ዕዝራ 10:5-6
ዕዝራ 10:5-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹንና ካህናቱንም፥ ሌዋውያኑንም፥ እስራኤልን ሁሉ እንደዚህ ቃል ያደርጉ ዘንድ አማላቸው፤ እነርሱም ማሉ። ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤሊያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኀጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም።
Share
ዕዝራ 10 ያንብቡዕዝራ 10:5-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ዕዝራም ተነሥቶ ዋና ዋናዎቹ ካህናት፣ ሌዋውያንና እስራኤል ሁሉ የቀረበውን ሐሳብ እንዲፈጽሙ አስማላቸው፤ እነርሱም ማሉ። ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ፤ ምርኮኞቹ ታማኞች ሆነው ባለ መገኘታቸው ያለቅስ ነበር፤ በዚያም ምግብ አልቀመሰም፤ ውሃም አልጠጣም።
Share
ዕዝራ 10 ያንብቡዕዝራ 10:5-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዕዝራም ተነሣ፤ አለቆቹንና ካህናቱን፥ ሌዋውያኑንና እስራኤልን ሁሉ እንደዚህ ቃል ያደርጉ ዘንድ አማለ፤ እነርሱም ማሉ። ዕዝራም ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ጓዳ ገባ፤ ስለ ምርኮኞቹም ኃጢአት ያለቅስ ነበርና ገብቶ እንጀራ አልበላም፤ ውኃም አልጠጣም።
Share
ዕዝራ 10 ያንብቡ