በውኃውም በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ በወንዶችና በሴቶች በሚያስተውሉትም ፊት፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ ለመስማት ያደምጥ ነበር። ጸሓፊውም ዕዝራ ስለዚህ ነገር በተሠራ በዕንጨት መረባርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ መቲትያ፥ ሰምያ፥ ሐናንያ፤ ኦርያ፥ ሕልቅያ፥ መዕሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳኤል፥ ሚልክያ፥ ሐሱም፥ ሐስበዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሱላም በግራው በኩል ቆመው ነበር። ዕዝራም የሕዝቡ ሁሉ የበላይ ነበረና በሕዝቡ ሁሉ ፊት መጽሐፉን ገለጠ፤ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝራም ታላቁን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጃቸውን እየዘረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳቸውንም አዘነበሉ፤ በግንባራቸውም ወደ ምድር ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ። ደግሞ ኢያሱና ባኒ፥ ሰራብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛርያ፥ ኢዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፌልዕያ፥ ሌዋውያኑም ሕጉን ለሕዝቡ ያስተምሩ ነበር፤ ሕዝቡም በየስፍራቸው ቆመው ነበር። የእግዚአብሔርንም ሕግ መጽሐፍ አነበቡ፤ ዕዝራም እግዚአብሔርን ማወቅ ያስተምርና ያስታውቅ ነበር፤ ሕዝቡም የሚነበበውን ያስተውሉ ነበር። ሕቴርሰታ ነህምያም፥ ጸሓፊውም ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡንም የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፥ “ዛሬ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቀን ነው፤ አትዘኑ፤ አታልቅሱም” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና። እርሱም፥ “ሂዱ፤ የሰባውንም ብሉ፤ ጣፋጩንም ጠጡ፤ ለእነዚያም ምንም ለሌላቸው እድል ፈንታቸውን ላኩ፤ ዛሬ ለጌታችን የተቀደሰ ቀን ነው፤ እግዚአብሔርም ኀይላችን ነውና አትዘኑ” አላቸው።
መጽሐፈ ነህምያ 8 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ነህምያ 8:3-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች