ዘፀአት 7:14-25
ዘፀአት 7:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ። ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፤ ትገናኘውም ዘንድ አንተ በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ እባብም ሆና የተለወጠችውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ። እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆም እስከ ዛሬ አልሰማህም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል። በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’” እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፥ ‘በትርህን ውሰድ፤ ደምም እንዲሆኑ በግብፅ ውኆች በወንዞቻቸውም በመስኖቻቸውም በኩሬዎቻቸውም በውኃ ማከማቻዎቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ በግብፅም አገር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።” ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፤ በፈርዖንና በባሪያዎቹም ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ። በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ አገር ሁሉ ነበረ። የግብፅም ጠንቍዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም። ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ ይህንም ደግሞ በልቡ አላኖረውም። ግብፃውያንም ሁሉ የወንዙን ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ አጠገብ ውኃ ሊጠጡ ቆፈሩ። እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።
ዘፀአት 7:14-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝቡን እንዳይለቅቅ የፈርዖን ልብ ደነደነ። ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነሆ፥ ወደ ውኃ ይወጣል፤ ትገናኘውም ዘንድ አንተ በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ እባብም ሆና የተለወጠችዉን በትር በእጅህ ትወስዳለህ። እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆም፥ እስከ ዛሬ አልሰማህም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል። በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት አይችሉም።” እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ውሰድ፤ በግብፅ ውኆች፥ በወንዞቻቸው፥ በመስኖዎቻቸውም፥ በኩሬዎቻቸውም፥ በውኃ ማከማቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆናል፤” በግብፅም ሀገር ሁሉ በዕንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ። ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን አነሣ፤ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ። በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ። የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም። ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ በዚህም ሁሉ ልቡ አልተመለሰም። ግብፃውያንም ሁሉ ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ ዳር ውኃ ሊጠጡ ቈፈሩ። እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።
ዘፀአት 7:14-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡን ለመልቀቅ አልፈቀደም። ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እንድታገኘውም በአባይ ዳር ተጠባበቅ፤ ወደ እባብ ተለውጣ የነበረችውንም በትር በእጅህ ያዝ። ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር “ሕዝቤ በምድረ በዳ ያመልኩኝ ዘንድ እንዲሄዱ ልቀቃቸው” ብዬ እንድነግርህ ላከኝ፤ አንተ ግን እስካሁን ድረስ ዕሺ አላልህም። እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ “እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እይ! በዚህች በእጄ በያዝኋት በትር የአባይን ውሃ እመታለሁ፤ ወደ ደምም ይለወጣል። በአባይ ወንዝ ውስጥ ያለው ዓሣ ይሞታል፤ ወንዙ ይከረፋል፤ ግብጻውያንም ውሃውን መጠጣት አይችሉም።” ’ ” እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “አሮንን፣ ‘በትርህን ውሰድና በግብጽ ውሆች ላይ፣ ይኸውም በምንጮች፣ በቦዮች፣ በኵሬዎችና በውሃ ማጠራቀሚያዎች ላይ እጅህን ዘርጋ’ ብለህ ንገረው፤ ወደ ደምም ይለወጣሉ። ከዕንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ውሃ መያዣዎች ውስጥም ሳይቀር በግብጽ ምድር ደም በየቦታው ይሆናል።” ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንደ አዘዛቸው አደረጉ። እርሱም በፈርዖንና በሹማምቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የአባይን ወንዝ ውሃ መታ፤ ውሃውም በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ። በአባይ ያሉት ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ከመከርፋቱ የተነሣ ግብጻውያኑ ውሃውን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብጽ ምድር ሁሉ ደም ነበረ። የግብጽ አስማተኞች በድብቅ ጥበባቸው ተመሳሳይ ነገር አደረጉ፤ የፈርዖንም ልብ ደነደነ፤ ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም። ተመልሶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገባ እንጂ ይህን ከቁም ነገር አልቈጠረውም። ግብጻውያን ሁሉ የወንዙን ውሃ መጠጣት ባለመቻላቸው ውሃ ለማግኘት የአባይን ዳር ይዘው ጕድጓድ ቈፈሩ። እግዚአብሔር አባይን ከመታ ሰባት ቀን ሞላ።
ዘፀአት 7:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ። ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፤ ትገናኘውም ዘንድ አንተ በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ እባብም ሆና የተለወጠችውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ። እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆም እስከ ዛሬ አልሰማህም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል። በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’” እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “አሮንን፥ ‘በትርህን ውሰድ፤ ደምም እንዲሆኑ በግብፅ ውኆች በወንዞቻቸውም በመስኖቻቸውም በኩሬዎቻቸውም በውኃ ማከማቻዎቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ በግብፅም አገር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።” ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፤ በፈርዖንና በባሪያዎቹም ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ። በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ አገር ሁሉ ነበረ። የግብፅም ጠንቍዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም። ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ ይህንም ደግሞ በልቡ አላኖረውም። ግብፃውያንም ሁሉ የወንዙን ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ አጠገብ ውኃ ሊጠጡ ቆፈሩ። እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።
ዘፀአት 7:14-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ንጉሡ ልቡን በማደንደን ሕዝቡን አለቅም ብሎአል፤ ስለዚህ ጠዋት በማለዳ ወደ ንጉሡ ሂድ፤ ወደ ዐባይ ወንዝ ሲወርድ ወደ እባብነት የተለወጠችውን በትር ይዘህ በወንዙ ዳር ቆመህ ጠብቀው። እንዲህም በለው፥ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር በበረሓ ያገለግሉት ዘንድ ሕዝቡን እንድትለቅ እንድነግርህ ወደ አንተ ልኮኛል፤ አንተ ግን እስከ ዛሬ እምቢ ብለሃል። አሁን ግን በሚያደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ማንነት በግድ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ፤ ውሃውም ወደ ደም ይለወጣል። በውስጡ ያሉ ዓሣዎች ሁሉ ይሞታሉ፤ የዐባይ ውሃ በጣም ከመሽተቱ የተነሣ ግብጻውያን ከዚህ ወንዝ ውሃ ቀድተው መጠጣት አይችሉም።’ ” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮን በትሩን ወስዶ በግብጽ ምድር በሚገኙት ወንዞች፥ ቦዮችና ኲሬዎች ሁሉ ላይ እንዲዘረጋ ንገረው፤ በዚያን ጊዜ ውሃው ሁሉ ተለውጦ ደም ይሆናል፤ ከእንጨትና ከድንጋይ በተሠሩት የውሃ ማጠራቀሚያ ዕቃዎች እንኳ ሳይቀር በግብጽ ምድር የሚገኘው ውሃ ሁሉ ደም ይሆናል።” ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የወንዙን ውሃ መታው። የወንዙም ውሃ ተለውጦ ደም ሆነ፤ በወንዝ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ሁሉ ሞቱ፤ የዐባይ ወንዝ ውሃ ስለ ገማ ግብጻውያን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብጽ ምድር ደም የሌለበት ስፍራ አልነበረም። ከዚህ በኋላ የንጉሡ አስማተኞች በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ፤ ንጉሡም ልቡን በማደንደን ጸና፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ማዳመጥ እምቢ አለ። የሆነውን ነገር ሁሉ ከቁም ነገር ሳይቈጥረው ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመልሶ ሄደ። ግብጻውያን ከዐባይ ወንዝ ውሃ መጠጣት ስላልቻሉ የሚጠጣ ውሃ ለማግኘት ከዐባይ ወንዝ ዳር ጒድጓድ ቈፈሩ። እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን አለፈ።
ዘፀአት 7:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታም ሙሴን አለው፦ “የፈርዖን ልብ ደነደነ፥ ሕዝቡንም አልለቅም አለ። ወደ ፈርዖን በጠዋት ሂድ፤ እነሆ ወደ ውኃ ይወጣል፥ አንተም እንድትገናኘው በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ ወደ እባብም የተለወጠውን በትር በእጅህ ትወስዳለህ። እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘ጌታ የዕብራውያን አምላክ፦ በምድረ በዳ እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ፥ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆ አንተ እስከ ዛሬ አልሰማህም። ጌታ እንዲህ ይላል፦ እኔ ጌታ እንደሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ በዓባይ ወንዝ ያለውን ውኃ በእጄ ባለው በትር እመታለሁ፥ ወደ ደምም ይለወጣል። በዓባይ ወንዝ ያሉትም ዓሦች ይሞታሉ፥ የዓባይ ወንዝም ይገማል፤ ግብፃውያንም የዓባይን ወንዝ ውኃ ለመጠጣት ይጠላሉ።’” ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘በትርህን ውሰድ፥ በግብጽ ውኆች፥ በፈሳሾቻቸው፥ በወንዞቻቸው፥ በኩሬዎቻቸው፥ በውኃ ማጠራቀሚያዎቻቸውም ላይ ደም እንዲሆኑ እጅህን ዘርጋ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ በእንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ይሆናል።’” ሙሴና አሮንም ልክ ጌታ እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፥ በፈርዖንና በአገልጋዮቹም ፊት በዓባይ ወንዝ የነበረውን ውኃ መታ፤ በዓባይ ወንዝ ላይ የነበረው ውኃ ሁሉ ወደ ደም ተቀየረ። በዓባይ ወንዝ የነበሩ ዓሦችም ሞቱ፤ የዓባይም ወንዝ ገማ፥ ግብጻውያንም ከዓባይ ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉም፤ ደሙም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ነበረ። የግብጽም አስማተኞች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ የፈርዖንም ልብ ጸና፥ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም። ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፥ ይህንም ደግሞ በልቡ አላኖረውም። ግብጽም ሁሉ የዓባይ ወንዝ አካባቢውን ቆፈሩ የዓባይን ወንዝ ውኃ መጠጣት አልቻሉምና። ጌታ ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።