መጽሐፈ ነህምያ 8
8
ለሕጉ እንዲገዙ ዕዝራ ሕዝቡን መሰብሰቡ
1 #
ዕዝ. 3፥1። ሕዝቡም ሁሉ በውኃው በር ፊት ወዳለው አደባባይ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰበሰቡ፤ ጌታ ለእስራኤል ያዘዘውን የሙሴን ሕግ መጽሐፍ እንዲያመጣ ለጸሐፊው ለዕዝራ ነገሩት። 2#ዘሌ. 23፥23-25፤ ዘኍ. 29፥1-6።ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን ወንዶች፥ ሴቶችና አስተውለው መስማት የሚችሉ ባሉበት በጉባኤው ሁሉ ፊት አመጣው። 3በውኃው በር ፊት ባለው አደባባይ ላይ ቆሞ፥ ወንዶች፥ ሴቶች፥ የሚያስተውሉም ባሉበት፥ ከማለዳ ጀመሮ እስከ ቀትር ድረስ አነበበው፤ የሕዝቡም ሁሉ ጆሮ የሕጉን መጽሐፍ በጽሞና ያደምጥ ነበር። 4ጸሐፊውም ዕዝራ ለዚህ ተብሎ በተሠራ የእንጨት መድረክ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአጠገቡ ማቲትያ፥ ሼማዕ፥ ዓናያ፥ ኡሪያ፥ ሒልቅያና ማዓሴያ በቀኙ በኩል፤ ፐዳያ፥ ሚሻኤል፥ ማልኪያ፥ ሐሹም፥ ሐሽባዳና፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላም በግራው በኩል ቆመው ነበር። 5ዕዝራም ከሕዝቡ ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ ነበርና በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ፊት መጽሐፉን ከፈተ፤ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። 6ዕዝራም ታላቁን አምላክ ጌታን ባረከ፤ ሕዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን በመዘርጋት፦ አሜን፥ አሜን ብለው መለሱ። ራሳቸውን አዘነበሉ፥ በግምባራቸውም ተደፍተው ለጌታ ሰገዱ። 7#ነህ. 10፥10-13።ደግሞ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻብታይ፥ ሆዲያ፥ ማዓሤያ፥ ቅሊጣ፥ አዛርያ፥ ዮዛባድ፥ ሐናን፥ ፐላያና ሌዋውያኑ ሕጉን ለሕዝቡ ያስረዱ ነበር፤ ሕዝቡም በቆሙበት ነበሩ። 8#ዕዝ. 7፥6።በመጽሐፉ ያለውን የእግዚአብሔርን ሕግ በግልጽ አነበቡ፥ የተነበበው እንዲገባቸውም ያስረዷቸው ነበር።
9ገዢው ነህምያ፥ ጸሐፊው ካህኑ ዕዝራ፥ ሕዝቡን የሚያስተምሩ ሌዋውያን ሕዝቡን ሁሉ፦ “ይህ ቀን ለጌታ አምላካችሁ ቅዱስ ነው፤ አታልቅሱ እንባም አታፍስሱ” አሉአቸው፤ ሕዝቡ ሁሉ የሕጉን ቃል በሰሙ ጊዜ ያለቅሱ ነበርና። 10#አስ. 9፥19።እርሱም፦ “ሂዱ፥ የሰባውን ብሉ፥ ጣፋጩንም ጠጡ፥ ለእነዚያ ምንም ላልተዘጋጀላቸው ድርሻቸውን ላኩ፤ ይህ ቀን ለጌታችን ቅዱስ ነውና፤ አትዘኑ የጌታ ደስታ ኃይላችሁ ነውና” አላቸው። 11ሌዋውያንም፦ “ቀኑ ቅዱስ ነውና ዝም በሉ፥ አትዘኑም” እያሉ ሕዝቡን ሁሉ ዝም አሰኙት። 12ሕዝቡም ሁሉ ሊበሉ፥ ሊጠጡ፥ ለሌላቸው ድርሻቸውን ሊልኩና ታላቅ ደስታ ሊያደርጉ ሄዱ፤ የተነገራቸውን ቃል ማስተዋል ችለው ነበርና።
የዳስ በዓል መከበር
13በሁለተኛው ቀን ከሕዝቡ ሁሉ አለቆች የሆኑ አባቶች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም የሕጉን ቃል እንዲተረጉምላቸው ወደ ጸሐፊው ወደ ዕዝራ ተሰበሰቡ። 14#ዘፀ. 23፥14-16፤ ዘሌ. 23፥33-36፤ ዘኍ. 29፥1-38፤ ሕዝ. 45፥25።በሰባተኛው ወር ባለው በዓል የእስራኤል ልጆች በዳስ እንዲቀመጡ ጌታ በሙሴ በኩል ያዘዘውን በሕጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ፤ 15#መዝ. 118፥27።በከተሞቻቸው ሁሉና በኢየሩሳሌምም፦ “እንደተጻፈው ዳሶችን ለመስራት ወደ ተራራ ውጡ፥ የዘይትና የበረሀ ወይራ፥ የባርሰነት፥ የዘንባባና የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ አምጡ” ብለው ይናገሩና ያውጁ። 16ሕዝቡም ወጥተው አመጡ፥ እያንዳንዱ በቤቱ ሰገነት ላይ፥ በየግቢያቸው፥ በእግዚአብሔር ቤት ግቢ፥ በ “ውኃ በር” አደባባይና በኤፍሬም በር አደባባይ ላይ ዳሶችን ሠሩ። 17#2ዜ.መ. 30፥26፤ 35፥18።ከምርኮ የተመለሱት ማኅበር ሁሉ ዳሶችን ሠሩ፥ በዳሶቹም ውስጥ ተቀመጡ። ከነዌ#8፥17 ዕብራይስጡ ከ “ኑን” ይላል። ልጅ ከኢያሱ ዘመን ጀምሮ እስከዚያ ቀን ድረስ የእስራኤል ልጆች እንዲህ ያለ ነገር አድርገው አያውቁም ነበርና። እጅግ ታላቅ ደስታም ሆነ። 18ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ዕዝራ ዕለት ዕለት የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ ያነብብ ነበር። በዓሉን ሰባት ቀን አከበሩ፤ በስምንተኛው ቀን በሕጉ መሠረት የተቀደሰ ጉባኤ ነበረ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ