ኢዮብ 23:10-12
ኢዮብ 23:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
መንገዴን ፈጽሞ ዐወቀ፥ እንደ ወርቅም ፈተነኝ እንደ ትእዛዙ እወጣለሁ፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። ከትእዛዙም አላለፍሁም፤ ቃሉን በልቤ ሰውሬአለሁ።
ያጋሩ
ኢዮብ 23 ያንብቡኢዮብ 23:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ግን እኔ የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ። እግሮቼ ርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ። ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣ የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።
ያጋሩ
ኢዮብ 23 ያንብቡኢዮብ 23:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፥ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ። እግሬ ወደ እርምጃው ተጣብቆአል፥ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፥ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።
ያጋሩ
ኢዮብ 23 ያንብቡ