እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝቡን እንዳይለቅቅ የፈርዖን ልብ ደነደነ። ማልደህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነሆ፥ ወደ ውኃ ይወጣል፤ ትገናኘውም ዘንድ አንተ በወንዝ ዳር ትቆማለህ፤ እባብም ሆና የተለወጠችዉን በትር በእጅህ ትወስዳለህ። እንዲህም ትለዋለህ፦ ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር፦ በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነሆም፥ እስከ ዛሬ አልሰማህም። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል። በወንዙም ያሉት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙም ይገማል፤ ግብፃውያንም የወንዙን ውኃ ለመጠጣት አይችሉም።” እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ውሰድ፤ በግብፅ ውኆች፥ በወንዞቻቸው፥ በመስኖዎቻቸውም፥ በኩሬዎቻቸውም፥ በውኃ ማከማቻቸውም ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆናል፤” በግብፅም ሀገር ሁሉ በዕንጨት ዕቃና በድንጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ። ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን አነሣ፤ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ። በወንዙም የነበሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወንዙም ገማ፤ ግብፃውያንም ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉም፤ ደሙም በግብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ። የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም። ፈርዖንም ተመልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ በዚህም ሁሉ ልቡ አልተመለሰም። ግብፃውያንም ሁሉ ከወንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አልቻሉምና በወንዙ ዳር ውኃ ሊጠጡ ቈፈሩ። እግዚአብሔርም ወንዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈጸመ።
ኦሪት ዘፀአት 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 7:14-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች