ኤርምያስ 31:1-22

ኤርምያስ 31:1-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከሰ​ይፍ የተ​ረ​ፈው ሕዝብ በም​ድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ሂዱ፦ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አታ​ጥፉ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሩቅ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “በዘ​ለ​ዓ​ለም ፍቅር ወድ​ጄ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ በቸ​ር​ነት ሳብ​ሁህ። የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ እንደ ገና እሠ​ራ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም ትሠ​ሪ​ያ​ለሽ፤ እንደ ገናም ከበ​ሮ​ሽን አን​ሥ​ተሽ ከዘ​ፋ​ኞች ጋር ትወ​ጫ​ለሽ። እንደ ገናም በሰ​ማ​ርያ ተራ​ሮች ላይ የወ​ይን ተክ​ሎ​ችን ትተ​ክ​ሊ​አ​ለሽ፤ የም​ት​ተ​ክሉ ትከሉ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ በኤ​ፍ​ሬም ተራ​ሮች ላይ የሚ​ከ​ራ​ከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ውጣ ብለው የሚ​ጠ​ሩ​ባት ቀን ትመ​ጣ​ለ​ችና።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቅሬታ አድ​ኖ​አል በሉ። እነሆ፥ ከሰ​ሜን ሀገር አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ለበ​ዓለ ፋሲካ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብም ይወ​ለ​ዳሉ፤ ወደ​ዚ​ህም ይመ​ለ​ሳሉ። እያ​ለ​ቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማ​ጽ​ና​ናት አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በወ​ንዝ ዳር በቅን መን​ገድ አስ​ሄ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም አይ​ሰ​ና​ከ​ሉም፤ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አባት ነኝና፥ ኤፍ​ሬ​ምም በኵሬ ነውና።” አሕ​ዛብ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ በሩ​ቅም ላሉ ደሴ​ቶች አው​ሩና፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን የበ​ተነ እርሱ ይሰ​በ​ስ​በ​ዋል፤ እረ​ኛም መን​ጋ​ውን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል በሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​ታል፤ ከበ​ረ​ቱ​በ​ትም እጅ አድ​ኖ​ታል። ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም። በዚ​ያን ጊዜም ደና​ግሉ በዘ​ፈን ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹም በአ​ንድ ላይ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እኔም ልቅ​ሶ​አ​ቸ​ውን ወደ ደስታ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከኀ​ዘ​ና​ቸ​ውም ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ። የካ​ህ​ና​ቱ​ንም የሌ​ዊን ልጆች ሰው​ነት ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ አረ​ካ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ከበ​ረ​ከቴ ይጠ​ግ​ባል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የኀ​ዘን፥ የል​ቅ​ሶና የጩ​ኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆ​ችዋ አለ​ቀ​ሰች፤ የሉ​ምና ስለ ልጆ​ችዋ መጽ​ና​ና​ትን እንቢ አለች። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ድም​ፅ​ሽን ከል​ቅሶ፥ ዐይ​ኖ​ች​ሽ​ንም ከእ​ንባ ከል​ክዪ፤ ለሥ​ራሽ ዋጋ ይሆ​ና​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከጠ​ላ​ትም ምድር ይመ​ለ​ሳሉ። ለፍ​ጻ​ሜ​ሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ልጆ​ች​ሽም ወደ ሀገ​ራ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ። “ኤፍ​ሬም ሲጨ​ነቅ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ ቀጣ​ኸኝ እኔም እን​ዳ​ል​ቀና ወይ​ፈን ተቀ​ጣሁ፤ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ነህና መል​ሰኝ፤ እኔም እመ​ለ​ሳ​ለሁ። ከተ​መ​ለ​ስሁ በኋላ ተጸ​ጸ​ትሁ፤ ከተ​ገ​ሠ​ጽ​ሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፤ የብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ቴ​ንም ስድብ ተሸ​ክ​ሜ​አ​ለ​ሁና አፈ​ርሁ፥ ተዋ​ረ​ድ​ሁም። በእ​ው​ነት ኤፍ​ሬም ለእኔ የተ​ወ​ደደ ልጅ ነው፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም ሕፃን ነው፤ በእ​ርሱ ላይ በተ​ና​ገ​ርሁ ቍጥር አስ​በ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ አን​ጀቴ ታወ​ከ​ች​ለት፤ ርኅ​ራ​ኄም እራ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። “ለራ​ስሽ የመ​ን​ገድ ምል​ክት አድ​ርጊ፥ መን​ገ​ድ​ንም የሚ​መሩ ዐም​ዶ​ችን ትከዪ፤ ልብ​ሽ​ንም ወደ ሄድ​ሽ​በት መን​ገድ ወደ ጥር​ጊ​ያው አቅኚ፤ አንቺ የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ! ተመ​ለሺ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ወደ ከተ​ሞ​ችሽ እያ​ለ​ቀ​ስሽ ተመ​ለሺ። አንቺ ከዳ​ተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅ​በ​ዘ​በ​ዣ​ለሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥ​ሮ​አ​ልና ሰው ወደ ድኅ​ነት ይመ​ጣል።”

ኤርምያስ 31:1-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“በዚያ ዘመን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለእስራኤል ነገድ ሁሉ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ፣ በምድረ በዳ ሞገስን ያገኛል፤ እኔም ለእስራኤል ዕረፍት ለመስጠት እመጣለሁ።” እግዚአብሔር ከሩቅ ተገለጠልን፤ እንዲህም አለን፤ “በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፤ እንደ ገና ዐንጽሻለሁ፤ አንቺም ትታነጺአለሽ፤ ከበሮችሽንም እንደ ገና አንሥተሽ፣ ከሚፈነጥዙት ጋራ ትፈነድቂአለሽ። እንደ ገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ፣ ወይን ትተክያለሽ፤ አትክልተኞች ይተክሏቸዋል፤ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል። ጠባቂዎች፣ በኤፍሬም ኰረብቶች ላይ፣ ‘ኑ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ!’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣል።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ፤ ስለ ሕዝቦች አለቃ እልል በሉ፤ ምስጋናችሁን አሰሙ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ የእስራኤልን ቅሬታ፣ ሕዝብህን አድን’ በሉ። እነሆ፤ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዕውሮችና ዐንካሶች፣ ነፍሰ ጡርና በምጥ ላይ ያሉ ሴቶች ይገኛሉ፤ ታላቅም ሕዝብ ሆነው ይመለሳሉ። እያለቀሱ ይመጣሉ፤ እያጽናናሁ አመጣቸዋለሁ፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፣ ኤፍሬም በኵር ልጄ ነውና፣ በውሃ ምንጭ ዳር፣ በማይሰናከሉበት ቀና መንገድ እመራቸዋለሁ። “ሕዝቦች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ሩቅ ባሉ የባሕር ጠረፎችም፣ ‘እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል’ ብላችሁ ዐውጁ። እግዚአብሔር ያዕቆብን ይዋጀዋልና፤ ከርሱም ከሚበረቱት እጅ ይታደገዋልና። መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣ በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣ በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህም አያዝኑም። ኰረዶች ይዘፍናሉ፤ ደስም ይላቸዋል፤ ጐረምሶችና ሽማግሌዎችም ይፈነጥዛሉ፤ ልቅሷቸውን ወደ ደስታ እለውጣለሁ፤ ከሐዘናቸውም አጽናናቸዋለሁ፤ ደስታንም እሰጣቸዋለሁ። ካህናቱን አትረፍርፌ እባርካለሁ፤ ሕዝቤም በልግስናዬ ይጠግባል፤” ይላል እግዚአብሔር። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ ከራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፣ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ድምፅሽን ከልቅሶ፣ ዐይኖችሽንም ከእንባ ከልክይ፤ ድካምሽ ያለ ዋጋ አይቀርምና፤” ይላል እግዚአብሔር። “ከጠላት ምድር ይመለሳሉ፤ ስለዚህ ወደ ፊት ተስፋ አለሽ” ይላል እግዚአብሔር። “ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ። “የኤፍሬምን የሲቃ እንጕርጕሮ በርግጥ ሰምቻለሁ፤ ‘እንዳልተገራ ወይፈን ቀጣኸኝ፤ እኔም ተቀጣሁ። አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና፣ መልሰኝ፤ እኔም እመለሳለሁ። ከአንተ ከራቅሁ በኋላ፣ ተመልሼ ተጸጸትሁ፤ ባስተዋልሁም ጊዜ፣ ጭኔን መታሁ፤ የወጣትነት ውርደቴን ተሸክሜአለሁና ዐፈርሁ፤ ቀለልሁም።’ ኤፍሬም የምወድደው፣ ደስም የምሰኝበት ልጄ አይደለምን? ብዙ ጊዜ ተቃውሜው ብናገርም፣ መልሼ ስለ እርሱ ዐስባለሁ፤ አንጀቴ ይላወሳል፤ በታላቅ ርኅራኄም እራራለታለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። “የጐዳና ምልክት አቁሚ፤ መንገድ አመልካች ትከዪ፤ የምትሄጂበትን መንገድ፣ አውራ ጐዳናውን አስተውዪ፤ ድንግሊቱ እስራኤል ሆይ፤ ተመለሺ፤ ወደ ከተሞችሽም ግቢ። አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ይፈጥራል፤ ሴት በወንድ ላይ ከበባ ታደርጋለች።”

ኤርምያስ 31:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በዚያን ዘመን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፥ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ እንደ ገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፥ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ዘፈን ትወጫለሽ። እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክሊአለሽ፥ አትክልተኞች ይተክላሉ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል። በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ጠባቆች፦ ተነሡ፥ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና። እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ስለ ያዕቆብ ደስ ይበላችሁ ስለ አሕዛብም አለቆች እልል በሉ፥ አውሩ፥ አመስግኑ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል በሉ። እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፥ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፥ በመካከላቸውም ዕውሩና አንካሳው ያረገዘችና የወለደችም በአንድነት፥ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ። በልቅሶ ወጡ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፥ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፥ በእርሱም አይሰናከሉም፥ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና። አሕዛብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፦ እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ። እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶታል፥ ከበረቱበትም እጅ አድኖታል። ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ እልል ይላሉ፥ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ፥ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም። በዚያን ጊዜም ድንግሊቱ በዘፈን ደስ ይላታል፥ ጐበዛዝቱና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፥ ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እመልሳለሁ፥ አጽናናቸውማለሁ፥ ከኅዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ። የካህናቱንም ነፍስ በብዛት አረካታለሁ ሕዝቤም በጎነቴን ይጠግባል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ድምፅሽን ከልቅሶ ዓይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፥ ለሥራሽ ዋጋ ይሆናልና፥ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ። ለፍጻሜሽም ተስፋ አለ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ። ኤፍሬም፦ ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፥ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ። ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ ጭኔን ጸፋሁ፥ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፥ ተዋረድሁም ብሎ ሲያለቅስ ሰማሁ። በእውነት ኤፍሬም ለእኔ የከበረ ልጅ ነውን? ወይስ የተወደደ ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አስበዋለሁ፥ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። ለራስሽ የመንገድ ምልክት አድርጊ፥ መንገድንም የሚመሩ ዓምዶችን ትከዪ፥ ልብሽንም ወደ ሄድሽበት መንገድ ወደ ጥርጊያው አቅኚ፥ አንቺ የእስራኤል ድንግል ሆይ፥ ተመለሺ፥ ወደ እነዚህም ወደ ከተሞችሽ ተመለሺ። አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፥ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሴት ወንድን ትከብባለች።

ኤርምያስ 31:1-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የእስራኤል ነገዶች ሁሉ አምላክ የምሆንበትና እነርሱም ሕዝቤ የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ እስራኤል ዕረፍትን ለማግኘት ወደ ፊት በመጣ ጊዜ ከጦርነት የተረፉት በምድረ በዳ የእኔን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛሉ። እኔ ለእነርሱ ከሩቅ ተገለጥኩላቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ እነሆ እናንተን ለዘለዓለም ወደድኳችሁ፤ ዘለዓለማዊ ቸርነቴም ለእናንተ የጸና ይሆናል። ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ። እንደገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ ወይን ትተክዪአለሽ ፍሬውንም የደከሙበት ሰዎች ይበሉታል፤ ጠባቂዎች በኤፍሬም ተራራ ላይ ሆነው ‘ኑ አምላካችን እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጽዮን እንሂድ’ የሚሉበት ጊዜ ይመጣል።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከሕዝቦች ሁሉ ስለምትበልጥ ስለ እስራኤል በደስታ ዘምሩ፤ ‘እግዚአብሔር ሕዝቡን አድኖአል፤ በእስራኤል ምድር የቀሩትን ሁሉ ተቤዥቶአል’ እያላችሁ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ።” “እኔ ከሰሜን አመጣቸዋለሁ፤ ከምድር ዳርቻም እሰበስባቸዋለሁ፤ ዕውሮች፤ አንካሶች፥ ነፍሰጡሮችና በምጥ የተያዙ ሴቶች ሁሉ ከእነርሱ ጋር አብረው ይመጣሉ፤ ታላቅ ሕዝብ ሆነው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፤ እኔ ወደ አገራቸው ስመራቸው ሕዝቤ ከደስታ የተነሣ እያለቀሱና እየጸለዩ ይመለሳሉ። በማይሰናከሉበት የተስተካከለ መንገድ ወደ ጥሩ ውሃ ምንጭ እመራቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝ፤ ኤፍሬምም የበኲር ልጄ ነው።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ። እኔ የእስራኤልን ሕዝብ ነጻ አውጥቼአቸዋለሁ፤ ከኀያል መንግሥትም እጅ በመታደግ አድኛቸዋለሁ፤ ስለዚህም ተመልሰው መጥተው በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በምሰጣቸውም የእህል፥ የወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ የበግና የቀንድ ከብት በረከት ሁሉ ተድላ ደስታ ያደርጋሉ፤ በቂ ውሃ እንዳገኘች የተክል ቦታ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህ ወዲያም አያዝኑም። ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤ ካህናቱን በምድሪቱ በረከት አጠግባቸዋለሁ፤ ለሕዝቤም ቸርነቴን አትረፈርፍላቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ ታለቅሳለች፤ ልጆችዋ በሕይወት ስለሌሉ መጽናናትን እምቢ አለች። ለቅሶአችሁን አቁማችሁ እንባችሁን ጥረጉ፤ ስለ ልጆቻችሁ ያደረጋችኹት ነገር ሁሉ ያለ ዋጋ አይቀርም፤ እነርሱ ከጠላት አገር ተመልሰው ይመጣሉ። ልጆቻችሁ ወደ አገራቸው ተመልሰው ስለሚመጡ፥ የወደፊት ተስፋ አላችሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። “የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን። ከአንተ ርቀን ብንሄድም እንኳ አሁን ንስሓ ገብተናል፤ በዕፍረትና በጸጸት ራሳችንን ዝቅ አድርገን ደረታችንን እንመታለን፤ በወጣትነት ዘመናችን ለፈጸምነው ኃጢአት ራሳችንን እንወቅሳለን።’ “እስራኤል ሆይ! እናንተ የተወደዳችሁ ልጆቼ ናችሁ፤ ከሁሉ አስበልጬ የምወዳችሁ አይደለምን? ምሕረት አደርግላችሁ ዘንድ ወደ እኔ ላቀርባችሁ እፈቅዳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። ለራሳችሁ የመንገድ ምልክቶችን አድርጉ፤ መንገድንም የሚመሩ ዐምዶችን ትከሉ፤ የሄዳችሁበትን ዐውራ ጐዳና አተኲራችሁ ተመልከቱ፤ ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ወደ እነዚህ ከተሞቻችሁ ተመለሱ። እናንተ እምነት የጐደላችሁ ሕዝብ፥ እስከ መቼ ታመነታላችሁ? እኔ እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገርን ፈጥሬአለሁ፤ ይኸውም ሴት ለወንድ ትከላከላለች። ልዩ የሆነ አዲስ ነገር ፈጥሬአለሁ።”

ኤርምያስ 31:1-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚያን ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። ጌታ እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ጌታም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ፦ “በዘለዓለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በጽኑ ፍቅር ሳብሁሽ። የእስራኤል ድንግል ሆይ! እንደገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ሐሤት በሚያደርጉ ዘፋኞች ሽብሸባ እያሸበሸብሽ ትወጫለሽ። እንደገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ ወይንን በወይን እርሻዎች ትተክዪአለሽ፤ አትክልተኞች ይተክላሉ እነርሱም በፍሬው ይደሰታሉ። በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ጠባቂዎች፦ ‘ተነሡ፥ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ ጌታ እንውጣ’ ብለው የሚጣሩበት ቀን ይመጣልና።” ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ስለ ያዕቆብ በደስታ ዘምሩ ስለ አሕዛብም አለቆች እልል በሉ፤ አውጁ፥ አመስግኑ፦ ጌታ ሆይ! ሕዝብህን የእስራኤልን ትሩፍ አድን በሉ። እነሆ፥ ከሰሜን አገር አመጣቸዋለሁ፤ ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ፤ በመካከላቸውም ዓይነ ስውርና አንካሳው ያረገዘችና ምጥ የያዛትም በአንድነት ይሆናሉ፤ ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ። በልቅሶ ይወጣሉ፤ እኔንም በመማፀናቸው እየመራሁ እመልሳቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስኬዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኩሬ ነውና። አሕዛብ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፥ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፥ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል” በሉ። ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶታል፥ ከበረታበትም እጅ አድኖታል። ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም። በዚያን ጊዜም ድንግሊቱ በሽብሸባ ትደሰታለች፥ ጉልማሶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ ልቅሶአቸውንም ወደ ደስታ እለውጣለሁ፥ አጽናናቸዋለሁም፥ ከኀዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ። የካህናቱንም ነፍስ በብዛት አረካታለሁ ሕዝቤም በጎነቴን ይጠግባል፥ ይላል ጌታ። ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።” ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ድምፅሽን ከልቅሶ ዓይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ለሥራሽ የሚከፈልሽ ዋጋ ይሆናልና፥ ከጠላትም ምድር ይመለሳሉ፥ ይላል ጌታ። ለወደፊት ላለሽ ጊዜ ተስፋ አለሽ፥ ይላል ጌታ፥ ልጆችሽም ወደ ግዛታቸው ይመለሳሉ። በእውነት ኤፍሬም ሲያለቅስ ሰማሁ፦ ‘ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ ጌታ አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ። ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ በኀዘን ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ ተዋረድሁም።’ በእውነት ኤፍሬም የተወደደ ልጄ ነውን? ወይስ ደስ የምሰኝበት ሕፃን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር አሁንም ድረስ በትክክል አስታውሰዋለሁ፤ ስለዚህ አንጀቴ ታወከችለት ርኅራኄም እራራለታለሁ፥ ይላል ጌታ። “ለራስሽ የመንገድ ምልክት አድርጊ፥ መንገድንም የሚመሩ ዓምዶችን ትከዪ፥ የሄድሽበትን መንገድ ዐውራ ጐዳናውን ልብ አድርገሽ ተመልከቺ፤ አንቺ የእስራኤል ድንግል ሆይ! ተመለሺ፥ ወደ እነዚህም ወደ ከተሞችሽ ተመለሺ። አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ታመነቻለሽ? ጌታ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሴት ወንድን ትከብባለች።”