መጽሐፈ ኢዮብ 22
22
1 #
ኢዮብ 35፥6-8። ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“በውኑ ሰው እግዚአብሔርን ይጠቅመዋልን?
ይልቁንም ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማል።
3ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን?
መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን?
4እርሱንስ ስለ ፈራህ ይዘልፍሃልን?
ወደ ፍርድስ ከአንተ ጋር ይገባልን?
5ክፋትህስ ብዙ አይደለምን?
ለዐመፅህም ወሰን የለውም።
6ከወንድሞችህ አላግባብ መያዣ ወስደሃል፥#22፥6 ያበደረ ሰው ተበዳሪው ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ ለማስያዣነት ከተበዳሪው አንድ ዕቃ ይወስድ ነበር።
የታረዙትንም ልብስ ዘርፈሃል።
7በጥም የደከመውን ውኃ አላጠጣህም፥
የተራበውንም እንጀራ ከልክለሃል።
8ኃይለኛ ሰው መሬት ገዛ፥
የተከበረ ሰው ተቀመጠባት።
9መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰድደሃቸዋል፥
የወላጅ አልቦችም ክንዶች ተሰብረዋል።
10ስለዚህ ወጥመዶች ከብበውሃል፥
ድንገተኛ ፍርሃትም አናውጦሃል።
11እንዳታይ ብርሃን ጨለማ ሆነችብህ፥
የውኆችም ሙላት አሰጠመህ።”
12“እግዚአብሔር በላይ በሰማያት አይደለምን?
ከዋክብትም እንዴት ከፍ ባለ ስፍራ ላይ እንዳሉ ተመልከት።”
13አንተም፦ “እግዚአብሔር ምን ያውቃል?
በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?
14እንዳያይ የጠቈረ ደመና ጋርዶታል፥
በሰማይ ክበብ ላይ ይራመዳል” ብለሃል።
15“በውኑ ክፉ ሰዎች የሄዱበትን
የዱሮውን መንገድ ትከተላለህን?
16ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፥
መሠረታቸውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።”#22፥16 መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ ማለትም ይቻላል።
17እነርሱም እግዚአብሔርን፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ፥
ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል?” አሉት።
18“ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞልቶት ነበር፥
የክፉ ሰው ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።
19ይህንን አይተው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፥
ንጹሑም ሰው ይስቅባቸዋል።
20በእውነት ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፥
ከንብረታቸው የተረፈውንም እሳት በላች።”
21“እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥
በዚያም መልካምን ታገኛለህ።
22ከአፉም ትምህርቱን ተቀበል፥
በልብህም ቃሉን አኑር፥
23ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ ትደረጃለህ#22፥23 ሰባ ሊቃናት “እራስህን ዝቅ ብታደርግ” ይላል።፥
ክፋትንም ከድንኳንህ#22፥23 ከቤትህ። ብታርቅ፥
24ወርቅን በአፈር ውስጥ#22፥24 “ወርቅን እንደ አፈር ብትቆጥር” ማለትም ይቻላል።፥
የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
25ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል።
26የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥
ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
27ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥
ስእለትህንም ትሰጣለህ።
28በጉዳዮችም ላይ ትመክራለህ፥ እርሱም ይሳካልሃል፥
ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።
29ቢያዋርዱ፥ አንተ ‘መነሣት#22፥29 ወይም “ትዕቢት አለ።” አለ’ ትላለህ፥
ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።
30ንጹሑን ሰው ያድነዋል፥
በእጅህም ንጽሕና ትድናለህ።”#22፥30 በመልካም ተግባርህ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 22: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ