መዝሙረ ዳዊት 105
105
ሃሌ ሉያ።
1ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና
እግዚአብሔርን አመስግኑ።
2የእግዚአብሔርን ኀይል ማን ይናገራል?
ምስጋናውንስ ሁሉ ይሰማ ዘንድ ማን ያደርጋል?
3ፍርድን የሚጠብቁ፥
ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው።
4አቤቱ፥ ሕዝብህን በይቅርታህ#ዕብ. “በሕዝብህ ሞገስ” ይላል። ዐስበን፥
በማዳንህም ይቅር በለን፤
5የመረጥሃቸውን በጎነት እናይ ዘንድ፥
በሕዝብህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥
ከርስትህም ጋር እንከብር ዘንድ።
6ከአባቶቻችን ጋር ኃጢአት ሠራን፥
ዐመፅንም፥ በደልንም።
7አባቶቻችን በግብፅ ሀገር ሳሉ ተአምራትህን አላስተዋሉም፥
የምሕረትህንም ብዛት አላሰቡም፤
በኤርትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስመረሩህ።#ዕብ. “ዐመፁብህ” ይላል።
8ኀይሉን ያሳያቸው ዘንድ
ስለ ስሙ አዳናቸው።
9የኤርትራንም ባሕር ገሠጻት፥ ደረቀችም፤
እንደ ምድረ በዳ በጥልቅ መራቸው።
10ከጠላቶቻቸውም እጅ አዳናቸው፥
ከጠላቶቻቸውም እጅ ተቤዣቸው።
11ያሳደዱአቸውንም ውኃ ደፈናቸው፥
ከእነርሱም አንድ ስንኳ አልቀረም።
12ያንጊዜም በቃሉ አመኑ፥
በምስጋናውም አመሰገኑት።
13ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥
በምክሩም አልጸኑም።
14በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥
በበረሃም እግዚአብሔርን አሳዘኑት።
15የለመኑትንም ሰጣቸው፤
ለነፍሳችውም ጥጋብን#ዕብ. “ክዳትን” ይላል። ላከ።
16ሙሴንም፥ እግዚአብሔር የቀደሰውን አሮንንም
በሰፈር አስቈጧቸው።
17ምድር ተከፈተች፥ ዳታንንም ዋጠችው፥
የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤
18በማኅበራቸው እሳት ነደደች፥
ነበልባልም ኃጥኣንን አቃጠላቸው።
19በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥
ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
20ሣርንም በሚበላ በበሬ ምሳሌ
ክብራቸውን ለወጡ።
21ያዳናቸውን እግዚአብሔርን ረሱ።
ታላቅ ነገርንም በግብፅ፥
22ድንቅንም በካም ምድር፥
ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን።
23እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ
የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥
ባጠፋቸው ነበር አለ።
24የተወደደችውንም ምድር ናቁ፥
በቃሉም አልታመኑም፥
25በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፤
የእግዚአብሔርንም ቃል አልሰሙም።
26እጁንም አነሣባቸው።
በምድረ በዳ ይጥላቸው ዘንድ፥
27ዘራቸውንም በአሕዛብ መካከል ይጥል ዘንድ፥
በየሀገሩም ይበትናቸው ዘንድ።
28በብዔል ፌጎርም ዐለቁ፥#ዕብ. “ተባበሩ” ይላል።
የሞተ መሥዋዕትንም በሉ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሙታን መሥዋዕትን በሉ” ይላል።
29በሥራቸውም አነሣሱት
ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
30ፊንሐስም ተነሥቶ አዳናቸው፥
ቸነፈሩም ተወ።
31ያም እስከ ዘለዓለም ለልጅ ልጅ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።
32በክርክር ውኃ ዘንድም አስቈጡት፥
ስለ እነርሱም ሙሴ ተበሳጨ፤
33መንፈሱን አስመርረዋታልና፤
በከንፈሮቹም አዘዘ።
34እግዚአብሔርም እንዳላቸው አሕዛብን አላጠፉም፤
35ከአሕዛብ ጋር ተደባለቁ፥ ሥራቸውንም ተማሩ።
36ለጣዖቶቻቸውም ተገዙ፥ በደልም ሆነባቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወጥመድም ሆኑባቸው” ይላል።
37ወንዶች ልጆቻቸውንና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንት ሠዉ፤
38ንጹሕ ደምንም አፈሰሱ፥
የወንዶች ልጆቻቸውንና የሴቶች ልጆቻቸውን ደም፥
ለከነዓን ጣዖቶች ሠዉ፥
ምድርም በደም ታለለች።
39በሥራቸውም ረከሰች፥#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ረከሱ” ይላል።
በጣዖታቸውም#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሥራቸውም” ይላል። አመነዘሩ።
40እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥
ርስቱንም ተጸየፈ።
41በጠላቶቻቸውም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
የሚጠሉአቸውም ገዙአቸው።
42ጠላቶቻቸውም አሠቃዩአቸው፥
ከእጃቸውም በታች ተዋረዱ።
43ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤
እነርሱ ግን በምክራቸው አስመረሩት፥
በኀጢአታቸውም መከራ ተቀበሉ።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ተዋረዱ” ይላል።
44እንደ ተጨነቁም ተመለከታቸው፥
ጸሎታቸውንም ሰማቸው፤
45ለእነርሱም ኪዳኑን አሰበ፥
እንደ ምሕረቱም ብዛት አዘነላቸው።
46በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ይቅርታን ሰጣቸው።
47አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፥ አድነን፤
ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥
በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥
ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።
48ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤
ሕዝቡም ሁሉ ይሁን ይሁን ይበል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 105: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ