ዘሌዋውያን 14:33-57

ዘሌዋውያን 14:33-57 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “ርስት አድርጌ ወደምሰጣቸው ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፣ በዚያ አገር አንዱን ቤት በተላላፊ በሽታ የበከልሁ እንደ ሆነ፣ ባለቤቱ ወደ ካህኑ ሄዶ፣ ‘በቤቴ ውስጥ ተላላፊ በሽታ የሚመስል ነገር አይቻለሁ’ ብሎ ይንገረው። ካህኑ ወደዚያ ቤት በመግባት በሽታውን መርምሮ ርኩስ መሆኑን ከማስታወቁ በፊት፣ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉት ይዘዝ፤ ከዚህ በኋላ ካህኑ ወደ ቤቱ ገብቶ ይመርምር። በግድግዳው ላይ ያለውን ተላላፊ በሽታ በሚመረምርበት ጊዜ፣ መልኩ ወደ አረንጓዴነት ወይም ወደ ቀይነት የሚያደላ የተቦረቦረ ነገር በግድግዳው ቢታይ፣ ካህኑ ከቤቱ ወደ ደጅ ወጥቶ ቤቱን ሰባት ቀን ይዝጋው። ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቤቱን ለመመርመር ይመለስ፤ ተላላፊው በሽታ በግድግዳው ተስፋፍቶ ቢገኝ፣ ካህኑ የተበከሉት ድንጋዮች ተሰርስረው እንዲወጡና ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲጣሉ ይዘዝ፤ የቤቱ ግድግዳ በሙሉ በውስጥ በኩል እንዲፋቅና ፍቅፋቂው ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲደፋ ያድርግ። በወጡትም ድንጋዮች ቦታ ሌሎች ድንጋዮች አምጥተው ይተኩ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይምረጉ። “ድንጋዮቹ ወጥተው፣ ቤቱ ከተፈቀፈቀና ከተመረገ በኋላ ተላላፊው በሽታ እንደ ገና በቤቱ ውስጥ ከታየ፣ ካህኑ ሄዶ ይመርምረው፤ ተላላፊው በሽታ በቤቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ከተገኘ፣ አደገኛ በሽታ ነው፤ ቤቱም ርኩስ ነው። ስለዚህ ቤቱ ይፍረስ፤ ድንጋዩ፣ ዕንጨቱና ምርጊቱ በሙሉ ከከተማ ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ ይጣል። “ቤቱ ተዘግቶ ሳለ ማንኛውም ሰው ቢገባበት፣ ያ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። በዚያ ቤት ገብቶ የተኛ ወይም የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ። “ነገር ግን ቤቱ ከተመረገ በኋላ፣ ካህኑ ሊመረምረው በሚመጣበት ጊዜ ተላላፊው በሽታ ሳይስፋፋ ቢገኝ፣ በሽታው ስለ ለቀቀው ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የዝግባ ዕንጨት፣ ደመቅ ያለ ቀይ ድርና ሂሶጵ ያቅርብ። ከወፎቹም አንዱን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ባለ የምንጭ ውሃ ላይ ይረድ። የዝግባውን ዕንጨት፣ ሂሶጱን፣ ደመቅ ያለውን ቀይ ድርና በሕይወት ያለውን ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውሃ ውስጥ ይንከር፤ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይርጭ። ቤቱንም በወፉ ደም፣ በምንጩ ውሃ፣ በሕይወት ባለው ወፍ፣ በዝግባው ዕንጨት፣ በሂሶጱና ደመቅ ባለው ቀይ ድር ያንጻው። በሕይወት ያለውንም ወፍ ከከተማ ወደ ውጭ ይልቀቀው፤ በዚህ ሁኔታ ለቤቱ ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል።” ይህ ሕግ ለማንኛውም ተላላፊ የቈዳ በሽታ፣ ለሚያሳክክ ሕመም፣ በልብስና በቤት ላይ ለሚመጣ ተላላፊ በሽታ፣ ለዕብጠት፣ ለችፍታ ወይም ለቋቍቻ፣ አንድ ነገር ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑ የሚታወቅበት ነው። ይህ ለተላላፊ የቈዳ በሽታ እንዲሁም በልብስና በቤት ላይ ለሚወጣ ተላላፊ በሽታ የሚያገለግል ሕግ ነው።

ዘሌዋውያን 14:33-57 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ወደምሰጣችሁ ወደ ከነዓን ምድር በምትገቡበት ጊዜ በዚያ አገር በሚገኝ በአንድ ቤት ውስጥ ሻጋታ ሳሠራጭ፥ የሻጋታው ምልክት በራሱ ቤት ውስጥ መኖሩን የተገነዘበ ማንም ሰው ሄዶ ለካህኑ ‘በቤቴ ሻጋታ መሰል ነገር አለ’ ብሎ ይንገር፤ ካህኑም ሄዶ የሻጋታውን ዐይነት ከመመርመሩ በፊት በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እንዲወጣ ትእዛዝ ይስጥ፤ አለበለዚያ በቤቱ ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ካህኑ ወደ ቤት ገብቶ ይመርምር፤ የሻጋታውን ዐይነት በሚመረምርበት ጊዜ ግድግዳውን እየቦረቦሩ የሚበሉት አረንጓዴ ወይም ቀይ ዐይነት ዝንጒርጒር ምልክቶች ቢታዩበት፥ ከዚያ ቤት ወጥቶ ለሰባት ቀን እንዲዘጋ ያድርገው። በሰባተኛው ቀን ተመልሶ መጥቶ እንደገና ይመርምረው፤ የሻጋታው ምልክት ተስፋፍቶ ቢገኝ፥ የሻጋታው ምልክት ያለባቸው ድንጋዮች ተፈልፍለው ወጥተው ከከተማው ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ ማከማቻ እንዲጣሉ ይዘዝ። ከዚያም በኋላ የውስጡ ግድግዳ ሁሉ እንዲፋቅና ምርጊቱ ሁሉ ተቀርፎ ከከተማ ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ መጣያ እንዲጣል ያድርግ። ከዚህም በኋላ በእነዚያ በቀድሞዎቹ ድንጋዮች ምትክ ሌሎች አዳዲስ ድንጋዮች ተገንብተው ቤቱ በአዲስ ጭቃ ይመረግ። “ድንጋዮቹ ተወግደው፥ ግድግዳው ተፍቆ፥ ምርጊቱም ተነሥቶ ቤቱ በዐዲስ ጭቃ ተመርጎ ከታደሰ በኋላ የሻጋታው ምልክት እንደገና ቢታይ፥ ካህኑ ሄዶ ይመልከተው፤ የሻጋታው ዐይነት የሚስፋፋና የማይለቅ ሻጋታ ስለ ሆነ ቤቱ ርኩስ ነው። ስለዚህ መፍረስ አለበት፤ ድንጋዮቹ እንጨቱና ምርጊቱ ሁሉ ከከተማ ውጪ ተወስዶ በረከሰ ጒድፍ ማከማቻ ስፍራ ይጣል፤ ከተዘጋ በኋላ ወደዚያ ቤት የገባ ሰው ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ወይም ምግብ የተመገበ ቢኖር ልብሱን ይጠብ። “ቤቱ እንደገና ታድሶ ከተለሰነ በኋላ ካህኑ መጥቶ በሚመለከትበት ጊዜ ሻጋታው የመስፋፋት ምልክት የማያሳይ ሆኖ ከተገኘ ግን የሻጋታው ምልክት ጨርሶ ስለ ጠፋ ያ ቤት ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፥ ጥቂት የሊባኖስ ዛፍ እንጨት፥ የቀይ ከፈይ ክርና የሂሶጵ ቅጠል ይውሰድ። ከወፎቹ አንዱን ንጹሕ የምንጭ ውሃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ላይ ይረደው፤ ከዚያም በኋላ የሊባኖሱን ዛፍ እንጨት፥ የሂሶጱን ቅጠል፥ የቀዩን ከፈይ ክርና በሕይወት ያለውን ወፍ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውሃ ውስጥ ይንከረው፤ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይርጨው። በዚህም ዐይነት ካህኑ ያንን ቤት በወፉ ደም፥ በንጹሑ ውሃ፥ ሕይወት ባለው ወፍ፥ በሊባኖሱ ዛፍ እንጨት በሂሶጱ ቅጠልና በቀዩ የከፈይ ክር እንዲነጻ ያደርገዋል። ከዚያም በኋላ በሕይወት ያለውን ወፍ ከከተማ ውጪ ወደ ሜዳ እንዲበር ይለቀዋል፤ በዚህም ዐይነት ለቤቱ የማንጻት ሥርዓት ይፈጽማል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል። “እነዚህም ለማንኛውም ተላላፊ ለሆነ የሥጋ ደዌ በሽታ፥ ለእከክ የሥርዓት መመሪያዎች ናቸው። በልብስና በቤት ላይ የሚወጣ ሻጋታን፥ እባጭን፥ ሽፍታንና ቋቊቻን ለማንጻት የወጡ ሕጎች ናቸው። እነዚህ ሥርዓቶች አንድን ነገር ንጹሕ መሆኑን ወይም አለመሆኑን የሚወስኑ ናቸው።”

ዘሌዋውያን 14:33-57 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እኔም የለምጽ ደዌ በርስታችሁ ምድር በአንድ ቤት ባደረግሁ ጊዜ፥ ባለቤቱ መጥቶ ካህኑን፦ ደዌ በቤቴ ውስጥ እንዳለ ይመስለኛል ብሎ ይንገረው። ካህኑም በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እንዳይረክስ፥ እርሱ ደዌውን ለማየት ወደ ቤት ሳይገባ፥ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉት ያዝዛል፤ በኋላም ካህኑ ቤቱን ለማየት ይገባል። ደዌውንም ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በግንቡ ላይ በአረንጓዴና በቀይ ቢዥጐረጐር፥ መልኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠልቅ፥ ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ቤቱ በር ወጥቶ ሰባት ቀን ቤቱን ይዘጋዋል። ካህኑም በሰባተኛው ቀን ተመልሶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ወደ ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል። ቤቱንም በውስጡ በዙሪያው ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል። በእነዚያም ድንጋዮች ስፍራ ሌሌች ድንጋዮች ያገባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይመርጉታል። ደዌውም ዳግም ቢመለስ፥ ድንጋዮቹም ከወጡ ቤቱም ከተፋቀና ከተመረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥ ካህኑ ገብቶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ውስት ቢሰፋ፥ በቤቱ ውስጥ ያለው እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው። ቤቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ እንጨቱንም፥ የቤቱንም ምርጊት ሁሉ ያፈርሳል፤ እነርሱንም ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወጣል። በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። በቤቱም የሚተኛ ልብሱን ያጥባል፤ በቤቱም የሚበላ ልብሱን ያጥባል። ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፥ የዝግባም እንጨት፥ ቀይ ግምጃም፥ ሂሶጵም ይወስዳል። አንደኛውንም ወፍ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከምንጩ ውኃ በላይ ያርዳል። የዝግባውን እንጨት፥ ሂሶጱንም፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ሕያውንም ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፥ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። ቤቱንም በወፉ ደም በምንጩም ውኃ በሕያውም ወፍ በዝግባውም እንጨት በሂሶጱም በቀዩም ግምጃ ያነጻዋል። ሕያውንም ወፍ ከከተማ ወደ ሜዳ ይሰድደዋል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፥ ንጹሕም ይሆናል። ይህም ሕግ ነው ለሁሉ ዓይነት ለምጽ ደዌ፥ ለቈረቈርም፥ በልብስና በቤትም ላለ ለምጽ፥ ለእባጭም፥ ለብጕርም፥ ለቍቁቻም፤ በሚረክስና በሚነጻ ጊዜ እንዲያስታውቅ ይህ የለምጽ ሕግ ነው።

ዘሌዋውያን 14:33-57 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ “ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ እኔ ወደ​ም​ሰ​ጣ​ችሁ ርስት ወደ ከነ​ዓን ምድር በገ​ባ​ችሁ ጊዜ፥ እኔም የለ​ምጽ ደዌ ምል​ክት በር​ስ​ታ​ችሁ ምድር ቤቶች ባደ​ረ​ግሁ ጊዜ፥ ባለ​ቤቱ መጥቶ ካህ​ኑን፦ ‘ደዌ በቤቴ ውስጥ እን​ዳለ አይ​ቻ​ለሁ’ ብሎ ይን​ገ​ረው። ካህ​ኑም በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ፥ እርሱ የለ​ም​ጹን ምል​ክት ለማ​የት ወደ ቤት ሳይ​ገባ፥ ቤቱን ባዶ እን​ዲ​ያ​ደ​ር​ጉት ያዝ​ዛል፤ በኋ​ላም ካህኑ ቤቱን ለማ​የት ይገ​ባል። የለ​ም​ጹ​ንም ምል​ክት ያያል፤ እነ​ሆም፥ የለ​ምጹ ምል​ክት በግ​ንቡ ላይ በአ​ረ​ን​ጓ​ዴና በቀይ ቢዥ​ጐ​ረ​ጐር፥ መል​ኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠ​ልቅ፥ ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ቤቱ በር ወጥቶ ሰባት ቀን ቤቱን ይዘ​ጋ​ዋል። ካህ​ኑም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ተመ​ልሶ ቤቱን ያያል፤ እነ​ሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለ​ባ​ቸ​ውን ድን​ጋ​ዮች እን​ዲ​ያ​ወጡ፥ ከከ​ተ​ማ​ውም ወደ ውጭ ወደ ረከ​ሰው ስፍራ እን​ዲ​ጥ​ሉ​አ​ቸው ያዝ​ዛል። ቤቱ​ንም በው​ስጡ በዙ​ሪ​ያው ያስ​ፍ​ቀ​ዋል፤ የፋ​ቁ​ት​ንም የም​ር​ጊ​ቱን አፈር ከከ​ተ​ማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈ​ስ​ሱ​ታል። በእ​ነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች ስፍራ ሌሎች ድን​ጋ​ዮ​ችን ያገ​ባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስ​ደው ቤቱን ይመ​ር​ጉ​ታል። “ደዌ​ውም ዳግም ቢመ​ለስ፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹም ከወጡ፥ ቤቱም ከተ​ፋ​ቀና ከተ​መ​ረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥ ካህኑ ገብቶ ያያል፤ እነ​ሆም፥ ደዌው በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥ በቤቱ ውስጥ ያለው እየ​ፋገ የሚ​ሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው። ቤቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም፥ የቤ​ቱ​ንም ምር​ጊት ሁሉ ያፈ​ር​ሳል፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከከ​ተ​ማው ወደ ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወ​ጣል። በተ​ዘ​ጋ​በ​ትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚ​ገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆ​ናል። በቤ​ቱም የሚ​ተኛ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው፤ በቤ​ቱም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። “ካህ​ኑም ገብቶ ቢያ​የው፥ እነ​ሆም፥ ቤቱ ከተ​መ​ረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይ​ሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለ​ዋል። ካህ​ኑም ቤቱን ለማ​ን​ጻት ሁለት ዶሮ​ዎች፥ የዝ​ግባ ዕን​ጨት፥ ቀይ ግምጃ፥ ሂሶ​ጵም ይወ​ስ​ዳል። አን​ደ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ከም​ንጩ ውኃ በላይ ያር​ዳል። የዝ​ግ​ባ​ውን ዕን​ጨት፥ ሂሶ​ጱ​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ደኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ ወስዶ በታ​ረ​ደ​ችው ዶሮ ደምና በም​ንጩ ውኃ ውስጥ ይነ​ክ​ራ​ቸ​ዋል፥ ቤቱ​ንም ሰባት ጊዜ ይረ​ጨ​ዋል። ቤቱ​ንም በዶ​ሮ​ዪቱ ደም በም​ን​ጩም ውኃ፥ በደ​ኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱም ዶሮ፥ በዝ​ግ​ባ​ውም ዕን​ጨት፥ በሂ​ሶ​ጱም፥ በቀ​ዩም ግምጃ ያነ​ጻ​ዋል። ደኅ​ነ​ኛ​ዪ​ቱ​ንም ዶሮ ከከ​ተማ ወደ ሜዳ ይሰ​ድ​ዳ​ታል፤ ለቤ​ቱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ንጹ​ሕም ይሆ​ናል። “ይህም ሕግ ነው፤ ለሁሉ ዓይ​ነት ለም​ጽና የቈ​ረ​ቈር ደዌ ሕጉ ይህ ነው፤ በል​ብ​ስና በቤ​ትም ላለ ለምጽ፥ ለዕ​ባ​ጭም፥ ለብ​ጕ​ርም፥ ለቋ​ቍ​ቻም፤ በሚ​ረ​ክ​ስና በሚ​ነጻ ጊዜ እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ውቅ ይህ የለ​ምጽ ሕግ ነው።”

ዘሌዋውያን 14:33-57 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “ርስት አድርጌ ወደምሰጣቸው ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፣ በዚያ አገር አንዱን ቤት በተላላፊ በሽታ የበከልሁ እንደ ሆነ፣ ባለቤቱ ወደ ካህኑ ሄዶ፣ ‘በቤቴ ውስጥ ተላላፊ በሽታ የሚመስል ነገር አይቻለሁ’ ብሎ ይንገረው። ካህኑ ወደዚያ ቤት በመግባት በሽታውን መርምሮ ርኩስ መሆኑን ከማስታወቁ በፊት፣ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉት ይዘዝ፤ ከዚህ በኋላ ካህኑ ወደ ቤቱ ገብቶ ይመርምር። በግድግዳው ላይ ያለውን ተላላፊ በሽታ በሚመረምርበት ጊዜ፣ መልኩ ወደ አረንጓዴነት ወይም ወደ ቀይነት የሚያደላ የተቦረቦረ ነገር በግድግዳው ቢታይ፣ ካህኑ ከቤቱ ወደ ደጅ ወጥቶ ቤቱን ሰባት ቀን ይዝጋው። ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቤቱን ለመመርመር ይመለስ፤ ተላላፊው በሽታ በግድግዳው ተስፋፍቶ ቢገኝ፣ ካህኑ የተበከሉት ድንጋዮች ተሰርስረው እንዲወጡና ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲጣሉ ይዘዝ፤ የቤቱ ግድግዳ በሙሉ በውስጥ በኩል እንዲፋቅና ፍቅፋቂው ከከተማው ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ እንዲደፋ ያድርግ። በወጡትም ድንጋዮች ቦታ ሌሎች ድንጋዮች አምጥተው ይተኩ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይምረጉ። “ድንጋዮቹ ወጥተው፣ ቤቱ ከተፈቀፈቀና ከተመረገ በኋላ ተላላፊው በሽታ እንደ ገና በቤቱ ውስጥ ከታየ፣ ካህኑ ሄዶ ይመርምረው፤ ተላላፊው በሽታ በቤቱ ውስጥ ተስፋፍቶ ከተገኘ፣ አደገኛ በሽታ ነው፤ ቤቱም ርኩስ ነው። ስለዚህ ቤቱ ይፍረስ፤ ድንጋዩ፣ ዕንጨቱና ምርጊቱ በሙሉ ከከተማ ውጭ ባለው ርኩስ ስፍራ ይጣል። “ቤቱ ተዘግቶ ሳለ ማንኛውም ሰው ቢገባበት፣ ያ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። በዚያ ቤት ገብቶ የተኛ ወይም የበላ ማንኛውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ። “ነገር ግን ቤቱ ከተመረገ በኋላ፣ ካህኑ ሊመረምረው በሚመጣበት ጊዜ ተላላፊው በሽታ ሳይስፋፋ ቢገኝ፣ በሽታው ስለ ለቀቀው ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የዝግባ ዕንጨት፣ ደመቅ ያለ ቀይ ድርና ሂሶጵ ያቅርብ። ከወፎቹም አንዱን በሸክላ ዕቃ ውስጥ ባለ የምንጭ ውሃ ላይ ይረድ። የዝግባውን ዕንጨት፣ ሂሶጱን፣ ደመቅ ያለውን ቀይ ድርና በሕይወት ያለውን ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውሃ ውስጥ ይንከር፤ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይርጭ። ቤቱንም በወፉ ደም፣ በምንጩ ውሃ፣ በሕይወት ባለው ወፍ፣ በዝግባው ዕንጨት፣ በሂሶጱና ደመቅ ባለው ቀይ ድር ያንጻው። በሕይወት ያለውንም ወፍ ከከተማ ወደ ውጭ ይልቀቀው፤ በዚህ ሁኔታ ለቤቱ ያስተሰርይለታል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል።” ይህ ሕግ ለማንኛውም ተላላፊ የቈዳ በሽታ፣ ለሚያሳክክ ሕመም፣ በልብስና በቤት ላይ ለሚመጣ ተላላፊ በሽታ፣ ለዕብጠት፣ ለችፍታ ወይም ለቋቍቻ፣ አንድ ነገር ንጹሕ ወይም ርኩስ መሆኑ የሚታወቅበት ነው። ይህ ለተላላፊ የቈዳ በሽታ እንዲሁም በልብስና በቤት ላይ ለሚወጣ ተላላፊ በሽታ የሚያገለግል ሕግ ነው።

ዘሌዋውያን 14:33-57 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ እኔም የለምጽ ደዌ በርስታችሁ ምድር በአንድ ቤት ባደረግሁ ጊዜ፥ ባለቤቱ መጥቶ ካህኑን፦ ደዌ በቤቴ ውስጥ እንዳለ ይመስለኛል ብሎ ይንገረው። ካህኑም በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እንዳይረክስ፥ እርሱ ደዌውን ለማየት ወደ ቤት ሳይገባ፥ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉት ያዝዛል፤ በኋላም ካህኑ ቤቱን ለማየት ይገባል። ደዌውንም ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በግንቡ ላይ በአረንጓዴና በቀይ ቢዥጐረጐር፥ መልኩም ወደ ግንቡ ውስጥ ቢጠልቅ፥ ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ቤቱ በር ወጥቶ ሰባት ቀን ቤቱን ይዘጋዋል። ካህኑም በሰባተኛው ቀን ተመልሶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግንብ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ወደ ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል። ቤቱንም በውስጡ በዙሪያው ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል። በእነዚያም ድንጋዮች ስፍራ ሌሌች ድንጋዮች ያገባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይመርጉታል። ደዌውም ዳግም ቢመለስ፥ ድንጋዮቹም ከወጡ ቤቱም ከተፋቀና ከተመረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥ ካህኑ ገብቶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ውስት ቢሰፋ፥ በቤቱ ውስጥ ያለው እየፋገ የሚሄድ ለምጽ ነው፤ ርኩስ ነው። ቤቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ እንጨቱንም፥ የቤቱንም ምርጊት ሁሉ ያፈርሳል፤ እነርሱንም ከከተማው ወደ ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወጣል። በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። በቤቱም የሚተኛ ልብሱን ያጥባል፤ በቤቱም የሚበላ ልብሱን ያጥባል። ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ሻረ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፥ የዝግባም እንጨት፥ ቀይ ግምጃም፥ ሂሶጵም ይወስዳል። አንደኛውንም ወፍ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ከምንጩ ውኃ በላይ ያርዳል። የዝግባውን እንጨት፥ ሂሶጱንም፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ሕያውንም ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፥ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። ቤቱንም በወፉ ደም በምንጩም ውኃ በሕያውም ወፍ በዝግባውም እንጨት በሂሶጱም በቀዩም ግምጃ ያነጻዋል። ሕያውንም ወፍ ከከተማ ወደ ሜዳ ይሰድደዋል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፥ ንጹሕም ይሆናል። ይህም ሕግ ነው ለሁሉ ዓይነት ለምጽ ደዌ፥ ለቈረቈርም፥ በልብስና በቤትም ላለ ለምጽ፥ ለእባጭም፥ ለብጕርም፥ ለቍቁቻም፤ በሚረክስና በሚነጻ ጊዜ እንዲያስታውቅ ይህ የለምጽ ሕግ ነው።

ዘሌዋውያን 14:33-57 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ወደምሰጣችሁ ወደ ከነዓን ምድር በምትገቡበት ጊዜ በዚያ አገር በሚገኝ በአንድ ቤት ውስጥ ሻጋታ ሳሠራጭ፥ የሻጋታው ምልክት በራሱ ቤት ውስጥ መኖሩን የተገነዘበ ማንም ሰው ሄዶ ለካህኑ ‘በቤቴ ሻጋታ መሰል ነገር አለ’ ብሎ ይንገር፤ ካህኑም ሄዶ የሻጋታውን ዐይነት ከመመርመሩ በፊት በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እንዲወጣ ትእዛዝ ይስጥ፤ አለበለዚያ በቤቱ ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ካህኑ ወደ ቤት ገብቶ ይመርምር፤ የሻጋታውን ዐይነት በሚመረምርበት ጊዜ ግድግዳውን እየቦረቦሩ የሚበሉት አረንጓዴ ወይም ቀይ ዐይነት ዝንጒርጒር ምልክቶች ቢታዩበት፥ ከዚያ ቤት ወጥቶ ለሰባት ቀን እንዲዘጋ ያድርገው። በሰባተኛው ቀን ተመልሶ መጥቶ እንደገና ይመርምረው፤ የሻጋታው ምልክት ተስፋፍቶ ቢገኝ፥ የሻጋታው ምልክት ያለባቸው ድንጋዮች ተፈልፍለው ወጥተው ከከተማው ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ ማከማቻ እንዲጣሉ ይዘዝ። ከዚያም በኋላ የውስጡ ግድግዳ ሁሉ እንዲፋቅና ምርጊቱ ሁሉ ተቀርፎ ከከተማ ውጪ በሚገኘው በረከሰ ጒድፍ መጣያ እንዲጣል ያድርግ። ከዚህም በኋላ በእነዚያ በቀድሞዎቹ ድንጋዮች ምትክ ሌሎች አዳዲስ ድንጋዮች ተገንብተው ቤቱ በአዲስ ጭቃ ይመረግ። “ድንጋዮቹ ተወግደው፥ ግድግዳው ተፍቆ፥ ምርጊቱም ተነሥቶ ቤቱ በዐዲስ ጭቃ ተመርጎ ከታደሰ በኋላ የሻጋታው ምልክት እንደገና ቢታይ፥ ካህኑ ሄዶ ይመልከተው፤ የሻጋታው ዐይነት የሚስፋፋና የማይለቅ ሻጋታ ስለ ሆነ ቤቱ ርኩስ ነው። ስለዚህ መፍረስ አለበት፤ ድንጋዮቹ እንጨቱና ምርጊቱ ሁሉ ከከተማ ውጪ ተወስዶ በረከሰ ጒድፍ ማከማቻ ስፍራ ይጣል፤ ከተዘጋ በኋላ ወደዚያ ቤት የገባ ሰው ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ወይም ምግብ የተመገበ ቢኖር ልብሱን ይጠብ። “ቤቱ እንደገና ታድሶ ከተለሰነ በኋላ ካህኑ መጥቶ በሚመለከትበት ጊዜ ሻጋታው የመስፋፋት ምልክት የማያሳይ ሆኖ ከተገኘ ግን የሻጋታው ምልክት ጨርሶ ስለ ጠፋ ያ ቤት ንጹሕ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፥ ጥቂት የሊባኖስ ዛፍ እንጨት፥ የቀይ ከፈይ ክርና የሂሶጵ ቅጠል ይውሰድ። ከወፎቹ አንዱን ንጹሕ የምንጭ ውሃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ላይ ይረደው፤ ከዚያም በኋላ የሊባኖሱን ዛፍ እንጨት፥ የሂሶጱን ቅጠል፥ የቀዩን ከፈይ ክርና በሕይወት ያለውን ወፍ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውሃ ውስጥ ይንከረው፤ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይርጨው። በዚህም ዐይነት ካህኑ ያንን ቤት በወፉ ደም፥ በንጹሑ ውሃ፥ ሕይወት ባለው ወፍ፥ በሊባኖሱ ዛፍ እንጨት በሂሶጱ ቅጠልና በቀዩ የከፈይ ክር እንዲነጻ ያደርገዋል። ከዚያም በኋላ በሕይወት ያለውን ወፍ ከከተማ ውጪ ወደ ሜዳ እንዲበር ይለቀዋል፤ በዚህም ዐይነት ለቤቱ የማንጻት ሥርዓት ይፈጽማል፤ ቤቱም ንጹሕ ይሆናል። “እነዚህም ለማንኛውም ተላላፊ ለሆነ የሥጋ ደዌ በሽታ፥ ለእከክ የሥርዓት መመሪያዎች ናቸው። በልብስና በቤት ላይ የሚወጣ ሻጋታን፥ እባጭን፥ ሽፍታንና ቋቊቻን ለማንጻት የወጡ ሕጎች ናቸው። እነዚህ ሥርዓቶች አንድን ነገር ንጹሕ መሆኑን ወይም አለመሆኑን የሚወስኑ ናቸው።”

ዘሌዋውያን 14:33-57 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “እኔ ወደምሰጣችሁ ርስት ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ በምትወርሱአት ምድር በአንድ ቤት ውስጥ የለምጽ ደዌ ባኖር፥ የቤቱ ባለቤት መጥቶ ካህኑን፦ ‘ደዌ የሚመስል ነገር በቤቴ ውስጥ ያለ ይመስለኛል’ ብሎ ይንገረው። ካህኑም በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እንዳይረክስ፥ እርሱ ደዌውን ለማየት ወደ ቤቱ ከመግባቱ በፊት፥ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉት ያዝዛል፤ ከዚያም በኋላ ካህኑ ቤቱን ለማየት ይገባል። ደዌውንም ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግድግዳ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀይ ሆኖ ቢዥጐረጐር፥ መልኩም ከግድግዳው ውጫዊ ገጽታ ዘልቆ ቢገባ፥ ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ቤቱ በር ወጥቶ ሰባት ቀን ቤቱን ይዘጋዋል። ካህኑም በሰባተኛው ቀን ተመልሶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ግድግዳ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ ደዌ ያለባቸውን ድንጋዮች እንዲያወጡ፥ ከከተማውም ውጭ ወደ ረከሰው ስፍራ እንዲጥሉአቸው ያዝዛል። የቤቱንም ውስጥ ዙሪያውን ያስፍቀዋል፤ የፋቁትንም የምርጊቱን አፈር ከከተማው ውጭ ወደ ረከሰ ስፍራ ያፈስሱታል። በእነዚያም ድንጋዮች ስፍራ ሌሌች ድንጋዮችን አምጥተው ያገባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስደው ቤቱን ይመርጉታል። “ደዌውም ዳግም ቢመለስ፥ ድንጋዮቹም ከወጡ ቤቱም ከተፋቀና ከተመረገ በኋላ በቤቱ ውስጥ ቢሰፋ፥ ካህኑ ገብቶ ያያል፤ እነሆም፥ ደዌው በቤቱ ውስት ቢሰፋ፥ በቤቱ ውስጥ ያለው እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነው፤ እርሱ ርኩስ ነው። ቤቱንም፥ ድንጋዮቹንም፥ እንጨቱንም፥ የቤቱንም ምርጊት ሁሉ ያፈርሳል፤ እነርሱንም ከከተማው ውጭ ወደ ርኩስ ስፍራ ያወጣል። በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። በቤቱም ውስጥ የሚተኛ ልብሱን ያጥባል፤ በቤቱም ውስጥ የሚበላ ልብሱን ያጥባል። “ካህኑም ገብቶ ቢያይ፥ እነሆም፥ ቤቱ ከተመረገ በኋላ ደዌው በቤቱ ውስጥ ባይሰፋ፥ ደዌው ስለ ጠፋ ካህኑ ቤቱን፦ ንጹሕ ነው ይለዋል። ቤቱንም ለማንጻት ሁለት ወፎች፥ የዝግባም እንጨት፥ ቀይ ግምጃም፥ ሂሶጵም ይወስዳል። አንደኛውንም ወፍ በሸክላ ዕቃ ውስጥ በምንጭ ውኃ ላይ ያርዳል። የዝግባውን እንጨት፥ ሂሶጱንም፥ ቀዩንም ግምጃ፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ ወስዶ በታረደው ወፍ ደምና በምንጩ ውኃ ውስጥ ይነክራቸዋል፥ ቤቱንም ሰባት ጊዜ ይረጨዋል። ቤቱንም በወፉ ደም፥ በምንጩም ውኃ፥ ሕይወትም ባለው ወፍ፥ በዝግባውም እንጨት፥ በሂሶጱም፥ በቀዩም ግምጃ ያነጻዋል። በሕይወትም ያለውን ወፍ ከከተማ ወጥቶ ወደ ተንጣለለው ሜዳ እንዲበር ይለቀዋል፤ ለቤቱም ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።” “ይህ ሕግ ለሁሉም ዓይነት የለምጽ ደዌ፥ ለቈረቈርም፥ በልብስ ላይና በቤት ውስጥ ላለ የለምጽ ደዌ፥ ለእባጭም፥ ለብጉርም፥ ለቋቁቻም የሚሆን ነው። እንዲሁም አንድ ነገር በሚረክስና በሚነጻ ጊዜ ለማልከት የሚያስችል ነው። ይህ የለምጽ ደዌ ሕግ ነው።”