ሰቈቃወ 3:37-66

ሰቈቃወ 3:37-66 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጌታ ካላዘዘ በቀር፣ ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው? ክፉም ሆነ መልካም ነገር፣ ከልዑል አፍ የሚወጣ አይደለምን? ታዲያ ሕያው ሰው በኀጢአቱ ሲቀጣ፣ ስለ ምን ያጕረመርማል? መንገዳችንን እንመርምር፤ እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። ልባችንን ከእጃችን ጋራ በሰማይ ወዳለው ወደ አምላካችን እናንሣ፤ እንዲህም እንበል፤ “ዐምፀናል፤ ኀጢአትም ሠርተናል፤ አንተም ይቅር አላልኸንም። “ራስህን በቍጣ ከደንህ፤ አሳደድኸንም፤ ያለ ርኅራኄም ገደልኸን። ጸሎት እንዳያልፍ፣ ራስህን በደመና ሸፈንህ። በአሕዛብ መካከል፣ አተላና ጥራጊ አደረግኸን። “ጠላቶቻችን ሁሉ፣ አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ። በጥፋትና በመፈራረስ፣ በችግርና በሽብር ተሠቃየን።” የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ ሕዝቤ ዐልቋልና። ያለ ዕረፍት፣ ያለ ማቋረጥ ዐይኖቼ እንባ ያፈስሳሉ፤ እግዚአብሔር ከላይ፣ ከሰማይ እስኪያይ ድረስ። በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ ነፍሴን አስጨነቃት። ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣ እንደ ወፍ ዐደኑኝ። ሕይወቴን በጕድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ ድንጋይም በላዬ አደረጉ። ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ። በጥልቁ ጕድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ። ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።” በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣ እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ። ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ ሕይወቴንም ተቤዠህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ ፍርዴን ፍረድልኝ! በቀላቸውን ሁሉ፣ በእኔም ላይ ያሰቡትን ዐድማ አየህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ስድባቸውን ሁሉ፣ በእኔ ላይ ያሰቡትን ዐድማ ሁሉ ሰማህ፤ ይህም ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ፣ ጠላቶቼ የሚያውጠነጥኑትና የሚያንሾካሹኩት ነው። ተመልከታቸው! ቆመውም ሆነ ተቀምጠው፣ በዘፈናቸው ይሣለቁብኛል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እጆቻቸው ላደረጉት፣ የሚገባውን መልሰህ ክፈላቸው። በልባቸው ላይ መጋረጃን ዘርጋ፤ ርግማንህም በላያቸው ይሁን! ከእግዚአብሔር ሰማያት በታች፣ በቍጣህ አሳድዳቸው፤ አጥፋቸውም።

ሰቈቃወ 3:37-66 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሜም። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ይመ​ጣል፥ ከል​ዑል አፍም ያል​ወጣ መል​ካም ወይም ክፉ ይሆ​ናል” የሚል ማን ነው? ሰው ሕያው ሲሆን ስለ ኀጢ​አቱ ለምን ያጕ​ረ​መ​ር​ማል? ኖን። መን​ገ​ዳ​ች​ንን እን​መ​ር​ም​ርና እን​ፈ​ትን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​መ​ለስ። ልባ​ች​ንን ከእ​ጃ​ችን ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ እና​ንሣ። በድ​ለ​ናል፤ ዐም​ፀ​ና​ልም፤ አን​ተም አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም። ሳም​ኬት። በቍ​ጣህ ከደ​ን​ኸን፤ አሳ​ደ​ድ​ኸ​ንም፤ ገደ​ል​ኸን፤ አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም። ጸሎ​ታ​ችን እን​ዳ​ያ​ርግ ራስ​ህን በደ​መና ከደ​ንህ። እን​ድ​ና​ዝ​ንና እን​ዳ​ና​ይም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸን። ዔ። ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ። ፍር​ሀ​ትና ቍጣ፥ ጥፋ​ትና ቅጥ​ቃጤ ያዘን። ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥ​ቃጤ ከዐ​ይኔ የውኃ ጐርፍ ፈሰሰ። ፌ። ዐይኔ ተደ​ፈ​ነች፤ እን​ግ​ዲህ ከማ​ን​ጋ​ጠጥ ዝም አል​ልም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ እስ​ኪ​መ​ለ​ከት ድረስ። ስለ ከተ​ማዬ ቈነ​ጃ​ጅት ሁሉ ዐይኔ ነፍ​ሴን አሳ​ዘ​ነች። ጻዴ። በከ​ንቱ ነገር ጠላ​ቶች ሁሉ እንደ ወፍ ማደ​ንን አደ​ኑኝ። ጠላ​ቶች ሕይ​ወ​ቴን በጕ​ድ​ጓድ አጠፉ፤ በላ​ዬም ድን​ጋይ ገጠሙ። በራሴ ላይ ውኃ ተከ​ነ​በለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር። ቆፍ። አቤቱ፥ በጥ​ልቅ ጕድ​ጓድ ውስጥ ሆኜ ስም​ህን ጠራሁ። አንተ ድም​ፄን ሰማህ፤ ጆሮ​ህ​ንም ከል​መ​ናዬ አት​መ​ልስ። በጠ​ራ​ሁህ ቀን ወደ እኔ ቅረብ፤ “አት​ፍ​ራም” በለኝ። ሬስ። አቤቱ፥ የነ​ፍ​ሴን ፍርድ ፈረ​ድህ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም ተቤ​ዥህ። አቤቱ፥ ጭን​ቀ​ቴን አይ​ተ​ሃል፤ ፍር​ዴን ፍረ​ድ​ልኝ። በቀ​ላ​ቸ​ውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ አየህ። ሣን። አቤቱ፥ ስድ​ባ​ቸ​ው​ንና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ ሰማህ። የተ​ነ​ሡ​ብ​ኝን ሰዎች ከን​ፈ​ሮች ቀኑ​ንም ሁሉ ያሰ​ቡ​ብ​ኝን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሰማህ። መቀ​መ​ጣ​ቸ​ው​ንና መነ​ሣ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ እኔ መዝ​ፈ​ኛ​ቸው ነኝ። ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃ​ቸው ሥራ ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው። የልብ ሕማ​ም​ንና ርግ​ማ​ን​ህን ስጣ​ቸው። አቤቱ፥ እንደ ልባ​ቸው ክፋት በቍ​ጣህ ታሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ማ​ይም በታች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ።

ሰቈቃወ 3:37-66 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጌታ ካላዘዘ በቀር፣ ተናግሮ መፈጸም የሚችል ማን ነው? ክፉም ሆነ መልካም ነገር፣ ከልዑል አፍ የሚወጣ አይደለምን? ታዲያ ሕያው ሰው በኀጢአቱ ሲቀጣ፣ ስለ ምን ያጕረመርማል? መንገዳችንን እንመርምር፤ እንፈትን፤ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። ልባችንን ከእጃችን ጋራ በሰማይ ወዳለው ወደ አምላካችን እናንሣ፤ እንዲህም እንበል፤ “ዐምፀናል፤ ኀጢአትም ሠርተናል፤ አንተም ይቅር አላልኸንም። “ራስህን በቍጣ ከደንህ፤ አሳደድኸንም፤ ያለ ርኅራኄም ገደልኸን። ጸሎት እንዳያልፍ፣ ራስህን በደመና ሸፈንህ። በአሕዛብ መካከል፣ አተላና ጥራጊ አደረግኸን። “ጠላቶቻችን ሁሉ፣ አፋቸውን በእኛ ላይ ከፈቱ። በጥፋትና በመፈራረስ፣ በችግርና በሽብር ተሠቃየን።” የእንባ ጐርፍ ከዐይኔ ፈሰሰ፤ ሕዝቤ ዐልቋልና። ያለ ዕረፍት፣ ያለ ማቋረጥ ዐይኖቼ እንባ ያፈስሳሉ፤ እግዚአብሔር ከላይ፣ ከሰማይ እስኪያይ ድረስ። በከተማዬ ባሉት ሴቶች ሁሉ ላይ የደረሰውን ማየቴ፣ ነፍሴን አስጨነቃት። ያለ ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ፣ እንደ ወፍ ዐደኑኝ። ሕይወቴን በጕድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ ድንጋይም በላዬ አደረጉ። ውሃ ሞልቶ በዐናቴ ላይ ፈሰሰ፤ ጠፍቻለሁ ብዬ አሰብሁ። በጥልቁ ጕድጓድ ውስጥ ሳለሁ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተን ስም ጠራሁ። ልመናዬን ሰምተሃል፤ “ርዳታም ፈልጌ ስጮኽ፣ ከመስማት ጆሮህን አትከልክል።” በጠራሁህ ጊዜ ቀረብኸኝ፣ እንዲሁም፣ “አትፍራ” አልኸኝ። ጌታ ሆይ፤ ለእኔ ተሟገትኽልኝ፤ ሕይወቴንም ተቤዠህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ ፍርዴን ፍረድልኝ! በቀላቸውን ሁሉ፣ በእኔም ላይ ያሰቡትን ዐድማ አየህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ስድባቸውን ሁሉ፣ በእኔ ላይ ያሰቡትን ዐድማ ሁሉ ሰማህ፤ ይህም ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ፣ ጠላቶቼ የሚያውጠነጥኑትና የሚያንሾካሹኩት ነው። ተመልከታቸው! ቆመውም ሆነ ተቀምጠው፣ በዘፈናቸው ይሣለቁብኛል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እጆቻቸው ላደረጉት፣ የሚገባውን መልሰህ ክፈላቸው። በልባቸው ላይ መጋረጃን ዘርጋ፤ ርግማንህም በላያቸው ይሁን! ከእግዚአብሔር ሰማያት በታች፣ በቍጣህ አሳድዳቸው፤ አጥፋቸውም።

ሰቈቃወ 3:37-66 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሜም። ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው? ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን? ሕያው ሰው የሚያጉረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጕረመርም ስለ ምንድር ነው? ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ። በድለናል ዐምፀናልም፥ አንተም ይቅር አላልህም። ሳምኬት። በቍጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፥ ገደልኸን፥ አልራራህም። ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ። በአሕዛብ መካከል ጕድፍና ውዳቂ አደረግኸን። ዔ። ጠላቶቻችን ሁሉ አፋቸውን ኣላቀቁብን። ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን። ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች። ፌ። እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባ ታፈስሳለች። ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዓይኔ ነፍሴን አሳዘነች። ጻዴ። በከንቱ ነገር ጠላቶች የሆኑኝ እንደ ወፍ ማደንን አደኑኝ። ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ። በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፥ እኔም፦ ጠፋሁ ብዬ ነበር። ቆፍ። አቤቱ፥ በጠለቀ ጕድጓድ ውስጥ ሆኜ ስምህን ጠራሁ። ድምፄን ሰማህ፥ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ። በጠራሁህ ቀን ቀርበህ፦ አትፍራ አልህ። ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ። አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፥ ፍርዴን ፍረድልኝ። በቀላቸውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ አየህ። ሳን። አቤቱ፥ ስድባቸውንና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ፥ የተነሡብኝን ሰዎች ከንፈሮች ቀኑንም ሁሉ ያሰቡብኝን አሳባቸውን ሰማህ። መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፥ እኔ መሳለቂያቸው ነኝ። ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ። የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ። አቤቱ፥ በቍጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።

ሰቈቃወ 3:37-66 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነው ካልሆነ በትእዛዙ አንድን ነገር ማስደረግ የሚችል ማነው? ደግም ሆነ ክፉ ነገር ተግባራዊ የሚሆነው ልዑል እግዚአብሔር በሚናገረው መሠረት አይደለምን? ሰው በሕይወቱ እያለ በኃጢአት ምክንያት ሲቀጣ የሚያጒረመርመው ለምንድን ነው? አካሄዳችንን መርምረን፤ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። በሰማይ ወዳለው አምላካችን ልባችንንና እጃችንን እናንሣ። “አምላክ ሆይ! እኛ ኃጢአትና ዐመፅ ሠርተናል፤ አንተም ይቅር አላልከንም። “በቊጣ ተሞልተህ አሳደድከን ያለ ርኅራኄ ገደልከን። ጸሎት አልፎ ሊገባ በማይችልበት ራስህን ጥቅጥቅ ባለ ደመና ሸፈንክ። መኖሪያህን በደመና ሸፈንክ። በሕዝቦች መካከል እንደ ጒድፍና ጥራጊ አደረግኸን። “ጠላቶቻችን ሁሉ አፋቸውን ከፈቱብን ፍርሀትና ውድቀት እንዲሁም ጥፋትና ውድመት በእኛ ላይ ደረሱ። በሕዝቤ ላይ በደረሰው ጥፋት ምክንያት እንባ ከዐይኖቼ እንደ ወንዝ ውሃ ይጐርፋል። “እንባዬ ያለማቋረጥ ይፈስሳል። ይህም የሚሆነው እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ታች ተመልክቶ እስኪያይ ድረስ ነው። በከተማዬ ውስጥ ባሉት ወጣት ሴቶች ላይ የደረሰውን ክፉ ዕድል በማየቴ የመረረ ሐዘን ደረሰብኝ። “ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ እንደ ወፍ አጠመዱኝ። ከነሕይወቴ ጒድጓድ ውስጥ ወርውረው የጒድጓዱን አፍ በድንጋይ ዘጉብኝ። ውሃ ከእራሴ በላይ ሞልቶ ሲፈስ የምሞትበት ጊዜ የተቃረበ መሰለኝ። “እግዚአብሔር ሆይ! በጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆኜ፥ ስምህን ጠራሁ። ጆሮህን ወደ እኔ መልስ፤ ለእርዳታም ድረስልኝ” የሚለውን ልመናዬን ሰምተሃል፤ ስለዚህ ዕረፍትን ስጠኝ። በጠራሁህ ጊዜ ወደ እኔ ቀርበህ “አትፍራ!” አልከኝ። “ጌታ ሆይ! የእኔን ጉዳይ ተከታትለህ ሕይወቴን አዳንክ። እግዚአብሔር ሆይ! በእኔ ላይ የደረሰውን በደል ሁሉ አይተሃልና ፍትሕን ስጠኝ። ጠላቶቼ በእኔ ላይ ያላቸውን የበቀል ስሜትና ያቀዱትን ሤራ አይተሃል። “እግዚአብሔር ሆይ! በእኔ ላይ የሰነዘሩትን ስድባቸውንና ያቀዱትንም ሤራ ሰምተሃል። ቀኑን ሙሉ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ይንሾካሾካሉ፤ ያጒረመርማሉም። ተቀምጠውም ሆነ ቆመው በቅኔ በእኔ ላይ በአሽሙር የሚሳለቁ መሆናቸውን ተመልከት። “አምላክ ሆይ! ለፈጸሙት ተግባር የሚገባቸውን ዋጋ ስጣቸው። ርግማንህ በእነርሱ ላይ ይሁን! ተስፋ እንዲቈርጡም አድርጋቸው! እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ አሳዳቸው፤ ከሰማያትም በታች ደምስሳቸው!”

ሰቈቃወ 3:37-66 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሜም። ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው? ከልዑል አፍ ክፉና መልካም ነገር አይወጣምን? ሕያው ሰው የሚያጉረመርም፥ ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት የሚያጉረመርም ስለ ምንድነው? ኖን። መንገዳችንን እንመርምርና እንፈትን፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ። ልባችንን ከእጃችን ጋር በሰማይ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣ። በድለናል ዐምፀናልም፥ አንተም ይቅር አላልህም። ሳምኬት። በቁጣ ከደንኸን አሳደድኸንም፥ ገደልኸን፥ አልራራህም። ጸሎት እንዳያልፍ ራስህን በደመና ከደንህ። በአሕዛብ መካከል ጉድፍና ውዳቂ አደረግኸን። ዔ። ጠላቶቻችን ሁሉ አፋቸውን ኣላቀቁብን። ድንጋጤና ቁጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን። ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች። ፌ። እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይኔ ሳታቋርጥ ዝም ሳትል እንባ ታፈስሳለች። ስለ ከተማዬ ቈነጃጅት ሁሉ ዓይኔ ነፍሴን አሳዘነች። ጻዴ። በከንቱ ነገር ጠላቶች የሆኑኝ እንደ ወፍ ማደንን አደኑኝ። ሕይወቴን በጉድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ። በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፥ እኔም፦ ጠፋሁ ብዬ ነበር። ቆፍ። አቤቱ፥ በጠለቀ ጉድጓድ ውስጥ ሆኜ ስምህን ጠራሁ። ድምፄን ሰማህ፥ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ። በጠራሁህ ቀን ቀርበህ፦ አትፍራ አልህ። ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ። አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፥ ፍርዴን ፍረድልኝ። በቀላቸውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ አየህ። ሳን። አቤቱ፥ ስድባቸውንና በእኔ ላይ ያለውን አሳባቸውን ሁሉ፥ የተነሡብኝን ሰዎች ከንፈሮች ቀኑንም ሁሉ ያሰቡብኝን አሳባቸውን ሰማህ። መቀመጣቸውንና መነሣታቸውን ተመልከት፥ እኔ መሳለቂያቸው ነኝ። ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ። የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ። አቤቱ፥ በቁጣ ታሳድዳቸዋለህ ከሰማይም በታች ታጠፋቸዋለህ።