የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕዝራ 10:1-4

ዕዝራ 10:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዕዝ​ራም እያ​ለ​ቀ​ሰና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​ወ​ደቀ በጸ​ለ​የና በተ​ና​ዘዘ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ የወ​ን​ድና የሴት፥ የሕ​ፃ​ና​ትም እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰበ፤ ሕዝ​ቡም እጅግ አለ​ቀሱ። ከኤ​ላም ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውም የኢ​ያ​ሔል ልጅ ሴኬ​ንያ ዕዝ​ራን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ እን​ግ​ዶች ሴቶ​ችን አግ​ብ​ተ​ናል፤ አሁን ግን ስለ​ዚህ ነገር ገና ለእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ አለ። አሁ​ንም እንደ ጌታ​ዬና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ትእ​ዛዝ እን​ደ​ሚ​ፈ​ሩት ምክር፥ ሴቶ​ችን ሁሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን እን​ሰ​ድድ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ጋር ቃል ኪዳን እና​ድ​ርግ። ተነሥ እንደ አም​ላ​ካ​ች​ንም ትእ​ዛዝ ገሥ​ፃ​ቸው፤ እንደ ሕጉም ያድ​ርጉ፤ ይህም ነገር ለአ​ንተ ይገ​ባ​ልና፥ እኛም ከአ​ንተ ጋር ነንና ተነሣ፤ በርታ፤ አድ​ር​ገ​ውም።”