የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 23

23
1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦
ኢዮብ
2“አሁንም ልቤ በመረረ ሐዘንና ሮሮ የተሞላ ነው፤
በመቃተት ብጮኽም
እጁ በእኔ ላይ እንደ ከበደች ናት።
3የሚገኝበትን ቦታ ባውቅ እንዴት በወደድሁ ነበር፤
ወደሚኖርበትም ቦታ ብደርስ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፤
4አቤቱታዬን በፊቱ አሰማ ነበር፤
የመከላከያ መልሴንም በዝርዝር አቀርብ ነበር።
5የሚሰጠኝን መልስ ዐውቅ ነበር፤
ምን እንደሚለኝም እረዳ ነበር።
6ታዲያ፥ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ይፋረደኝ ይሆን?
አይደለም፤ ነገር ግን ነገሬን ያዳምጣል።
7በዚያ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር ይከራከራል፤
ዳኛዬ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል።
8“ነገር ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ በዚያ የለም፤
ወደ ምዕራብም ብመለስ ላገኘው አልቻልኩም።
9እርሱ በሰሜን ሥራውን ይሠራል፤ እኔ ግን ላየው አልቻልኩም፤
ወደ ደቡብም ብዞር ላገኘው አልቻልኩም።
10እርሱ እርምጃዬን ሁሉ ያውቃል፤
ቢፈትነኝም እንደ ወርቅ ንጹሕ ሆኜ ያገኘኛል።
11እግሮቼ እርሱ በሚወደው መንገድ ይሄዳሉ፤
በማወላወል ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልልም።
12ከእርሱ ትእዛዞች አልወጣሁም፤
ቃሉንም በልቤ ውስጥ ጠብቄአለሁ።
13“እርሱ ራሱ ይወስናል፤
እርሱንም የሚቃወም የለም፤
እርሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።
14በእኔ ላይ ያቀደውን ሁሉ ይፈጽመዋል፤
ይህንንም የሚመስሉ ብዙ ዕቅዶች አሉት።
15ስለዚህ በእርሱ ፊት መቆም እጅግ ያስፈራኛል፤
ይህን ባሰብኩ ጊዜ እንኳ ፈራሁ።
16እግዚአብሔር ልቤ እንዲዝል አደረገው፤
ሁሉን የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።
17ምንም እንኳ ድቅድቅ ጨለማ ዐይኔን ቢጋርደኝ፥
የጨለማው ክብደት ከመናገር እንድቈጠብ አላደረገኝም።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ