች ሰብ​ሮ​አ​ልና፥
የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ ቀጥ​ቅ​ጦ​አ​ልና።
17ከበ​ደ​ላ​ቸው ጎዳና ተቀ​በ​ላ​ቸው፥#ዕብ. “ስለ ዐመ​ፃ​ቸው ሰነፉ” ይላል።
በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ተሠ​ቃ​ይ​ተ​ዋ​ልና።
18ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም መብ​ልን ሁሉ ተጸ​የ​ፈች፥
ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
19በተ​ጨ​ነ​ቁም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥
ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።
20ቃሉን ልኮ ፈወ​ሳ​ቸው፥
ከጥ​ፋ​ታ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።
21የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት
ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤
22የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትም ይሠ​ዉ​ለት፥
በደ​ስ​ታም ሥራ​ውን ይን​ገሩ።
23በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥
በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥
24እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥
በጥ​ል​ቅም ያለ​ች​ውን ድን​ቁን ዐወቁ።
25ተና​ገረ፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ተነሣ፥
ሞገ​ድም ከፍ ከፍ አለ።
26ወደ ሰማይ ይወ​ጣሉ፥ ወደ ጥል​ቅም ይወ​ር​ዳሉ፤
ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውም በመ​ከራ ቀለ​ጠች።
27ደነ​ገጡ፥ እንደ ሰካ​ራ​ምም ተን​ገ​ዳ​ገዱ፥
ጥበ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ተዋጠ።
28በተ​ጨ​ነቁ ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፥
ከመ​ከ​ራ​ቸ​ውም አዳ​ና​ቸው።
29ዐውሎ ነፋ​ሱ​ንም ጸጥ አደ​ረገ፥
ባሕ​ሩም ዝም አለ።
30ማዕ​በ​ሉም ዝም አለ፥ አር​ፈ​ዋ​ልና ደስ አላ​ቸው።
ወደ ፈለ​ጉ​ትም ወደብ መራ​ቸው።
31የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረ​ቱን
ለሰው ልጆ​ችም ድን​ቁን ንገሩ።
32በአ​ሕ​ዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጉ​ታል፥
በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ሸንጎ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
33ወን​ዞ​ችን ምድረ በዳ አደ​ረገ፥
የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ደረቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤
34በተ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ክፋት
ፍሬ​ያ​ማ​ዋን ምድር ጨው አደ​ረ​ጋት።
35ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መው​ረጃ፥
ደረ​ቁ​ንም ምድር የውኃ ምን​ጮች አደ​ረገ።
36በዚ​ያም ራብ​ተ​ኞ​ችን አስ​ቀ​መጠ፥
የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሠሩ።
37እር​ሻ​ዎ​ች​ንም ዘሩ፥ ወይ​ኖ​ች​ንም ተከሉ፥
የእ​ህ​ል​ንም ሰብል አደ​ረጉ።
38ባረ​ካ​ቸ​ውም፥ እጅ​ግም በዙ፤
እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አላ​ሳ​ነ​ሰ​ባ​ቸ​ውም።
39እነ​ርሱ በክፉ መከ​ራና በጭ​ን​ቀት ተሠ​ቃዩ፥ እያ​ነ​ሱም ሄዱ፤
40በአ​ለ​ቆ​ችም ላይ ኀሣር ፈሰሰ፥
መን​ገ​ድም በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ አሳ​ታ​ቸው።
41ችግ​ረ​ኛ​ንም በች​ግሩ ረዳው፤
እንደ ሀገር በጎች አደ​ረ​ገው።#ዕብ. “እንደ በጎች መንጋ” ይላል።
42ቅኖች ይዩ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤
ዐመ​ፃም ሁሉ አፍ​ዋን ትዘ​ጋ​ለች።
43ይህን የሚ​ጠ​ብቅ ጥበ​በኛ ማን ነው?
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይ እንደ ሆነ ያው​ቃል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ