ነህምያ 8:3-10

ነህምያ 8:3-10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በው​ኃ​ውም በር ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ላይ ቆሞ፥ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች በሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ፊት፥ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ጆሮ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ለመ​ስ​ማት ያደ​ምጥ ነበር። ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር። ዕዝ​ራም የሕ​ዝቡ ሁሉ የበ​ላይ ነበ​ረና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት መጽ​ሐ​ፉን ገለጠ፤ በገ​ለ​ጠ​ውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝ​ራም ታላ​ቁን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን እየ​ዘ​ረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳ​ቸ​ው​ንም አዘ​ነ​በሉ፤ በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደ ምድር ተደ​ፍ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ። ደግሞ ኢያ​ሱና ባኒ፥ ሰራ​ብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባ​ታይ፥ ሆዲያ፥ መዕ​ሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሐናን፥ ፌል​ዕያ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ሕጉን ለሕ​ዝቡ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ቆመው ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕግ መጽ​ሐፍ አነ​በቡ፤ ዕዝ​ራም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማወቅ ያስ​ተ​ም​ርና ያስ​ታ​ውቅ ነበር፤ ሕዝ​ቡም የሚ​ነ​በ​በ​ውን ያስ​ተ​ውሉ ነበር። ሕቴ​ር​ሰታ ነህ​ም​ያም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝ​ቡ​ንም የሚ​ያ​ስ​ተ​ምሩ ሌዋ​ው​ያን ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ አት​ዘኑ፤ አታ​ል​ቅ​ሱም” አሉ​አ​ቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕ​ጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለ​ቅሱ ነበ​ርና። እር​ሱም፥ “ሂዱ፤ የሰ​ባ​ው​ንም ብሉ፤ ጣፋ​ጩ​ንም ጠጡ፤ ለእ​ነ​ዚ​ያም ምንም ለሌ​ላ​ቸው እድል ፈን​ታ​ቸ​ውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌ​ታ​ችን የተ​ቀ​ደሰ ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይ​ላ​ችን ነውና አት​ዘኑ” አላ​ቸው።

ነህምያ 8:3-10 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እርሱም በውሃ በር ትይዩ ወደሚገኘው አደባባይ ፊቱን አቅንቶ፣ በወንዶች፣ በሴቶችና በሚያስተውሉ ሰዎች ሁሉ ፊት በመቆም፣ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ ድምፁን ከፍ አድርጎ አነበበ፤ ሕዝቡም ሁሉ የሕጉን መጽሐፍ በጥሞና አደመጡ። ጸሓፊው ዕዝራ ለዚሁ ተብሎ በተሠራውና ከፍ ብሎ በሚገኘው የዕንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡም በስተ ቀኙ በኩል መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ፣ መዕሤያ፣ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳና፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር። ዕዝራም መጽሐፉን ከፈተ፤ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ ቆሞ ስለ ነበረ፣ ሁሉም ያዩት ነበረ፣ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በማንሣት፣ “አሜን! አሜን!” ብለው መለሱ፤ ከዚህ በኋላ በግምባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን፣ ፌልያ ሕዝቡ በዚያው ቆመው እንዳሉ ሕጉን አስረዷቸው። ሕዝቡ የሚነበበውን ማስተዋል እንዲችሉ ከእግዚአብሔር ሕግ መጽሐፍ ካነበቡላቸው በኋላ ይተረጕሙላቸውና ይተነትኑላቸው ነበር። ከዚያም አገረ ገዥው ነህምያ፣ ካህኑና ጸሓፊው ዕዝራ፣ ሕዝቡንም የሚያስተምሩት ሌዋውያን፣ “ይህች ቀን ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት፤ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሏቸው፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሚሰሙበት ጊዜ ያለቅሱ ነበር። ነህምያም፣ “ሂዱ፤ ጥሩ ምግብ በመብላት፣ ጣፋጩን በመጠጣት ደስ ይበላችሁ፤ ምንም የተዘጋጀ ነገር ለሌላቸውም ካላችሁ ላይ ከፍላችሁ ላኩላቸው። ይህች ቀን ለጌታችን የተቀደሰች ናት፤ የእግዚአብሔር ደስታ ብርታታችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።

ነህምያ 8:3-10 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶችና ሴቶች የሚያስተውሉም ሲሰሙ፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፥ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር። ጸሐፊውም ዕዝራ ስለዚህ ነገር በተሠራ በእንጨት መረባርብ ላይ ቆሞ ነበር፥ በአጠገቡ መቲትያ፥ ሽማዕ፥ ዓናያ፥ ኦርዮ፥ ኬልቅያስ፥ መዕሤያ በቀኙ በኩል፥ ፈዳያ፥ ሚሳኤል፥ መልክያ፥ ሐሱም፥ ሐሽበዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላም በግራው በኩል ቆመው ነበር። ዕዝራም በሕዝቡ ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ መጽሐፉን ገለጠ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥ ሰራብያ፥ ያሜን፥ ዓቁብ፥ ሳባታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቆሊጣስ፥ ዓዛርያስ፥ ዮዛባት፥ ሐናን፥ ፌልያ፥ ሌዋውያኑም ሕጉን ያስተውሉ ዘንድ ሕዝቡን ያስተምሩ ነበር፥ ሕዝቡም በየስፍራቸው ቆመው ነበር። የእግዚአብሔርንም ሕግ መጽሐፍ አነበቡ፥ ዕዝራም እግዚአብሔርን ማወቅ ያስተምርና ያስታውቅ ነበር፥ ሕዝቡም የሚነበበውን ያስተውሉ ነበር። ሐቴርሰታ ነህምያም ጸሐፊውም ካህኑ ዕዝራ ሕዝቡንም የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ ዛሬ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ነው፥ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ አሉአቸው፥ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና። እርሱም፦ ሂዱ፥ የሰባውንም ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያም ላልተዘጋጀላቸው እድል ፈንታቸውን ስደዱ፥ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፥ የእግዚአብሔርም ደስታ ኃይላችሁ ነውና አትዘኑ አላቸው።

ነህምያ 8:3-10 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚያም አደባባይ ዕዝራ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ከንጋት እስከ ቀትር የሕጉን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ አነበበላቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ሁሉ በከፍተኛ ስሜት አዳመጡት። የሕግ ምሁሩ ዕዝራ ለዚሁ ተግባር አመች ይሆን ዘንድ ከዕንጨት በተሠራ መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር በስተቀኙ በኩል የቆሙት ሰዎች ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቂያና መዕሤያ ሲሆኑ፥ በስተ ግራው በኩል ደግሞ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳናህ፥ ዘካርያስና መሹላም ቆመው ነበር። ዕዝራ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ በተሠራው መድረክ ላይ በቆመ ጊዜ፥ ሁሉም ትኲር ብለው ይመለከቱት ነበር፤ እርሱም የሕጉን መጽሐፍ በከፈተ ጊዜ፥ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሡ፤ ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ሁሉም እጆቻቸውን ወደ ላይ በማንሣት “አሜን! አሜን!” ሲሉ መለሱ፤ ወደ ምድርም ለጥ ብለው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። ከዚህ በኋላ ተነሥተው ባሉበት ስፍራ ቆሙ፤ ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተዘረዘረ ሌዋውያንም የሕጉን መጽሐፍ ትርጒም ለሕዝቡ አብራሩላቸው፤ እነርሱም ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻበታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቀሊጣ፥ ዐዛርያስ፥ ዮዛባድ፥ ሐናንና ፐላያ ነበሩ። እነርሱም ለሕዝቡ የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አነበቡለት፤ ሕዝቡም የሚነበበው ይገባው ዘንድ ያብራሩለት ነበር። የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ሰዎቹ ስላለቀሱ፥ አገረ ገዢው ነህምያ፥ ካህኑና የሕግ ምሁሩ ዕዝራ፥ ሕዝቡን ያስተምሩ የነበሩት ሌዋውያን “ይህ ቀን ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ስለ ሆነ፥ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሉአቸው። ነህምያ፦ “ሂዱና ምርጡን ምግብ ብሉ፤ ጣፋጩን መጠጥ ጠጡ፤ ምንም ለሌላቸውም ላኩ፤ ይህ ቀን ለአምላካችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ደስታ ኀይላችሁ ስለ ሆነ አትዘኑ” አላቸው።

ነህምያ 8:3-10 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በውኃው በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶች፥ ሴቶች፥ የሚያስተውሉም ባሉበት፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ በጽሞና ያደምጥ ነበር። ጸሐፊውም ዕዝራ ለዚህ ተብሎ በተሠራ የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቅያና ማዓሴያ በቀኙ በኩል፤ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላም በግራው በኩል ቆመው ነበር። ዕዝራም ከሕዝቡ ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ ነበርና በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ፊት መጽሐፉን ከፈተ፤ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ። ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ። በመጽሐፉ ያለውን የእግዚአብሔርን ሕግ በግልጽ አነበቡ፥ የተነበበው እንዲገባቸውም ያስረዷቸው ነበር። ገዢው ነህምያ፥ ጸሐፊው ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡን የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህ ቀን ለጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነው፤ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና። እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው።