ሰቆ​ቃወ ኤር​ም​ያስ ነቢይ 3:37-66

ሰቆ​ቃወ ኤር​ም​ያስ ነቢይ 3:37-66 አማ2000

ሜም። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዘው ይመ​ጣል፥ ከል​ዑል አፍም ያል​ወጣ መል​ካም ወይም ክፉ ይሆ​ናል” የሚል ማን ነው? ሰው ሕያው ሲሆን ስለ ኀጢ​አቱ ለምን ያጕ​ረ​መ​ር​ማል? ኖን። መን​ገ​ዳ​ች​ንን እን​መ​ር​ም​ርና እን​ፈ​ትን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​መ​ለስ። ልባ​ች​ንን ከእ​ጃ​ችን ጋር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰማይ እና​ንሣ። በድ​ለ​ናል፤ ዐም​ፀ​ና​ልም፤ አን​ተም አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም። ሳም​ኬት። በቍ​ጣህ ከደ​ን​ኸን፤ አሳ​ደ​ድ​ኸ​ንም፤ ገደ​ል​ኸን፤ አል​ራ​ራ​ህ​ል​ንም። ጸሎ​ታ​ችን እን​ዳ​ያ​ርግ ራስ​ህን በደ​መና ከደ​ንህ። እን​ድ​ና​ዝ​ንና እን​ዳ​ና​ይም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸን። ዔ። ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ሁሉ በእኛ ላይ አፋ​ቸ​ውን ከፈቱ። ፍር​ሀ​ትና ቍጣ፥ ጥፋ​ትና ቅጥ​ቃጤ ያዘን። ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥ​ቃጤ ከዐ​ይኔ የውኃ ጐርፍ ፈሰሰ። ፌ። ዐይኔ ተደ​ፈ​ነች፤ እን​ግ​ዲህ ከማ​ን​ጋ​ጠጥ ዝም አል​ልም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ እስ​ኪ​መ​ለ​ከት ድረስ። ስለ ከተ​ማዬ ቈነ​ጃ​ጅት ሁሉ ዐይኔ ነፍ​ሴን አሳ​ዘ​ነች። ጻዴ። በከ​ንቱ ነገር ጠላ​ቶች ሁሉ እንደ ወፍ ማደ​ንን አደ​ኑኝ። ጠላ​ቶች ሕይ​ወ​ቴን በጕ​ድ​ጓድ አጠፉ፤ በላ​ዬም ድን​ጋይ ገጠሙ። በራሴ ላይ ውኃ ተከ​ነ​በለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር። ቆፍ። አቤቱ፥ በጥ​ልቅ ጕድ​ጓድ ውስጥ ሆኜ ስም​ህን ጠራሁ። አንተ ድም​ፄን ሰማህ፤ ጆሮ​ህ​ንም ከል​መ​ናዬ አት​መ​ልስ። በጠ​ራ​ሁህ ቀን ወደ እኔ ቅረብ፤ “አት​ፍ​ራም” በለኝ። ሬስ። አቤቱ፥ የነ​ፍ​ሴን ፍርድ ፈረ​ድህ፤ ሕይ​ወ​ቴ​ንም ተቤ​ዥህ። አቤቱ፥ ጭን​ቀ​ቴን አይ​ተ​ሃል፤ ፍር​ዴን ፍረ​ድ​ልኝ። በቀ​ላ​ቸ​ውን ሁሉና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ አየህ። ሣን። አቤቱ፥ ስድ​ባ​ቸ​ው​ንና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ ሰማህ። የተ​ነ​ሡ​ብ​ኝን ሰዎች ከን​ፈ​ሮች ቀኑ​ንም ሁሉ ያሰ​ቡ​ብ​ኝን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሰማህ። መቀ​መ​ጣ​ቸ​ው​ንና መነ​ሣ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ እኔ መዝ​ፈ​ኛ​ቸው ነኝ። ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃ​ቸው ሥራ ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው። የልብ ሕማ​ም​ንና ርግ​ማ​ን​ህን ስጣ​ቸው። አቤቱ፥ እንደ ልባ​ቸው ክፋት በቍ​ጣህ ታሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ማ​ይም በታች ታጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለህ።