መዝሙረ ዳዊት 104
104
ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ስሙንም ጥሩ፥
ለአሕዛብም ሥራውን ንገሩ።
2ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥
ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።
3በቅዱስ ስሙም ትከብራላችሁ።
4እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው፤
እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤
ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
5የሠራውን ድንቅ ዐስቡ፥
ተአምራቱን፥ የአፉንም ፍርድ።
6ባሪያዎቹ የአብርሃም ዘር፥
ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥
7እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤
ፍርዱ በምድር ሁሉ ነው።
8ለዘለዓለም የሚኖር ቃል ኪዳኑን፥
እስከ ሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን ዐሰበ።
9ለአብርሃም የሠራለትን፥
ለይስሐቅም የማለውን፤
10ለያዕቆብ ምስክርነትን አጸና።
11ለእስራኤልም ለዘለዓለም የሚኖር ኪዳኑን፤
እንዲህም አለው፥ “ለአንተ የከነዓንን ምድር፥
የርስታችሁ ገመድ ትሆናችሁ ዘንድ እሰጣለሁ፤”
12እነርሱ በቍጥር እጅግ ጥቂቶችና፥
በውስጧ ስደተኞች ሲሆኑ።
13ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥
ከነገሥታት#ዕብ. “ከመንግሥታት” ይላል። ወደ ሌላ ሕዝብ አለፉ።
14ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልተወም፥
ስለ እነርሱም ነገሥታቱን ገሠጸ።
15የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥
በነቢያቴም ላይ ክፉ አታድርጉ።
16በምድር ላይ ራብን አመጣ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጠራ” ይላል።
የእህልን ኀይል ሁሉ አጠፋ።#ዕብ. “ሰበረ” ይላል።
17በፊታቸው ሰውን ላከ፤
ዮሴፍ ተሸጠ፥ አገልጋይም ሆነ።
18እግሮቹም በእግር ብረት ሰለሰሉ፥
ሰውነቱም ከብረት አመለጠች።#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰውነቱም በብረት ውስጥ ገባች” ይላል።
19ቃሉ ሳይደርስ፥#ዕብ. “እስኪመጣለት” ይላል።
የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።
20ንጉሥ ላከ፥ ፈታውም፥
የሕዝብም አለቃ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አስፈታው” ይላል። አድርጎ ሾመው።
21የቤቱ ጌታም አደረገው፥
በገንዘቡ ሁሉ ላይ ገዢ አደረገው፥
22አለቆቹን ሁሉ እንደ እርሱ ይገሥጽ ዘንድ፥
ሽማግሌዎቹንም እንደ እርሱ ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ።
23እስራኤልም ወደ ግብፅ ገባ፥
ያዕቆብም በካም ምድር ተቀመጠ።
24ሕዝቡንም እጅግ አበዛቸው፥
ከጠላቶቻቸውም ይልቅ አበረታቸው።
25ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ
በባሪያዎቹም ላይ ይተነኰሉ ዘንድ ልባቸውን ለወጠ።
26ባሪያውን ሙሴን፥
የመረጠውንም አሮንን ላከ።
27የተአምራቱን ቃል በላያቸው
ድንቁንም በካም ምድር አደረገ።
28ጨለማንም ላከ ጨለመባቸውም፤
ቃሉንም መራራ አደረጉት።
29ውኃቸውን ደም አደረገ፥
ዓሦቻቸውንም ገደለ።
30ምድራቸው በንጉሦቻቸው ቤቶች
ጓጕንቸሮችን አወጣች።
31እርሱ ተናገረ፥ የውሻ ዝንብ
ትንኝም በምድራቸው ሁሉ መጡ።
32ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥
እሳትም በምድራቸው ነደደ።
33ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥
የሀገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
34ተናገረ፥ አንበጣም፥
ስፍር ቍጥር የሌለውም ኵብኵባ መጣ፥
35የምድራቸውንም ፍሬ ሁሉ በላ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሀገራቸውንም ልምላሜ በላ” ብሎ ይጨምራል።
የተግባራቸውን ሁሉ መጀመሪያ በላ፥
36የሀገራቸውንም በኵር ሁሉ ገደለ።
37ከወርቅና ከብር ጋርም አወጣቸው፥
በወገናቸውም ውስጥ ደዌ አልነበረም።
38ፈርተዋቸው ነበርና
ግብፅ በመውጣታቸው ደስ አላቸው።
39ደመናን ጋርዶ ሰወራቸው።
እሳትንም በሌሊት ያበራላቸው ዘንድ ዘረጋ።
40ለመኑ፥ ድርጭትም መጣ፥
የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
41ዓለቱን ሰነጠቀ ውኃንም አመነጨ፤
በበረሃ ወንዞች ውስጥ ሄዱ፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወንዞች በበረሃ ፈሰሱ” ይላል።
42ለባሪያው ለአብርሃም የነገረውን
ቅዱስ ቃሉን ዐስቦአልና።
43ሕዝቡንም በደስታ
የመረጣቸውንም በሐሤት አወጣ።
44የአሕዛብንም ሀገሮች ሰጣቸው፥
የባዕድን#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሕዝብን” ይላል። ድካም ወረሱ፥
45ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥
ሥርዐቱንም ይፈልጉ ዘንድ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 104: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ