መጽሐፈ ኢዮብ 23

23
1ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“ዛሬም ደግሞ የኀዘን እንጉርጉሮዬ ገና መራራ ነው፥
በመቃተት ብጮኽም እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።#23፥2 “እግዚአብሔር ስቃዬን አላቆመም” እንደማለት ነው።
3እርሱን እንዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ!
ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!
4በፊቱ አቤቱታዬን አቀርብ ነበር፥
አፌንም በማስረጃ እሞላው ነበር።
5የሚመልስልኝም ቃል ምን እንደሆነ አውቅ ነበር፥
የሚለኝንም አስተውል ነበር።
6በታላቅ ኃይሉ ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን?
ይልቁንም! ማዳመጥ ይበቃው ነበር።
7የሚከራከረው ቅን ሰው መሆኑን ይመሰክር ነበር፥
እኔም በፈራጅ ፊት ለዘለዓለም ነፃ እወጣ ነበር።”
8“እነሆ፥ ወደፊትም#23፥8 “ወደ ምሥራቅ ብሄድ” የሚሉ ትርጉሞችም አሉ። ብሄድ፥ እርሱ የለም፥
ወደ ኋላም ብሄድ፥ አላየውም፥
9ወደሚሠራበት ወደ ግራ#23፥9 ሰሜን። ብሄድ አይታየኝም፥
በቀኜም#23፥9 ደቡብ። ይሰወራል፥ አላየውምም፥
10የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፥
ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።
11እግሬ ዱካውን ተከትሎአል፥
መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ከመስመር አልወጣሁም።
12ከተናገራቸው ትእዛዛት አልኮበለልኩም፥
የአፉን ቃል በልቤ ደብቄአለሁ።
13እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል?
የወደደውንም ያደርጋል።
14በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥
እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት።
15ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፥
ባሰብሁም መጠን ፈራሁት።
16እግዚአብሔር ልቤን አባብቶታልና፥
ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል።
17በጨለማው አልተደመሰስኩም፥
ነገር ግን ድቅድቁ ጨለማ ፊቴን ሸፈነ።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ